Forward from: ከ ቀደምቶች ንግግር🔊
•በነገራችን ላይ…እንደሰው ሁሉ ሰው ለኔ መልካም ያስባል ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው፡፡ ቅናት ምቀኝነት ካልታሰበ ሰው ጭምር ሊያጋጥም ይችላል። በቅርብም ሆነ በሩቅ ሰው ላይ የምቀኝነት መንፈስ ካያችሁ፣ አደራችሁን ዱዓ አድርጉለት ከልባችሁ፡፡
ለርሱም ለናንተም ሰላምና ጤና ሲባል ስኬታችሁን ደብቁ ለሓሲድ አትናገሩ፣ ዓላማችሁን በየቦታው አታውሩ፣ የትርፍ መጠናችሁን አትለፍልፉ፡፡ስለ መልካም የትዳራ አጋራችሁ አትዘባርቁ፣እሱን ለማብሸቅ ይመስለዋልና ምቀኛ ፊት ሳቅ ፈገግታ አታብዙ፡፡ ዐይን ያገኛችኋልና በየቀኑ ካላማረብን ለብሰን ካልወጣን አትበሉ፡፡
ምቀኛ በዙርያችን አለ ብለን የምንተዋቸው ሥራዎች፣ የማንለብሳቸው ልብሦች፣ የማንሄድባቸው ቦታዎች አሉ፡፡
ማድረጋችሁ የግድ ከሆነ ደግሞ ከሓሲድ ዐይን ለመዳን በቁል አዑዙዎች ታጠሩ፣ ኣየት አል-ኩርሲን አዘውትሩ፣ የጠዋት ማታ ዱዓዎችን አትርሱ፡፡
=t.me/AbuSufiyan_Albenan