በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


ትክክለኛው ኢስላማዊ አስተምህሮ፦
👉 ከቁርኣን፣
👉ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ]
👉 ከታማኝ ዑለማዎችና
👉ከትክክለኛ ቂያስ ተጠናቅሮ ይቀርብበታል።
ማንኛውም አስተያዬት ሲኖራችሁ  @Abu_Sibewe ላይ አስፍሩት።
ስህተትም ባያችሁ ጊዜ አርሙኝ።
ጀዛኩሙል`ሏህ ኸይራ!

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


{ ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ ٱلَّذِيٓ أَنزَلَ عَلَىٰ عَبۡدِهِ ٱلۡكِتَٰبَ وَلَمۡ يَجۡعَل لَّهُۥ عِوَجَاۜ }📚

➪ምስጋና ለአላህ ለዚያ መጽሐፉን በውስጡ መጣመምን ያላደረገበት ሲሆን በባሪያው ላይ ላወረደው ይገባው፡፡


https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik


◉አንድን ሰው ሙሉ ለሙሉ ስታምን ከሁለት ነገሮች አንዱን ታገኛለህ!!


❶የእድሜ ልክ ጓደኛ ወይም !!
❷የእድሜ ልክ ትምህርት!!


➴ሁለት ሸይኾች ታክሲ መሳፈር ፈለጉና አንዱ ሸይኽ ለባለታክሲው ስንት ትወስደናለህ?ብለው ጠየቁ
ባለታክሲውም ከነሱ ሂሳብ መቀበል አልፈለገምና 'ሊላህ' (ለአላህ ) ብየ ነው የምወስዳችሁ አላቸው
አንደኛው ሸይኽም ፦በነፃ ከሆነ
#በጣም_አስወደድከው ብለው መለሱ
አንድ ሰው ለአላህ ብሎ እርዳታ ሲያደርግልህ አንተ ነህ በነፃ  የተገለገልከው እሱ ግን ወጪ የማይሆን ሂሳብ. ለአኼራው አስቀምጧልና።

ጌታችን ሆይ! መልካም ሰርተው በመልካም ከምትመነዳቸው ባሮችህ አድርገን
  
https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik


◉የረመዳን ወር አቀባበል!!

ክፍል ❶

ታላቁ እንግዳችን! የተከበረውን የረመዳን ወር ለመቀበል ሁሉም በየፊናው ተፍተፍ እያለ ይገኛል። ከፊሉ ቤቱን በማሰናዳት፣ ሌላው የምግብ አይነቶችን በመሸመት፣ እኩሉም የወሩን ትሩፋት ለመጠቀም እቅድ እያወጣ…ወዘተ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

ለመሆኑ ይህ አያሌ የፈጣሪ ትሩፋትን በውስጡ ይዞ የመጣውን ይህን ወር ለመቀበል ትክክለኛው መንገድ የትኛው ነው?

በወሩ ውስጥ ያሉትን እያንዳንዱን የጦዓ (አምልኮ) ወቅቶችን ሁሉ አሟጦ ለመጠቀም ምን ማድረግ ይጠበቅብናል? በነዚህ በተከበሩ ጊዜያት ውስጥ በኸይር ነገሮች መሽቀዳደም ያስፈልጋልና፤ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡-

وَفِي ذَٰلِكَ فَلْيَتَنَافَسِ الْمُتَنَافِسُونَ

“በዚህም ተሽቀዳዳሚዎች ይሽቀዳደሙ።”(አል-ሙጦፊፊን 83፤ 26)
በመሆኑም ከዚህ በመቀጠል የረመዳንን ወር በተሻለ መንገድ ለመቀበል የሚረዱ መንገዶች እንጠቁማለን፡-

❶ ዱዐ ማድረግ፡- በፆም፤ በሶላትና በዚክር ላይ እንድትጠነክር አላህ (ሱ.ወ) በሙሉ ጤንነትና አቅም ላይ ሆነህ ረመዳን ወር እንዲያደርስህ ከአሁኑ ዱዓ አድርግ፤ አነስ ቢን ማሊክ (ረ.ዐ) ነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ) የረጀብ ወር ሲገባ እንዲህ ይሉ ነበር ብለዋል፡-

