➡ ጀነትና ጀሀነም
ቁርአን ስለ ሰማያዊ ሁነቶች የሰው ልጅ በሚገባው ቋንቋ እንዲህ እያለ ያስረዳል ።
« ከስሮቻቸው ወንዞች ይፈሱባቸዋል »
« በርሷም ( በጀነትም) የገቡት በወርቅና ሉል ጌጦች ያጌጣሉ ። ልብሶቻቸውም ሃር ናቸው »
የወይንና የማር ወንዞች በስሮቻቸው ይፈሳሉ ። በርሷም ዓይኖቻቸው በቅርፊቱ ያለ ሉል የመሰሉ ዓይን ያላቸው ሁሌም ወጣት የሆኑ ልጃገረዶች አሉ ። »
#የጀነትን እውነተኛ ገፅታ ማወቅ ከሰው እውቀት በላይ ነው ። አሏህም በሰው ልጆች ቋንቋ እንዲገባን አድርጎ አስረድቶናል ። ስለሆነም ፤ ስለ ጀነት የተነገረን ነገር በዚህ ምድር ካሉት ከየትኛውም ጋር እንደማይመሳሰል መታወቅ አለበት ።
#ወንዙ ፣ ማሩ ፣ ወተቱ ፣ እና ቆነጃጅቱ ልጃገረዶች ወዘተ እዚህ ምድር ካሉት ጋር አንድ አይነት አይደሉም ። ለዚህም አባባላችን ከቁርአን መረጃ አለን ፦
فَلَا تَعْلَمُ نَفْسٌ مَّا أُخْفِيَ لَهُم مِّن قُرَّةِ أَعْيُنٍ جَزَاءً بِمَا كَانُوا يَعْمَلُونَ
ይሠሩትም በነበሩት ለመመንዳት ከዓይኖች መርጊያ ለእነርሱ የተደበቀላቸውን (ጸጋ) ማንኛይቱም ነፍስ አታውቅም፡፡
(አስ_ሰጅዳህ 17)
#ተወዳጁ ነቢያችን ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰላም ሲናገሩ አሏህ እንዲህ ይላል ፦ « ለቅን ባሮቼ ዓይኖች ያላዯትን ፣ ጆሮ ያልሰማትን ፣ ልቦች ላይ ውልብ የማትል (ጀነት) አዘጋጅቻለሁ ። »
ይህም አስቀድመን ጀነት በሰው ልጆች ልትታሰብ እንኳን እንደማትችል የተነጋገርነው ይደግፍልናል ።
በዚህ ጉዳይ ላይ ሰፊ ትንታኔ የሰጡት የቁርአን ሙፈሲሮች ትንታኔዎቻቸውን በበቂ ማስረገጫ አላስደገፉም ። ስለመጪው ዓለም ስዕል ለመፍጠርና ከዚህ ዓለም ጋር ለማነፃፀር እምብዛም አልሞከሩም ። ጥረታቸው ልክ እንደ ስነ መለኮት ምሁራን ሁሉ የአሏህን ፍትሐዊነትና ባህሪያት ከሰው «ፍትሃዊነት» ጋር ማነፃፀር ነበር ።
በዚህም ምክንያት በንድፈ ሃሳብና በክርክሮች መረብ ተተብትበዋል ። ለነሱ በዚህ ጉዳይ ላይ የሰው ልጅ አዕምሮ ከድንበሩ አልፎ ማሰብ እንደማይችል ለማሳወቅ ከቁርአን አስተምህሮ ዝንፍ ያላሉትን ሰለፎች አቋም ቢይዙ ይሻላቸው ነበር ።
ከነዚህ ሰዎች ጉንጭ አልፋ ክርክሮች ውስጥ አንዱ ፣ ጀነት ውስጥ ያሉት ቆነጃጅትን ይመለከታል ። ጥያቄያቸው « ጀነት ውስጥ ካሉት ቆነጃጅት ጋር የሚኖረን ግንኙነት በዚህ ምድር ካሉት ጋር ያለ ዓይነት ነውን ?» የሚል ነው ።
የረሱት ግን በዚህ ምድር የትዳር ዓላማ ልጅ ማፍራትና ዘርን ማቆየት መሆኑን ነው ።በመጪው ዓለም ግን እነዚህ ዓላማዎች ስለሌሉ ጥያቄያቸው ትርጉም አልባ ይሆናል ። ቁርአን ውስጥ ያሉትን ነገሮች ሁሉ በጥልቅ አውቄ ካልተረዳሁ ከማለት ይልቅ ማመን ይበልጥ ምክንያታዊ ነው ።
ወደ #ጀነት …
ወደ #ጀነት መግባት በምኞትና በፍላጎት ብቻ የሚገኝ አይደለም ። በኢማንና በመታዘዝ እንጅ ። ቁርአን ስለዚህ ጉዳይ ሲገልፅ ፦
أَمْ حَسِبْتُمْ أَن تَدْخُلُوا الْجَنَّةَ وَلَمَّا يَعْلَمِ اللَّهُ الَّذِينَ جَاهَدُوا مِنكُمْ وَيَعْلَمَ الصَّابِرِينَ
በእውነቱ አላህ ከናንተ እነዚያን የታገሉትን ሳያውቅ (ሳይለይ) ታጋሾቹንም ሳያውቅ ገነትን ልትገቡ አሰባችሁን ??
