አዲስ ሪፖርተር - NEWS


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic


🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !
=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !
🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addis_reporter_bot
#ADDIS ABABA, ETHIOPIA

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Statistics
Posts filter


ፌስቡክን የሚያስተዳድረው ሜታ ኩባንያ በርካታ ሰራተኞቹን ሊያሰናብት መሆኑ ተሰምቷል

የፌስቡክ፣ ዋትስአፕ እና ኢንስታግራም እናት ኩባንያ ሜታ በርከት ያሉ ሰራተኞቹን ከስራ ሊያሰናብት መሆኑ ተነግሯል።

ሜታ ኩባንያ ሰራተኞቹን ለማሰናበት ውጥን ቢይዝም በምትኩ ሮቦተችን ስራ የሚያለማምዱ ኢንጂነሮች በመቅጠር ተጠምዷል ነው የተባለው።

ከስራቸው የሚሰናበቱ ሰራተኞችን ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ ማሳወቅ ይጀመራል የተባለ ሲሆን፤ ከስራቸው የሚሰናበቱ ሰራኞችም አሜሪካን ጨምሮ በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ ናቸው ተብሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter


የቡና ባንክ ጥበቃ ሰራተኞች ጋፋት ላይ ክስ አቀረቡ

በቡና ባንክ ውስጥ የጥበቃ ሰራተኛ ሆነው ሲሰሩ የነበሩ ሰራተኞች፣ በአሰሪ ድርጅታቸው "ጋፋት" ላይ ከባድ ክስ አቀረቡ። ሰራተኞቹ፣ ድርጅቱ ለዓመታት ሲያቀርብላቸው የነበረውን የአገልግሎት ውል በመጣስ፣ ያለአመት እረፍት፣ የጡረታ እና ሌሎች መሰረታዊ ጥቅማጥቅሞች ሳይሰጥ እንደተዋቸው ይናገራሉ።

"ለዓመታት ስንሰራ ቆይተናል፣ አሁን ግን ምንም አይነት መብታችን ሳይጠበቅልን ተጥለናል" ሲሉ ሰራተኞቹ ለዜና_ኢትዮጵያ  በምሬት ተናግረዋል። "ይህ ድርጊት ፍጹም ኢፍትሐዊነት ነው። የብዙ ዓመታት ልፋታችን ዋጋ የሌለው ሆኗል።" ሲሉ ተናግረዋል

ሰራተኞቹ አክለውም፣ ጋፋት ድርጅት ምንም አይነት አስቀድሞ ማስጠንቀቂያ ሳይሰጥ እንደዘጋውና አሁን ባሉበት ሁኔታ ለከፍተኛ ችግር እንደተጋለጡ ገልጸዋል። "ቤተሰቦቻችንን እንዴት እንደምንመግብ አናውቅም። የወደፊት ህይወታችን አደጋ ላይ ነው" ሲሉ በምሬት  ተናግረዋል።

የቡና ባንክ ጥበቃ ሰራተኞች ጉዳዩን ወደሚመለከተው አካል ለማቅረብ እየተዘጋጁ ሲሆን፣ መንግስትና የሚመለከታቸው አካላት ለዚህ ጉዳይ ትኩረት እንዲሰጡና ፍትህ እንዲሰፍን ጠይቀዋል።

''ይህ ክስተት በኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ የግል ድርጅቶች ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች መብት ምን ያህል እየተጣሰ እንደሆነ በግልጽ የሚያሳይ ነው። መንግስትና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ለዚህ ጉዳይ ትኩረት በመስጠት ሰራተኞች መብታቸውን እንዲጠብቁና ፍትህ እንዲሰፍን ማድረግ አለባቸው ''ሲሉ አክለው ተናግረዋል

via:ዜና ETHIOPA

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter


መረጃ‼️

ጨፌ ኦሮሚያ በዛሬው ዕለት ሲያካሄደ በዋለው ስብሰባው ለ7 ሰዎች ሹመት ሰጠ። አቶ አዲሱ አረጋ እንደገና ወደ ኦሮሚያ ተመልሰዋል።