اللهم بارك لنا في رجب وشعبان وبلغنا رمضان

“አላህ ሆይ! ረጀብንና ሸዕባንን ብሩክ አድርግልን፤ ረመዳንንም አድርሰን” (አህመድና ጦብራኒ ዘግበውታል)።

ሰለፎች (ቀደምት ደጋግ አቦዎች) ረመዳንን እንዲያደርሳቸውና ከዚያም ሥራቸውን እንዲቀበላቸው አላህን (ሱ.ወ) ይለምኑ ነበር፤ ስለዚህ አንተም የረመዳን ጨረቃ ስትወጣ እንዲህ ብለህ ዱዓ አድርግ፡-

الله أكبر اللهم أهله علينا بالأمن والإيمان والسلامة والإسلام , والتوفيق لما تحب وترضى ربي وربك الله

“አላሁ አክበር አላህ ሆይ! ይህን ጨረቃ የአማንና የኢማን፣ የሰላምና የኢስላም፣ እንዲሁም አንተን የሚያስደስት ተግባር መስራት የምንችልበት ጊዜ አድርግልን፤ የኔም የአንተም ጌታ አላህ ነው፤” (ቲርሚዚ ዘግበውታል)።

❷ ምስጋና ማቅረብ፡- ረመዳን ወር ከደረስክ ምስጋና ለአላህ አቅርብ፤ ኢማሙ ነወዊይ አል-አዝካር በተባለው ኪታባቸው ውስጥ እንዲህ ብለዋል

“አንድ አዲስ ፀጋን ያገኘ ወይም አንድ ችግር የተወገደለት ሰው ለአላህን ምስጋና ለማቅረብ ሱጁድ አድረጎ አላህን በሚገባው መልኩ ማወደስ ይገባዋል።

”አላህን ማምለክና የሱን ትእዛዝ መፈጸም መቻል በራሱ አላህ (ሱ.ወ) ለአንድ ሙእሚን ከሚለግሰው ታላላቅ ፀጋዎች ነው።

አንድ ሙእሚን የረመዳን ወር ሲገባ በጥሩ ጤንነት ላይ መገኘቱ ብቻ ፀጋውንና ችሮታውን ለለገሰው አላህ (ሱ.ወ) ምስጋና እንዲያቀርብ የሚያስገድደው በቂ ነገር ነው፤

ስለዚህ የረመዳንን ወር በሰላምና በጤና የደረሰ ሰው ለአላህ (ሱ.ወ) ትልቅ ምስጋና ሊያቀርብና እሱን በብዛት ሊያወድስ ይገባል፤ ለልቅናውና ለግዙፍ ስልጣኑ የሚመጥን ታላቅ ምስጋናና ውዳሴ ለአላህ (ሱ.ወ) ይሁን!!

❸ መደሰት፡- ነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ) የረመዳን ወር ሲመጣ እንዲህ በማለት ባልደረቦቻቸውን ያበስሩ እንደነበር ተረጋግጧ፡-

جاءكم شهر رمضان شهر مبارك كتب الله عليكم صيامه فيه تفتح أبواب الجنان وتغلق فيه أبواب الجحيم

“የተባረከው የረመዳን ወር መጥቶላችኋል፤ እሱን መፆም አላህ (ሱ.ወ) በናንተ ላይ ደንግጓል፤ በረመዳን ወር የጀነት በሮች ይከፈታሉ፤ የገሀነም በሮች ደግሞ ይዘጋሉ”(አህመድ ዘግበውታል)።

ሰሐባዎችንና ታቢዒዮችን ጨምሮ ያለፉት ደጋግ አቦዎች (ሰለፎች) ለረመዳን ወር ልዩ ትኩረት ይሰጡ ነበር፤ ረመዳን ሲመጣም ይደሰቱ ነበር፤ አዎ ይህ ትልቅ ደስታ ነው!

የኸይርና የአላህ እዝነት መውረጃ የሆነ ወቅት ሲመጣ ጤና ሆኖ በሂይወት ከመኖር የበለጥ የሚያስደስት ነገር አለን?!