(አል_ዒምራን 142)
لَّيْسَ بِأَمَانِيِّكُمْ وَلَا أَمَانِيِّ أَهْلِ الْكِتَابِ ۗ مَن يَعْمَلْ سُوءًا يُجْزَ بِهِ وَلَا يَجِدْ لَهُ مِن دُونِ اللَّهِ وَلِيًّا وَلَا نَصِيرًا
(ነገሩ) በምኞታችሁና በመጽሐፉ ሰዎች ምኞት አይደለም፡፡ መጥፎን የሚሠራ ሰው በእርሱ ይቀጣል፡፡ ለእርሱም ከአላህ ሌላ ጠባቂንም ረዳትንም አያገኝም፡፡
(አል_ኒሳእ 123)
ስለዚህ ፥ በምድረ_ጀነት ተቀባይነት የሚያገኘው ሰው በመልካም የሚያዝ ። ስለአሏህ የሰራ ፤ ጊዜውን ፣ ሀብቱን ፣ ኃይሉን ሁሉ ለአሏህ ብሎ እውነትን ለማስፋፋት የተጠቀመ ነው ። ይህ ቢያቅተው እንኳ ፣ ነፍሱን ከሚያቆሽሿት ስራዎች ታግሶ ያልፋቸዋል ።
ደህንነት ( ነጃ መውጣት) የሚረጋገጠው ሂሳብ ከተጠናቀቀ ፥ ሲራጥም በሰላም ከታለፈ በኋላ ነው ።
وَسِيقَ الَّذِينَ اتَّقَوْا رَبَّهُمْ إِلَى الْجَنَّةِ زُمَرًا ۖ حَتَّىٰ إِذَا جَاءُوهَا وَفُتِحَتْ أَبْوَابُهَا وَقَالَ لَهُمْ خَزَنَتُهَا سَلَامٌ عَلَيْكُمْ طِبْتُمْ فَادْخُلُوهَا خَالِدِينَ
እነዚያም ጌታቸውን የፈሩት የተከፋፈሉ ጭፍሮች ኾነው ወደ ገነት ይንነዳሉ፡፡ በመጧትም ጊዜ ደጃፎችዋ የተከፈቱ ሲኾኑ ዘበኞችዋም ለእነርሱ «ሰላም በናንተ ላይ ይኹን፡፡ ተዋባችሁ፡፡ ዘውታሪዎች ኾናችሁ ግቧት» በሏቸው ጊዜ (ይገቧታል)፡፡
وَقَالُوا الْحَمْدُ لِلَّهِ الَّذِي صَدَقَنَا وَعْدَهُ وَأَوْرَثَنَا الْأَرْضَ نَتَبَوَّأُ مِنَ الْجَنَّةِ حَيْثُ نَشَاءُ ۖ فَنِعْمَ أَجْرُ الْعَامِلِينَ
«ምስጋና ለአላህ ለዚያ ተስፋ ቃሉን ለሞላልን፡፡ የገነትን ምድር በምንሻው ስፍራ የምንሰፍር ስንኾን ላወረሰን ይገባው» ይላሉም፡፡ የሠሪዎችም ምንዳ ምን ያምር!
(አዝ_ዙመር 73➖74)
https://telegram.me/Bistima1