በምክትል ፕሬዝደንት ማዕረግ የማህበራዊ ጉዳይ ክላስተር አስተባባሪ የነበሩት አቶ አዲሱ አረጋ በጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ የውጭ ጉዳይ አማካሪ፣ ከዛም ወደ ብልጽግና ፓርቲ ሄደው የነበረ ሲሆን ዛሬ ደግሞ ዳግም ወደ ኦሮሚያ ተመልሰው አቶ አዲሱ አረጋ በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪ ሆነው ተሹመዋል።

ዛሬ ሹመት ያገኙት 7 ሰዎች፦

⚫ አቶ ከፋያለው ተፈራ - በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የጨፌ ኦሮሚያ ዋና ተጠሪ

⚫ አቶ አዲሱ አረጋ -በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪ

⚫ አቶ ሳዳት ነሻ - በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ

⚫ ፕሮፌሰር ነጻነት ወርቅነህ - የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ሃላፊ

⚫ አቶ ተስፋዬ ቱሉ - የኦሮሚያ ገቢዎች ቢሮ ሃላፊ

⚫ዶክተር ነመራ ገበየሁ - የኦሮሚያ ማዕድን ልማት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር

⚫ አቶ ፍሰሃ በላይነህ - የኦቢኤን (OBN) ዋና ዳይሬክተር

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter


ይነበብ‼️

አንዱ የ400 ብር የመብራት አገልግሎት ቻርጅ ለማድረግ መብራት ኋይል ሄዶ የገጠመው የሰርቪስና የታክስ ብዛት ይህንን ይመስላል።

ሰርቪስ ቻርጅ 15.65
የተቆጣጣሪ ክፍያ 1.95
የኢቢሲ ቴሌቭዠን 10
ቫት ዶሜስቲክ 336.32
ቫት ሰርቪስ ቻርጅ 2.35

በድምሩ ከ 400 ብር ላይ በርካታ ታክሶችና ቅንስናሾች 366. 27 ከፍሎ ለመብራት አገልግሎት ብር 33 ከ73 ቻርጅ ተደርጎለት ተመልሷል። (መረጃው ተያይዟል)

የጉድ አገር ገንፎ እያደር ይፋጃል ይሏችኋል ይሄ ነው። በቻርጅ ላይ ቻርጅ፣ በቫት ላይ ቫት፣ በታክስ ላይ ታክስ፣ በክፍያ ላይ ክፍያ! እንዲህ ያለ ነገር የየትኛው ሀገር ተመክሮ ይሆን ?

እንደኔ እንደኔ ግን ከዚህ ሁሉ ውጣ ውረድ በየወሩ መጨረሻ በመገናኛ ብዙሃን ጥሪ እየተደረገልን ቤታችን ሳንገባ አንድም ሳንቲም ሳናጎድል ደመወዛችንና ገቢያችንን ለወረዳ ፋይናንስ ብናስረክብ የሚሻል ይመስለኛል ?!

ማለቴ፣ እኛንም እናንተንም ከማሰብ፣ ከመጨነቅ ከውጣ ውረድና ከድካም ይገላግለናል። ደረሰኝ ምናምንስ ለምን ያስፈልጋል። "ኪሳችን ኪሳችሁ። ቤታችን ቤታችሁ እንዲያው አንድ አምሳልና አንድ አካል ሆነን የለ ¡¡¡"

ያለ ገቢ መኖር እንዴት እንደሚቻል በጾም በጸሎት እስኪገለጽልን ደረስ ደግሞ ደመወዛችንን ብቻ ሳይሆን በነካ እጃችሁ ቤተሰቦቻችንንም ጭምር መረከቡን እንዳትረሱት። ሲመቸንና ስራ በሌለን ጊዜ፣ በበዓልና በእረፍት ቀን እየመጣን እንጠይቃቸዋለን
የኢኮኖሚ ባለሙያ አቶ ሙሼ ሰሙ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter


በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት በአቶ ጌታቸው ረዳ በሚመራው ህወሓት እና በዶክተር ደብረጺዮን በሚመራው የህወሓት ቡድን መካከል የተፈጠረውን ልዩነት በውይይት ለመፍታት አሸማጋይ ሆኖ የተሰየመ ቡድን ከሁለቱ ቡድን ከፍተኛ አመራሮች ጋር ንግግር በማድረግ ሁለቱም ቡድኖች በአካል ተገናኝቸው በልዩነቶቻቸው ዙሪያ ለመወያየት ፈቃደኝነታቸውን የገለፁ ሲሆን በዛሬው ዕለት ፊት ለፊት ተገናኝተው ለውይይት ሊቀመጡ እንደሚችሉ ሰምተናል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter


የመቄዶንያ የገቢ ማሰባሰቢያ 101 ሚሊዮን ብር ደረሰ

በሚያስደንቅ ፍጥነት እየተከናወነ የሚገኘው የመቄዶንያ የገቢ ማሰባሰቢያ 101 ሚሊዮን ብር፣ በዜልና ካሻ-አኘ የገንዘብ ማስተላለፊያ 275,000 ዶላር፣ እንዲሁም በጎፈንድ ሚ ደግሞ 111, 003 ሺ  ዶላር በላይ የተሰበሰበ ሲሆን በመርሃ ግብሩ በርካታ ልብ የሚነኩ ስጦታዎች እየተደረጉ ነው።
Via dagu

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter


መረጃ ‼️

የኢትዮጵያ ማሪታይም ትሬኒንግ ኢንስትትዩት ተማሪዎች ትምህርቱን ተከታትለው ከጨረሱ በኋላ 36,000 ዶላር እየጠየቀ እንደሆነ ታውቋል።

መርከበኞችን አሰልጥኖ ማስቀጠር ከጀመረ ከአስር አመት በላይ የሆነው ተቋሙ በ Marine Engineering and Electrotechnical Officer አስተምሮ ወደ ስራ የሚያሰማራቸው ዜጎችን የሚጠየቀው የገንዘብ መጠን በጣም የተጋነነ እና ከሌሎች ሃገራት አንፃር ሲታይ በብዙ እጥፍ እንደሚበልጥ ታውቋል።

ለምሳሌ በተመሳሳይ ትምህርት የተማሩ ሰዎች በህንድ 5,000 ዶላር እንዲሁም በፊሊፒንስ 10,000 ዶላር ብቻ ይጠየቃሉ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter


እስከ 30,000 ብር የሚጠይቁት ህገወጥ የፍተሻ ጣቢያዎች ሊዘጉ ነዉ ተባለ

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የትራንስፖርት እንቅስቃሴን ለማቀላጠፍና የኢኮኖሚ እድገትን ለማሳደግ በሚደረገው እንቅስቃሴ በመላ አገሪቱ በርካታ ሕገ-ወጥ የፍተሻ ጣቢያዎች እንደሚዘጉ አስታውቋል።

ሚኒስትሩ ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) አንዳንድ ሲሉ የጠሯቸው ቀበሌዎችና ከተሞች ያልተፈቀዱ የፍተሻ ጣቢያዎችን በመክፈት ከ10 እስከ 30,000 ብር የሚደርስ ክፍያ ሲጠይቁ እንደነበር ገልጸዋል።

እነዚህ የፍተሻ ጣቢያዎች ብዙውን ጊዜ በአካባቢዎች መካከል በሚደረግ ፉክክር መንፈስ የሚቆሙ፣ አላስፈላጊና ለኢኮኖሚው ጎጂ እንደሆኑ ተመላክቷል።