❹ ወሩን በአግባቡ ለመጠቀም መወሰንና ቀድሞ እቅድ ማውጣት፡- ብዙ ሙስሊሞች- ዲነኞችን ጨምሮ- ለዱንያ ጉዳያቸው በሚገባ እቅድ ሲያወጡ ይታያሉ፤ ነገር ግን ለአኺራቸው እቅድ በማውጣት የሚሰሩት ጥቂቶች ናቸው።

ይህም የሚሆንበት ምክንያት ሙእሚን በዚች ህይወት ያለውን መልዕክት ካለመረዳትና አንድ ሙእሚን ነፍሱ በአላህ ዲን ላይ ፅናት እንዲኖራት ራሱን ለማለማመድ ከአላህ ዘንድ የሚገኙ መልካም አጋጣሚዎች ችላ ከማለት የሚመነጭ ነው።

ለአኺራ ከምናቅድባቸው ጉዳዮች መካከል የረመዳንን ወር በጧዐና ኢባዳ ለማሳለፍ የምናደርገው ዝግጅትና እቅድ አንዱ ነው፤ ስለሆነም ማንኛውም ሙስሊም የረመዳንን ወር በትክክል አላህን በመታዘዝ ማሳለፍ እንዲችል ተግባራዊ ሊሆን የሚችል ፕሮግራም ማውጣት ያስልገዋል።

❺ ቁርጠኛ አቋም፡- የረመዳንን ወር በመልካም ሥራዎች ለመሙላት ቁርጠኛ አቋም መያዝ። ከልቡ በእውነት ወደ አላህ የቀረበ ሰው አላህ ይቀበለዋል፤ እሱን ለመገዛትና ኸይር ለመስራትም ያግዘዋል፤ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡-

فَلَوْ صَدَقُوا اللَّهَ لَكَانَ خَيْرًا لَّهُمْ

“እውነተኞች በኾኑ ኖሮ ለእነርሱ የተሻለ በኾነ ነበር።” (ሙሐመድ 47፤ 21)

   
#ሼር #ሼር ይደረግ

ክፍል ❷

  ቀ
     ጥ
      ላ
       ል
 
https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik


እጅግ በርካታ ሰዎች በሚዘነጉበት ወር ትልቅ እድል እስቲ ወጣ ብላቹ ጨረቃዋ እንዴት እንዳሸበረቀች ተመልከቷትማ

ነጌ ጀምሮ እስከ ጁሙዐ አያመል ቢድ ነው እንዳያመልጠን

ነጌ ሮብ 13
ሀሙስ 14
ጁሙዐ 15

የአላህ መልእክተኛ ﷺ"በረጀብ እና በረመዷን መካከል የሚገኘው የሸዕባን ወር ብዙ ሰዎች የሚዘናጉበትወር ነው።
በዚህ ወርም መልካም ሥራዎች ወደ ዓለማት ጌታ ይቀርባሉ እኔደግሞ ((ፆመኛ)) ሆኜ ሥራዬ እንዲወጣልኝ እወዳለሁ ብለዋል።"


መፆም ባንችል እንኳ ሌላውን እናስታውስ

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik


قال بعد أهل العلم
شهر شعبان شهر تخلية
وشهر رمضان شهر تحلية


የሸዕባን ወር ውዳቂ ከሆኑ ተግባሮቻችን እራሳችንን ለማፅዳት የምንታገልበት እና ፅድት የምንልበት ወር ሲሆን

የረመዳን ወር ደሞ በተለያዩ መጌጫዎች የምናጌጥበት ወር ነው

ቆሻሻውን ማስወገድ ከማስጌጥ ይቀደማል❗️


☞ለረመዳን መዘጋጀት ያስፈልጋል

وقال تعالى :( ﻭَﻟَﻮْ ﺃَﺭَﺍﺩُﻭﺍ ﺍﻟْﺨُﺮُﻭﺝَ ﻷَﻋَﺪُّﻭﺍ ﻟَﻪُ ﻋُﺪَّﺓً )
(መውጣትን ቢፈልጉ ኖሮ መዘጋጀትን ይዘጋጁ ነበር )

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
➴➴ምንኛ ያማረች ምክር‼


◉ አያት ለልጅ ልጁ የመከረው ጣፋጭ ምክር!

