EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic


Ethiopian Broadcasting Corporation (EBC)

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Statistics
Posts filter


የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክርስታሊና ጂኦርጂዬቫ የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኙ
***************************

የዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋም ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክርስታሊና ጂኦርጂዬቫ የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል።

ማኔጂንግ ዳይሬክተሯ ከገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ፣ ከብሔራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምህረቱ፣ ከፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) እና ከሌሎች የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር የአድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል።

ክርስታሊና ጂኦርጂዬቫ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው የሥራ ቆይታ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት፣ ቅድሚያ በሚሰጣቸው ፖሊሲዎች፣ በኢኮኖሚ ማሻሻያዎችና በግሉ ዘርፍ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዕድሎች ላይ ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የኢትዮጵያ የሥራ ጉብኝታቸውም አይኤምኤፍ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ልማት ለመደገፍ እና የፖሊሲ ምክክሮችን በማድረግ የማይበገር እና ዘላቂ ሀገራዊ ብልፅግናን ለማምጣት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑ ተመላክቷል።

ማኔጂንግ ዳይሬክተሯ በትላንትናው ዕለት ብሔራዊ ቤተ መንግሥትን እና ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና የክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከልንና ብርሃን የዓይነ ስውራን አዳሪ ትምህርት ቤትን መጎብኘታቸው ይታወቃል፡፡


ሐኪሞች የአሳማ ኩላሊትን በመውሰድ ለአንድ ግለሰብ የተሳካ የኩላሊት ንቅለ ተከላ አከናወኑ
********************************

በማሳቹሴትስ አጠቃላይ ሆስፒታል የሚገኝ የሐኪሞች ቡድን ፤ በላቦራቶሪ የዘረመል ማስተካከያ የተደረገለት የአሳማ ኩላሊትን በመጠቀም ቲም አንድሪውስ ለተባለ ግለሰብ የተሳካ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማድረጉ ተነግሯል።

ለ66 ዓመቱ ቲም አንድሪውስ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማድረግ የሕይወት እና የሞት ጉዳይ ነበር። እናም በሐኪሞቹ የቀረበለትን የአሳማ ኩላሊት ንቅለ ተከላ ጥያቄ ለመቀበል አላመነታም።

ምክንያቱም አንድሪውስ መጨረሻ ደረጃ በደረሰው የኩላሊት በሽታ ምክንያት ለሁለት ዓመታት ያህል በዳያሊሲስ ላይ ቆይቷል።

አዲስ ኩላሊት ለማግኘት ስሙ በመጠባበቂያ ዝርዝር ውስጥ ቢሰፍርም ፤ የደም ዓይነቱ ለጋሽ አካል ለማግኘት አስቸጋሪ አድርጎበት ቆይቷል።

አንድ ኩላሊት ለመተካት በአማካይ ከሦስት እስከ አምስት ዓመታት ይወስዳል ፤ ነገር ግን ጥናቶች እንደሚያሳዩት የደም ዓይነታቸው “O” የሆኑ ሰዎች ኩላሊት ለማግኘት እስከ 10 ዓመታት ሊጠብቁ እንደሚችሉ ጥናቶች ያመላክታሉ።
https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0vL7y2isbJsxp12RRKjhY5mVCfaN2x97EGCxvBvWH1qq4x7jGMqEfSn2fASBWedwrl?cft[0]=AZWxEzqrEzBABEvRz6URRqztKF6GU2Fs6rviXF-rI-DRdI7qLygxWLwTqkt2-zU-RwW8xC2IIyTzuoWXi2-tayqeDeQob-CQv7rIu9udNDm2w3BARKOUdJ0OzP7pZrapUqv-uAwcqMIhTsQMx0i-O-nNVvYj644dG7T6QQY5XZgTPeY2jKHPpi8AYeOouWQm724&tn=%2CO%2CP-R


ሰላምን ለማፅናት ከውስጥ እና ከውጭ ያጋጠሙ ጫናዎችን ከሕዝቡ ጋር ማሸነፍ ተችሏል - አቶ ሽመልስ አብዲሳ
********************

ሰላምን ለማፅናት ከውስጥ እና ከውጭ ያጋጠሙ ጫናዎችን ከሕዝቡ ጋር ማሸነፍ ተችሏል ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ተናግረዋል።

ጨፌ ኦሮሚያ 4ኛ ዓመት 6ኛ የሥራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ጉባኤውን በአዳማ ጨፌ አዳራሽ እያካሄደ ይገኛል።

ርዕሰ መሥተዳድሩ የክልሉን የ6 ወራት የሥራ ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ሪፖርት ለጨፌው አቅርበዋል።

ባቀረቡት ሪፖርትም ሰላምን ለማፅናት ከውስጥ እና ከውጭ ያጋጠሙ ጫናዎችን ከሕዝቡ ጋር ማሸነፍ መቻሉን ገልጸው፣ አስፈላጊውን መሥዕዋትነት ከፍለን ሕዝቡን ወደሚፈልገው ሰላም እናሸጋግራለን ብለዋል።

