"ጠላትን የምታሳፍር እውነተኛው ጻድቅ ዮሴፍ ሆይ የሃይማኖት ጠላቶች በላያችን በድንፋታ በተነሱ ጊዜ ያቺ ረደኤትህ ረዳት ትሁነን" የማትፈርሰው ዓለት ቤተ ክርስቲያን
ቤተ ክርስቲያን የመሰረታት ውይም የቤተ ክርስቲያን መሰረቷና ዓለቷ ለስም አጠራሩ ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችን መዳኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው እርሱም በደሙ መሰረታት ስለዚህም መሰረቷም ጉለላቷም ጣራው ግድግዳዋም የክርስቶስ ደም ሆኖ ሳለ ቤተ ክርስቲያን የመክፈል እንቅሳቃሴዎች የእግዚአብሔርን መንግስት እንደመክፈል የእግዚአብሔርን መንግስት እንደመቃወም እንዲሁም የእግዚአብሔርን መንበር እንደመነቅነቅ ይቆጠራል!!!!
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀገር ናት ስንል ለፖለቲካ ፍጆታ እና በሰው ዘናድ ድጋፍ ያስግኝልናል በሚል ለአፍ ቃል ማሳመሪያ ብለን አጉል ብንራቀቅ አባቶቻችንን ብንሸነግል ምዕመኑን ብናሞኝ ጠባቂዋ መንፈስ ቅዱስ ነው እና ሰው ያላወቀውን ልብ የሸመቀውን የውስጡን የክፉ ምክረ ሃሳብ እግዚአብሔር አምላክ ገልጦ የክፋቱን ስራ በአደባባይ ያሰጣዋል::
አሁንም በዚህ ጊዜ ያየነው ይህንኑ ነው ይቺን ታላቅ ሀገር እንዲመራ እድል የገጥመው ሁሉ ማንኛውም አካል ቤተ ክርስቲያንን አማካሪው እና አስተማሪው አድረጎ በመውሰድ ሌሎች መሪዎች የወደቁበትን ሚስጥር በማወቅ የራሱን ጠንካራ መንግስታዊ አስተዳደር በመመስረት የተፈራ እና የተከበረ ታሪክ ይሰራ ነበር ብዬ አምናለው።
ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያኗ የሚመስለን ድንጋዩ ቆርቆሮ ምስማሩ ብሎኬቱ መስሎን እሱን ካፈረስን እሷ የለችም ብለን የምናምን የዘመኑ ጅሎች ካለን ይህ አሁን ከላይ የጠቀስኩትን ቁሳቁስ መስሏቸው ከግራኝ ጀምሮ እስከ ጉዲት ተሞክሮ ያልተሳካ የዘመናት ልምምድ ነው ።
አሁን እኛ ባለንበት ዘመንም ይህን ለማደረግ ብዙ እርቀት ለመሄድ ቢሞከርም አሁንም መሰረቷ የክርስቶስ ደም ነውና አልተቻለም አይቻልምም።
አለት ሲከፈል አየው ኪሚል ቅዠት ጀመሮ ተገንጣይን እና ህጋዊን እኩል እስከሚያይ አስተዳደር ድረስ ፈጦ የሚታል ጥላቻ ላይ ያደረሳትን ነገር ብናውቀው ለህሊናችንም ዕረፍት ነበር። መንግስት ቢቀያየር ከትኛውም የእምነት አካል ቢነግስ እንደ መንግስት ተቀብላና አክባራ እውቅና የምትሰጥን የእምነት ተቋም በዘር እና በቋንቋ መክሰስና መውቀስ ፍትሀዊ አይደለሽም ብሎ መኮነን ክርስቶስን ፍትሀዊ አይደለህም እንደማለት ነው። ማለትም ነው።
ምክንያቱም ይቺ እምነት ተወካይነቷ ወይም እንደራሴነቷ ለእግዚአብሔር ነውና። ከዘር ከጥላቻ ከቋንቋና ከሀሰት ጋር እንድትቆም ሰማያዊ ተልኮዋ አይፈቅድምና እንደው ሊባሏት ያሰቧትን አሞራ ጅግራ ነች ይሏታል በሚባለው በሀገራችን ቢህል ብንዘጋው ይቀላል።
ይቺ በዘመናት ውጣውረድ በከባድ ፈተና ወስጥ ሳትበገር አልፋ እዚህ የደረሰች ታላቅ ቤተ ክርስቲያን ዛሬም እንዳለፈው እንደወም በተሻል ችግሮቿን እንደምታልፍ እሙን ነው። ሌላው የሀገር መሰሶ ሲነካ ሁሉም መነካቱ የማይቀር ነው እና ሁላችንም ቤተ ዕምነቶች የምንጠብቃት የሁላችን ጉዳይ ልናደርጋት ይገባል በማለት መልዕክቴን አበቃለው።
ቤተ ክርስቲያኔ ዕውቀት የገበየውብሽ ጥበብን የታደልኩብሽ ምግባርንና ሰውመሆንን ብቻ የተማርኩብሽ ጉልላቴ ሁሌም አለው ከጎንሽ ዘብ ሆኜ ለክብርሽ ልጠብቅሽ የሰማይ ሀምሳል መንበር የእግዚአብሔር ሀገር በምድር ቀዳማዊት ሉላዊት አጸድ ቤተ መቅደስሽ ይከበር
#እንዲት ዕምነት
#እንዲት ጥምቀት
#እንዲት ሀይማኖት
#እንድ ሲኖዶስ
#እንድ መንበር
#እንድ ፓትሪያሪክ
ሎቱስባት
#ዳን_አድማሱ
#Dan_Admasu
YouTube:-
https://bit.ly/3ckOkCFTelegram:-
https://t.me/Dan_Admasu