ሚኒስትሩ እነዚህ የመንገድ መዝጊያዎች አላስፈላጊ ወጪዎችንና መዘግየቶችን ከማስከተላቸውም በላይ የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊ እድገት እንደሚያደናቅፉ አስረድተዋል።

በሁሉም መንገድ ላይ እውቅና የሌላቸው የፍተሻ ጣቢያዎች መኖራቸውን አምነው የተቀበሉት ሚኒስቴሩ የጉምሩክ ፣ የፀጥታ ፍተሻ ፣ የድንበር (ለገቢ/ወጪ) እና ዋና ዋና የጭነት ተርሚናል የፍተሻ ጣቢያዎች ( ኬላ) ብቻ የተፈቀዱ መሆናቸውን ግልጽ አድርገዋል ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter


ደብዛው ጠፍቶ የቆየው አነስተኛ አውሮፕላን ስብርባሪው ተገኘ።

ከቀናት በፊት በአሜሪካ አላስካ ግዛት 9 መንገደኞችን እና 1 አብራሪን ይዞ ሲጓዝ የነበረ አነስተኛ አውሮፕላን ደብዛው ጠፍቶ ከቆየ በኃላ በአየር እና ምድር በተደረገ አሰሳ ስብርባሪው ተገኝቷል።

በአደጋው በሕይወት የተረፈ ሰው የለም።

የ3 ሰዎች አስክሬን በነፍስ አድን ሰራተኞች ተገኝቷል።

ይህ አደጋ በአሜሪካ ከ1 ሳምንት ባነሰ ጊዜ የደረሰ 3ኛው የአቬዬይሽን አደጋ መሆኑን የቪኦኤ ዘገባ ያሳያል።

በአሜሪካ፣ ፔንሲልቫኒያ ግዛት፣ አንድ አነስተኛ የሕክምና ማጓጓዣ አገልግሎት የሚሰጥ ጄት በርካታ ሕንጻዎች በሚገኙበት ሰፈር ውስጥ ተከስክሶ በህይወት የተገኘ እንደሌለ ይታወቃል።

ከዚህ አደጋ በፊት ደግሞ በዋሽንግቶን ዲሲ 60 መንገደኞች እና 4 የበረራ ሰራተኞችን የያዘ የመንገደኞች አውሮፕላን 3 ሰዎች ከያዘ የጦር ሄሊኮፕተር ጋር ተላትሞ አንድም ሰው በህይወት አለመገኘቱ መገለጹ ይታወሳል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter


ባህር ሀይል⁉️

ትላንት አርብ በኢትዮጵያ የታዩ ሁለት ቪድዮዎች የአለምን ትኩረት ስበዋል።

አንድ ለጦርነት የተዘጋጀ የኢትዮጵያ የጦር መርከብ ትክክለኛ ቦታው ባልተገለጸ ቦታ ላይ በጦር መሳሪያ ታጭቆ ሲጓዝ የሚያሳይ ቪድዮ ተለቆ መነጋገሪያ ሆኗል።

ከዚህ ቪድዮ በኋላ አርብ አመሻሹን ደግሞ ሌላ አነስተኛ የውጊያ ጀልባ የኢትዮጵያ ባሕር ሃይል የሚል የተጻፈበት ቪድዮ ታይቷል። ከፍተኛ መነጋገሪያ የሆነው ግን ቀደም ብሎ የወጣው ቪድዮ ላይ የታየው የጦር መርከብ ነው።

የጦር መርከቡ የት ቦታ እንዳለም ሆነ ወዴት እያቀና እንዳለ ያልገለጸው ቪድዮ ላይ አንድ ኢትዮጵያዊ የባሕር ሃይል አባል መርከቡ ላይ ሆኖ መርከቡ የኢትዮጵያ መሆኑን የሚያሳዩ ምልክቶችን እና ለውጊያ የተዘጋጀ መሆኑን የሚገልጹ ምስሎች ሲቀርጽ ታይቷል።