በክልሉ የተለያዩ አከባቢዎች መሳሪያ ታጥቀው ለሚንቀሳቀሱ ኃይሎች በተደረገው የሰላም ጥሪም ከኦሮሞ ነፃነት ግንባር አባላት እና አመራሮች ጋር የሰላም ስምምነት መፈረሙ በ6 ወራቱ የተገኘ ውጤት መሆኑን ጠቅሰዋል።

ሕዝቡ ከዚህ በፊት ቅሬታ የሚያነሣበትን የአገልግሎት አሰጣጥ ዘርፉን ለማሻሻል እና ጥራት ያለው እና የተደራጀ አገልግሎት ለመስጠት የሪፎርም ሥራ በመሥራት የቀበሌ አረጃጀቶች ሥርዓት ተዘርግቶ እየተሠራበት መሆኑንም ነው አቶ ሽመልስ አብዲሳ የገለጹ።

በሐምራዊት ብርሀኑ


አትሌት ያለምዘርፍ የኋላው የዱባይ ግማሽ ማራቶን አሸናፊ ሆነች
****************

በዱባይ በተካሄደው የግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ያለምዘርፍ የኋላው አሸናፊ ሆናለች።

አትሌቷ 1 ስዓት ከ7 ደቂቃ ከ9 ሴኮንድ በመግባት ውድድሩን ማሸነፏን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡


በኮሪደር ልማት ተከታታይ የምስል አቅርቦታችን ሰባተኛው አማራ ክልል ነው።

በአሁኑ ወቅት የኮሪደር ልማት በአማራ ክልል ሰባት ከተሞች በመስፋፋት ላይ ይገኛል፡፡

የኮሪደር ልማት በከተሞቹ የራስ ዐቅም፣ ከሕዝብ ተሳትፎ፣ ከፌደራልና ከልዩ ልዩ ድጋፎች በሚገኝ ዐቅም እየተተገበረ ነው። በባሕር ዳር፣ ጎንደር፣ ደሴ፣ ኮምቦልቻ፣ ደብረ ብርሃን፣ ደብረ ማርቆስ እና ወልድያ ከተሞች ተጀምሮ 32.23 ኪ.ሜ መንገድ 27.04 ሄ/ር አረንጓዴና ፓርክ ልማት፣ 3.7 ሄ/ር የሕዝብ አደባባይ፣ 25 ኪ.ሜ የመንገድ ዳር መብራትና ሕንፃ የማስዋብ ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛል፡፡

የኮሪደር ልማቱ ከተለመደዉ የፕሮጀክት አፈጻጸም በተለየ ሁኔታ በተለያዩ ምእራፎች ተከፋፍሎ በአጭር ጊዜ ጥራቱን ጠብቆ እየተተገበረ ነው። ጎንደር፣ ኮምቦልቻና ባሕርዳር ከተሞች የመጀመሪያ ምእራፍ በማገባደድ ወደ ሁለተኛ ምእራፍ ሥራዎች በመሸጋገር ላይ ናቸዉ፡፡

በዚህ የኮሪደር ልማት እንደ ባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ባሉ ከተሞች ግራ እና ቀኝ ሰፋፊ የእግረኛ መንገዶች፣ የብስክሌት መንገድ፣ ፐብሊክ-ፕላዛ (ማረፊያና መዝናኛ)፣ የመጸዳጃ ቤቶችና ዘመናዊ ካፍቴሪያዎች እየተገነቡ ነው።

በግራ እና ቀኝ ከ5 ሜትር በላይ ስፋት ያለዉ አረንጓዴ ልማት ተከናውኗል። የሐይቅ ዳርቻውን ለሕዝብ የመክፈት ሥራ ተሠርቷል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት


የጨፌ ኦሮሚያ መደበኛ ጉባኤ እየተካሄደ ነው
*******************

የጨፌ ኦሮሚያ 4ኛ ዓመት 6ኛ የሥራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ጉባኤ በአዳማ ጨፌ አዳራሽ መካሄድ ጀምሯል፡፡

በጉባኤው ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳ፣ የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱራህማንና በየደረጃው የሚገኙ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የጨፌው አባላት ተሰይመዋል።

የጨፌ ኦሮሚያ መደበኛ ጉባኤ በክልሉ በኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ዘርፎች የተገኙ ስኬቶችን ማስቀጠል በሚያስችሉ አጀንዳዎች ላይ መክሮ ተግዳሮቶችን መፍታት የሚያስችሉ አቅጣጫዎችን እንደሚያስቀምጥ ይጠበቃል፡፡

ጨፌው የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ውሳኔዎችና የተለያዩ ሹመቶችን መርምሮ ያጸድቃል ተብሎም ይጠበቃል።

በሀምራዊት ብርሀኑ







9 last posts shown.