የፈረሱት ሰፈሮች ለጨረታ ቀረቡ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ፣ በአራዳ ክፍለ ከተማ ፒያሳ ለኮሪደር ልማት ሲል ያፈረሳቸውን ሠፈሮች ጨምሮ በ250 በላይ ቦታዎች ላይ የሊዝ ጨረታ ማውጣቱን ተሰምቷል።
የሊዝ ጨረታው የወጣባቸው ቦታዎች በአስር ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ናቸው። በፈረሰው ፒያሳ አካባቢ 2 ሺህ 179 ካሬ ሜትር ስፋት ካለው ቦታ ጀምሮ እስከ ዝቅተኛው 650 ካሬ ሜትር ድረስ የሚገኙ 22 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ ወጥቶባቸዋል።
አስተዳደሩ ለ22ቱም ቦታዎች ያቀረበው የሊዝ መነሻ ዋጋ በካሬ 2 ሺህ 213 ብር ከ25 ሳንቲም ነው። የአኹኑ የሊዝ ጨረታ፣ የከተማ አስተዳደሩ ባለፈው ዓመት መጨረሻ ካወጣው የሊዝ ጨረታ በኋላ ለኹለተኛ ጊዜ የወጣ ነው።
https://t.me/Ankuar_news
https://t.me/Ankuar_news
👆👆ለበለጠ መረጃ ይቀላቀላሉን👆👆