√➳ የምትወደውን ሰው ማሞገስ አታብዛ፣
√➳ ጌታውን ከማይታዘዝ ሰው ጋር አትጓዝ፣
√➳ ቁጭ ስትል ሰዎችን አትማ፣
√➳ በራሱ ጊዜ ከአንተ የራቀን ጓደኛ ለመቅረብ አትሯሯጥ፣
√ ራስህን አታቅል፥ አትኩራ፣
√➳ እጅግም አትለሳለስ፥ እጅግም አትንጠባረር፣
√➳ እውነቱን የሚያወራ ሰው በብዛት አይምልም፥ ታማኝ ሰው ራሱን መልካም አድርጎ አይስልም፣
√➳ ሥራውን ለአላህ ብሎ የሚሠራ ሰው ኋላ ላይ አይጸጸትም፣
√➳ ቸር ሰው አይመጻደቅም፣
√➳ ራስህን ሁን፥ ሌሎች እንደሚፈልጉት አትሁን፣
√ ➳ሰዎችን ማክበርህ የሆነ የምትፈልግባቸው ጉዳይ አለ ማለት አይደለም። ስለ ዲንህና አስተዳደግህ ልታስተምራቸው ጅማሮ እንጅ፣
√ ➳አክብር → ትከበራለህ!
√➳ በጸባይህ ውብ ሁን!
√➳ ባለህ ተብቃቃ፥ ራስህን ዝቅ በማድረግ ትልቅ ሁን።
√➳ ከኋላህ ሆኖ ስለአንተ ወደሚያወራ ሰው አትመልከት። ምክንያቱም እርሱ በመሠረቱ ከኋላህ እንጅ ከፊት ለፊትህ አይደለም።
√➳ ከቁርኣን ምን ያክል እንደምትሸመድድና እንደምትቀራ ለሰዎች አትንገራቸው። ይልቁንም በአንተ ውሰጥ ቁርኣንን እንዲያዩ አድርጋቸው።
√➳ የተራበን አብላ፣ የተራቆተን አልብስ፣ እርዳታህን የሚሻን አግዝ፣ ለየቲም እዘን፣ የበደለህን እለፈው፣ ለወላጆችህ መልካም ዋል፣ ለሁሉም ፈገግ በል!
√➳ ቁም ነገሩ ከቁርኣን ምን ያክል ደርሰሐል ወይንም ሸምደሃል ሳይሆን፤ ቁርኣን በአንተ ውስጥ የት ደርሷል የሚለው ነው።


https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik


وَصَـايَـا جَليلَة من الشيخ الفوزان حفظه الله تعالى :

📌قـال الـشّيخ الـعلّامة صالح بن فوزان الـفوزان حفظه الله تعالى :
ሸይህ ፈውዛን እንድህ ይሉናል

الّذِي نـُوصِي بِهِ أَنـفُـسَنَـا وَإِخْـوَانَنَـا :
እኔ ለራሴም ለወንድሞቸም የምመከረው
①- تَـقـْوَى الله والـتّمَسُـكُ بِمَنْـهَجِ الـسّـلـفِ الـصَّالـِحِ
አላህን መፍራት እና የሰለፎችን ፣ የሷሊሆችን መንገድ አጥብቆ መያዝ

②- الـحـَذَرُ مِنَ الـبِـدَعِ وَالـمُبْتَدِعـِينَ،
ከቢደዓ እና የቢደዓ ሰወችን እራቅ

③- الـعِنَـايَة بـِدِرَاسَـةِ الـعَقِـيدَةِ الـصَّحِيْحـَةِ وَمـَا يُضَـادُّهَـا،
አቂዳን በመማር በማስተማር አቂዳን ወይም እምነትን የሚቃረኑ ነገሮች በመማር ሰወችን በማስተማር መታገዝ

④- الأَخـْذَ عَنِ الـعُلَمَـاءِ الـمُوْثُوقِينَ فِي عِلْـمِهِمْ وَفي عَـقِيدَتـِهِمْ،

እውቀትን አቂዳን ትክክለኛ ከሆኑ ኡለሞች በሀቅ ጎዳና ካሉ ኡለሞች ላይ መውሰድ ወይም መማር
⑤- الـحَذَر منْ دُعـاةِ الـسُّـوء الـذّيْن يُلـبِسُـونَ الْـحـَقّ بِالـبَاطِـلِ.
ወደ መጥፎ ከሚጣሩ ዳኢወች መጠንቀቅ ፣መራቅ እነዛ እውነታን በውሸት የሚያለባብሱ የሆኑ መጥፎ የሆኑ ኡለሞ
📖: الأجوبة المفيدة (س١١٢)

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik


ሱፍያኑ_ሰውሪይ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ :

«በዕድሜው የተጫወተ የመዝሪያው ወቅት ላይ ይጠፋል፣ የመዝሪያው ወቅት ላይ የጠፋ ደግሞ የማጨጃው ወቅት ላይ ይፀፀታል።»