ከቪድዮ ለመረዳት እንደተቻለው ከሆነ መርከቡ ግዙፍ ሲሆን በትንሹ በ ሶስት አቅጣጫ ለመተልኮስ የተዘጋጁ ተተኳሽ ሚሳኤሎችን ታጥቋል። የጦር መርከቡ እየሄደ ያለው ወዴት ነው የሚለው ግን የብዙዎች ጥያቄ ሆኗል።

የኢትዮጵያ ባህር ሃይል ዋና ማዘዣ ግንባታ እየተጠናቀቀ መሆኑን ሪፖርተር ከወራት በፊት መዘገቡ ይታወሳል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter


ዶናልድ ትራምፕ የአፍሪካ መሪዎች ሰው መሆናቸውን እጠራጠራለሁ አሉ⁉️

👉🏿 ከ50 ዓመታት የአህጉሪቷ የነጻነት ጉዞ በኋላ፣ ለህዝባችው አስፈላጊውን መሠረተ ልማት ካላሟላችው ሰው ነን ብላችው ታስባላችው?


👉🏿በወርቅ፣ በአልማዝ፣ በነዳጅ፣ በዩራኒየም፣ በብረት፣ በማዕድን፣ በብር፣ በማግኒዥየም፣ በነሐስ፣ በጋዝ የተፈጥሮ ሃብቶቻችው ላይ ተቀምጣችው፣ ህዝባችው በረሃብ፣ በትምህርት አለመዳረስ፣ በጤና አገልግሎት እጦት፣ ቢሞት፣ ሰው ነን ብላችው ታምናላችው?

👉🏿በስልጣን ላይ ቆይታችው፣የራሳችሁን  ዜጎች ለመግደል ከውጭ የጦር መሣሪያዎችን ስታስገቡ፣ ሰው ነን ብላችው ታስባላችው?

👉🏿የገዛ ዜጎቻችሁን እንደውሻ ስታንገላቱና ስትገድሉ፣ ማን ዜጎቻችሁን እንዲያከብር  ትጠብቃላችው?

👉🏿በራሳችው  አገር ላይ ቀማኛና ሌባ በመሆናችው ፣ የሃገራችሁን  ሀብቶች ሁሉ በመስረቅ፣ አብዛኞቹ ዜጋዎቻችው በስደትና በድህነት ውስጥ እንዲያልፉ ስታረጉ፣ የሰው ልጆ ነን ብላችው ታስባላችው?
ትራምፕ ይሄን የተናገሩት ሰሞኑን በዋሽንግተን ዋይት ሀውስ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ መሆኑን ተመልክቻለሁ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter

5.6k 0 44 16 175

'ብርጌድ ንሐመዱ' የተሰኘዉ የፕሬዝዳንት ኢሳያስ አገዛዝ ተቃዋሚ ቡድን አዲስአበባ ላይ ቢሮ ሊከፍት ነዉ ተባለ

በውጭ አገራት የተመሠረተው 'ብርጌድ ንሐመዱ' የተሠኘው የኤርትራ ተቃዋሚዎች ስብስብ ኢትዮጵያ ውስጥ በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ቢሮ ሊከፍት መኾኑን መስማቱን አፍሪካ ኢንተለጀንስ ዘግቧል።

'ብርጌድ ንሐመዱ' ወይም 'የሰማያዊ አብዮት ንቅናቄ' የተሰኘው የለውጥ ፈላጊ ወጣቶች ስብስብ፣ ከአንድ ሳምንት በፊት አዲስ አበባ ውስጥ ስብሰባ ማካሄዱን ዳጉ ጆርናል የጀርመን ድምፅ ራዲዮን ዘገባ ዋቢ በማድረግ መረጃ ማድረሱ ይታወሳል።

በዚኹ ስብሰባ ላይ ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የተወከሉ የንቅናቄው አባላት እንደተሳተፉ በወቅቱ ተዘግቦ ነበር።