‏﴿ وَمَا خَلَقْنَا السَّمَاء وَالأَرْضَ وَمَا بَيْنَهُمَا بَاطِلا ذَلِكَ ظَنُّ الَّذِينَ كَفَرُوا ‏﴾
https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik


أذكار الصباح ☕️

اللّهُـمَّ عالِـمَ الغَـيْبِ وَالشّـهادَةِ فاطِـرَ السّماواتِ وَالأرْضِ رَبَّ كـلِّ شَـيءٍ وَمَليـكَه ، أَشْهَـدُ أَنْ لا إِلـهَ إِلاّ أَنْت ، أَعـوذُ بِكَ مِن شَـرِّ نَفْسـي وَمِن شَـرِّ الشَّيْـطانِ وَشِرْكِهِ ، وَأَنْ أَقْتَـرِفَ عَلـى نَفْسـي سوءاً أَوْ أَجُـرَّهُ إِلـى مُسْـلِم.
(مره واحده).

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik


አባት ያላችሁ አላህ ረጅም እድሜ ይስጥላችሁ
ሁሉም ነገር ሚታወቀው ከኛ ሲርቅ ነውና ወላጅ ያላቹ ተጠቅሙባቸው አባት ለሌለን አላህ በጀነት ያገናኘን ያረብ

አባቴ አላህ ይዘንልህ ቀብርህ የጀነት ጨፌ ያድርግልህ ያረብ


زاحموا سَيِّئَاتِكُم بِالِاسْتِغْفَار .

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik


መሳቅ የተሻለ መድሀኒት ነው ነገር ግን ያለ ምክንያት የምትስቅ ከሆነ ሌላ መድሀኒት ያስፈልገሀል።

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik


{فَقُلْتُ اسْتَغْفِرُوا رَبَّكُمْ إِنَّهُ كَانَ غَفَّارًا}


አልከሶ ላይ የሚደረጉ የሽርክ አይነቶች  በጥቂቱ በስልጥኛ ቋንቋ !!



❶ አልከስዬን ካሌ ዩለ አቦተ = ዮክቤ ረክቤን ወዬ በጫረተ

❷ ዮልዬይ ወልዬ አልከስዬ = የረህመተይ በረ ክፈቱዬ

❸ ያልከሶ አባባዬ ትልብል ትልብል = ለማኒ ጣልኩሙኝ ውርውር ልልብል

❹ ያልከሶ አባብዬ ኑዲኒሞ = ኤወዲ እለፈዲ ብለኒሞ

❺ ብንጥረታም ውስጥ ኡፍታሙ ሙለ = አቤት አቤት ይላን የሙሪዲ በላ

❻ አልከስዬን ካሌ ባዬት አለ = የትቆጬ ህንጣብተ ያበቀለ

❼ ያልከሶይ ጎተረ ባባተረ = ለኘ ልዮቡነ ምን ሀተረ

➑ ምንን በባሉሞ ትመጦሞ = አቤት አቤት ህላን በላይ ሰቦ

➒ ያልከሶ አባባዬ ላአሏህ በሎ = ይንጭነናይ ደዊ እትደሎ

❿ ህንጥረት ህንጥሮ ለዙረነ = ተላላፊ ነቶ ለይነቺነ 

=============

ይህነው ሽርክ ማለት !! ቀላል ነገር  አድርገን ማያት የለብንም !! ከቤተሰቦቻችን ጀምረን አከባቢያችነን ጭምር ልናስጠንቅቅ ይገባል ባይነኝ !!
منقول
https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik


‏﴿ قُلِ اللَّهُمَّ مَالِكَ الْمُلْكِ تُؤْتِي الْمُلْكَ مَن تَشَاءُ ‏﴾


.              ꧁ ﷽ ꧂
.  ╔════❁════❁════╗
.  ሽርክ ማለት ምን ማለት ነው❓
.  ╚════❁════❁════╝
.     
🍃 هو جعل شريك لله تعلى في ربوبيته وإلهيته.

.       📚 ሽርክ ማለት ፦  በሶስቱ የተውሂድ ክፍሎች አጋር ማድረግ ነው።
በተለይ ደግሞ የተውሂድ አንኳር በሆነው በአላህ ብቸኛ ተመላኪነት ( ተውሂድ አል– ኡሉሂያ) አጋር ማድረግ ነው።

🍃 قول الله تعلى:
[ وعبدوٱ الله ولا تشركوا به،شَيٕاً].