ንቅናቄው በውጭ አገር የተመሠረተው ከኹለት ዓመት በፊት ሲኾን፣ በተለያዩ የምዕራቡ ዓለም አገራት የኤርትራ ኢምባሲዎችና የመንግሥት ደጋፊዎች ያካሄዷቸውን የባሕል ፌስቲቫሎች በማወክና በማስተጓጎል ይታወቃል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter


የዓለም ምግብ ፕሮግራም እርዳታ እንዲያቆም ታዘዘ‼️

የዓለም ምግብ ፕሮግራም፣ በአሜሪካ የገንዘብ ድጋፍ በተለያዩ አገራት የሚሠጣቸውን ዕርዳታዎች እንዲያቆም ትዕዛዝ እንደደረሰው ሮይተርስ ዘግቧል። ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ማርክ ሩቢዮ፣ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ያስተላለፉት የ90 ቀናት የዕርዳታ እገዳ ትዕዛዝ አሜሪካ በዩ ኤስ ኤ አይ ዲ በኩል በምትሠጣቸው አስቸኳይ የምግብ ዕርዳታዎችና የነፍስ አድን ዕርዳታዎች ላይ እንዳይተገበር መመሪያ አስተላልፈው ነበር። ኾኖም ለዓለም ምግብ ፕሮግራም የደረሰው የእገዳ ትዕዛዝ 507 ሺሕ ሜትሪክ ቶን የሚደርስ የምግብ አቅርቦትን እንደሚያስተጓጉል ድርጅቱ መናገሩን ዘገባው ጠቅሷል። ከዚህ ምግብ ውስጥ አብዛኛው በ23 አገራት መጋዘኖች እንደሚገኝና ከፊሉ ወደተለያዩ አገራት በመጓጓዝ ላይ መኾኑን ጠቅሶ ማብራሪያ እንደጠየቀም ዘገባው አመልክቷል። የዓለም ምግብ ፕሮግራም ኢትዮጵያ ውስጥ ዋነኛው የአስቸኳይ ሰብዓዊ ዕርዳታ አቅራቢ ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter


ሁለት ሦስተኛው የሰው ልጅ ከ 70 ዓመት በላይ በሆኑ ወንዶች ኃይል ሥር ነው - ቢልድ

በመላው ዓለም የፖለቲካ ሥልጣን በሽማግሌዎች እጅ እየጨመረ ነው፡:

አሜሪካ፣ ሩሲያ፣ ቻይና፣ ህንድ፣ ኢራን ሀገራት እንደምሳሌነት መሪዎቻቸው ከሰባ አመት በላይ ናቸው።

በምድር ላይ ካሉት በግምት 8 ቢሊዮን ሰዎች 5.4 ቢሊዮን ሰዎች ወይም 67.5% የሚሆኑት ህዝቦች የሚመሩት ከ70 አመት በላይ በሆኑ ወንዶች ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter


የጦሩ አዛዥ ተማረከ❗️

የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አዛዥን መያዟን ኬንያ ይፋ አደረገች፡፡

የኢትዮጵያ እና ኬንያ መንግስት ድንበር ላይ የጀመሩት ኦፕሬሽን የቀጠለ ሲሆን፤ የኬንያ ጸረ ሽብር ቢሮ ዛሬ ባወጣው መረጃ የአካባቢው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት መሪ የሆነውን ሳዳም ቡኬን በቁጥጥር ስር አውያለሁ ብሏል፡፡ መሪው ሳዳም ቡኬ በሰሜናዊ ኬንያ በመርሳቢት እና ኢሲዎላ አውራጃዎች የቡድኑ መሪ እንደሆነ የኬንያ ዜና ምንጮች ዘግበዋል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter


#ነዳጅ

የነዳጅ ምርቶች ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል ተብሏል።

የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።


➡ አንድ ሊትር ቤንዚን 101.47 ብር

➡ አንድ ሊትር ናፍጣ 98.98 ብር

➡ አንድ ሊትር ኬሮሲን 98.98 ብር

➡ የአውሮፕላን ነዳጅ 109.56 ብር

➡ አንድ ሊትር ከባድ ጥቁር ናፍጣ 105.97 ብር

➡ አንድ ሊትር ቀላል ጥቁር ናፍጣ 108.30 ብር

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter


🎁 አሸናፋዎቹ  ዛሬ ይታወቃሉ⁉️

ለጓደኞቻችሁ ሼር አርጉላቸው✅

⭐️500STAR ለ 5 እድለኛ ሰዎች, አሸናፊውን TELEGRAM RANDOM ይመርጣል  ለመሳተፍ 4 ቱን ቻናሎች የግድ መቀላቀል ይኖርባቹሀል። Share ስታደርጉ ደግሞ እድላችሁ ይሰፋል

🎁መልካም እድል 🙏

የኛ ቤተሰብ ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን 👍

ሞቅ ሞቅ አርጉት እንጂ👍🔥

መልካም እድል


Forward from: Dubai Furniture Ethiopia ዱባይ ፈርኒቸር ኢትዩጵያ🇪🇹
Розыгрыш 500 Telegram Stars, которые будут распределены среди 5 победителей
Participation terms:
  • All subscribers participate in the giveaway
  • You must be a subscriber of 5 channels
  • End of giveaway: 07.02.2025 22:20


በአሜሪካ አላስካ ግዛት ደብዛው የጠፋው አውሮፕላን

10 ሰዎችን የጫነ አውሮፕላን በአሜሪካ አላስካ ግዛት መጥፋቱ ተገለፀ።

የቤሪንግ አየር መንገድ ንብረት የሆነው ሴስና ካራቫን አውሮፕላን ከአሜሪካዋ አናላክሌት ወደ ኖም እያቀና ሳለ መጥፋቱ ነው የተገለፀው።

አውሮፕላኑ በጠፋበት ወቅት አብራሪውን ሳይጨምሮ 9 ሰዎችን ይዞ እንደነበረ ነው የተገለጸው።

የአየር መንገዱ ባለሙያዎች ከአብራሪው ጋር ለመጨረሻ ጊዜ ያደረጉት የመረጃ ልውውጥ አብራሪው የማረፊያ ቦታ እስኪስተካከል አየር ላይ ለመቆየት መወሰኑን ሲያሳውቅ ነው ተብሏል።

ይህም ትናንት ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ነበር።

እስከ አሁን የጠፋውን አውሮፕላን ለማግኘት በአየር እና በምድር የፍለጋ ቡድን ሥራ መጀመሩ ተገልጿል።

ቤሪንግ አየር መንገድ በአሜሪካዋ ምዕራብ አላስካ የሚገኙ 32 መንደሮችን ኖሜን ጨምሮ ከሶስት ዋና ማእከል ጋር የሚያገናኝ ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter


በሙቀት የተነሳ ከቅዳሜ ጀምሮ በጋምቤላ ክልል የመንግስት የሥራ ሰዓት ለውጥ ይደረጋል

በክልሉ የሙቀቱ መጨመር ለሥራ ምቹ ባለመሆኑ ከነገ የካቲት 1 ቀን 2017 ዓ.ም የሚጀምረው የሥራ ሰዓት ለውጥ ለ3 ወራት ይቆያል።

በዚህ መሰረትም ቀደም ሲል የመደበኛው የሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 1፡00 እስከ 6 ፡30 የነበረው ከ1፡00 እስከ 5፡30 ይሆናል።

እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 9፡00 እስከ 11፡30 የነበረው ከ10፡00 እስከ 12፡30 እንዲሆን የክልሉ አስተዳደር ወስኗል።

የሥራ ሰዓት ለውጡ በማጃንግ ዞን የመንገሺና ጎደሬ ወረዳዎችን እንደማይጨምር ተጠቁሟል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter

20 last posts shown.