[ አላህን ተገዙ በሱም ላይ አንዳችን እንዳታጋሩ(እንዳታሻርኩ)].

🍃 قول الله تعلى:
{ قل هو الله احد } [الإخلاص:١].

[ በል እርሱ አላህ አንድ ነው]

◾ መልእክተኞች በአጠቃላይ ወደዚሁ ተውሂድ  እንዲጣሩና ከሽርክ እንዳስጠነቅቁ  ነው የተላኩት .
  ➡   አላህም ይላል

🍃 قول الله تعلى፡
{ولقد بعثنا فى كل أمة رسولا ان ٱعبدوا الله وجتنبو اطغوت} [النحل:٣٦].

➖[ በእርግጥም ልከናል በሁሉም ኡመቶች (ህዝቦች) ላይ መልእክተኛን አላህን እንዲገዙ እንዲርቁም ከአላህ ውጭ ማምለክን (ጣጉት)].


. ╔══════ ❁✿❁ ═══════╗
.    የትልቁ ሽርክ አይነቶች ❓
. ╚══════ ❁✿❁ ═══════╝

🍃 الشرك ينقسم الا القسمين.

1⃣ الشرك الأصغر.
2⃣ الشرك الأكبر.


. 📚ሽርክ በዋናነት በሁለት ይከፈላል፦
.        1 ሽርከ አል– አስገር ።
.        2 ሽርከ አል– አክበር።
.       
የታላቁ ሽርክ አይነቶች– በአጭሩ–              ① ከአላህ ውጭ ለሆነ አካል መሳል            ② ከአላህ ውጭ ለሆነ አካል ማረድ          ③ ድግምት                                       ④ ጥንቆላ                                             ⑤ ከአላህ ውጭ ሌላን አካል መለመን                 ⑥ ከአላህ ውጭ ሌላን አካል መፍራት        ⑦ ከአላህ ውጭ ባለ አካል መመካት         ⑧ በውዴታ ማጋራት                               ⑨ በመታዘዝ ማጋራት                              ⑩  በኢስቲጋሳ ማጋራት                          ·                    الدال على الخير كفاعله

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik


"የትኛው ይበልጥ ይደንቅችዋል ?

የረሱልን ደም ድፋ ተብሎ ደሙን ጭልጥ አርጎ የጠጣውን ሶሀባ ፍቅር?

ወይስ ሀቢቡና ለቀናት ሲለዩት ያማረ ገፅታው እና ሰውነቱ ከስቶ የጠበቃቸው ሶሀባ ፍቅር ?

ነው ወይስ ሀቢቢ ከሞቱ በኋላ በህልማቸው አይቷቸው ከመጣ በኋላ አዛን ማውጣት ያቃተው ናፍቆት?

አሊያም ደሞ እንደሞቱ ሲያረዱት ህልፈታቸውን በጉልበት ላለማመን ሰይፍ እመዛለሁ ያሉት ጥልቅ ፍቅር?

በጦር አውድማ ከቤተሰቧ ህልፈት ባሻገር የነቢ መኖር ያስደሰታትስ ቢሆን ታሪኳ የወርቅ ብእር እንጂ ሌላ አያሻውም እንደው በመለክ እንጂ ሰው አይፅፈውም የተባለላት?

በአዛኙ ነብይ ላይ ሰላዋት እናውርድ

አላሁመሰሊ ወሰሊም ዓላ ሃቢቢና ሙሐመድ
https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik


በውስጥህ የምትይዛቸው እንደ ቂም፣ ቁጣና ጥላቻ ያሉ ስሜቶች አንተ ጠጥተሃቸው ሌላ ሰው እንዲሞት የምትጠብቅባቸው መርዞች ናቸው።


‏«ألا بذكرِ الله تطمئنُ القُلوب»

ድካም ፣ መረበሽ ፣ ሃሳብ መበታተን እና ጭንቀት ሲያጋጥመን አላህን ከማስታወስ የበለጠ ከነዚህ ስሜቶች ሊያወጣን የሚችል ምንም መፍትሄ የለም
ሁሉንም ነገር ትተን አላህን ማሳታወስ ስናዘወትር በአዲስ ስሜት አዲስ እና የተለየ እስትንፋስ ይኖረናል

20 last posts shown.