#ኢስራእ_እና_ሚዕራጅ
ክፍል 4⃣
🔘በደንብ ልናውቅ የሚገባው #ነብዩ_ሙሐመድ_ﷺ ወደ ሰባቱ ሰማያት ያደረጉት ጉዞ በጭራሽ እንዲህ የሚልን “የአሏህን መኖር ወደ ሚጠናቀቅበት ቦታ መድረስን ነው”የሚልን #በጭራሽ አልተፈለገበትም። ይልቁንስ እንዲህ ብሎ ያመነ ሰው የካዳ [የከፈር] ይሆናል የነብዩ ﷺ የጉዞው አላማም ይህ አልነበረምና።
#የጉዞው_አላማ ነብዩ ሙሐመድ ﷺ የላይኛውን ዓለም ተዓምራት በማሳየት ለማላቅ [ ለማክበር]ነው።
🔘 #ነብዩ_ሙሐመድ_ﷺ ጅብሪልን ለሁለተኛ ግዜ በትክክለኛ አፈጣጠሩ በሲደረተል ሙንታሀ አይተውታል በዚህ ሰዐትም ነቢዩ ﷺ እራሳቸውን አልሳቱም ነበር።በቁርአንም እንደተገለጸው
[ولقد رءاه نزلة أخرى عند سدرة المنتهى]
#ትርጉሙ “በእርግጥ ተመለከተው ለሁለተኛ ጊዜ ሲድረቱል ሙንተሀ ዘንድ”(የነጅም ምዕራፍ 14)::
ስለዚህ👆የቁርአን አንቀፅ #ሰይዲቲ_ዓኢሻ እንዲህ አሉ“ ከዚች ኡማ ስለዚህ አንቀጽ ማለትም (ከማንጋ እንደተገናኙ) የመጀመሪያዋ ጠያቂ እኔ ነኝ #ነቢዩም " ጂብሪል ዐለይሂ ሰላም ነው። " ብለው መለሱልኝ አለች ። [ ሙስሊም] ዘግበውታል።
🔘 መላኢካው ጂብሪል #ለነቢዩ_ﷺካለው ፍቅር እና ናፍቆት እንዲሁም ደስታ ወደ ነቢዩ ﷺ ተጠጋ። በመካከላቸውም #ሁለት_ክንድ ወይንም ከዛም ያነሰ በሆነ እርቀት ቀርባቸው::
እዚህ ላይ እንደዚህ ብሎ “አሏህ ሱብሐነሁ ወተዓላ ከነቢያችን ጋር ተቀራረበ”ብሎ ማመን ጨርሶ የማይፈቀድ ሲሆን የተጥራራው ጌታችን እንዳለው
ثم دنا فتدلى ﻓﻜﺎﻥ ﻗﺎﺏ ﻗﻮﺳﻴﻦ ﺃﻭ ﺃﺩﻧﻰ ”
በዚህ የቁርአን አንቀጽ ላይ የተጠቀሰው «የሁለት ክንድ ወይንም ከዛ ባነስ እርቀት ተቀራረቡ» የሚለው የተፈለገበት #ጂብሪል ዐለይሂ ሰላምን ነው ።
🔘እንዲሁም አንዳንድ ሰዎች #እንደሚዋሹት አይደለም እንዲህ ይላሉ«አሏህ በዛቱ ከሙሐመድ ጋር ተቀራረበ በመካከላቸውም ያለው እርቀት በሁለት ቅንድቦች መካከል እንዳለው እርቀት ሆነ ወይም ሁለት ክንድ ሆነ» ይላሉ ይህ አሏህን ከፍጥረታት ጋር ማመሳሰል ነው::እንዲሁም ለአሏህ ቦታን ማስጠጋት ነው ምክንያቱም እርቀትን ማስጠጋት ያው ቦታን ማስጠጋት ስለሆነ።አሏህ ደግሞ ያለ ቦታ ያለ ነው::
🔘ከዛም መልዕክተኛው ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም #ከሲድረተል_ሙንተሀ በኋላ ከጂብሪል ጋር የተለያዩ ሲሆን መላኢካዎች ከለውሁል መህፉዝ ላይ ወስደው በሚፅፉ ጊዜ የቀለማቸው ድምፅ እስከሚሰማበት ቦታ ድረስ ደርሰዋል። #እዛም ቦታ ላይ ሁነው ያለ ድምጽ ያለ ፊደል ያለ ቋንቋ እንዲሁም የዓለማትን ንግግር በጭራሽ የማይመስለውን የአሏህን ንግግር የሰሙ ሲሆን ከዛም #ነብዩ ሙሐመድ ﷺ ከዚህ ከአሏህ ንግገር #የ50_ሶላቶችን ግዴታነት ተረድተዋል።
🔘 #የተበላሹ የሆኑ መፅሐፎች ውስጥ እንደሚገኝው ይህ ቦታ ማለትም ከሲድረተል ሙንተሀ በላይ ያለው ቦታ የአሏህ መኖር የሚጠናቀቅበት ቦታ አይደለም ምክንያቱም አሏህ ያለ ቦታ ያለ ነውና።
.
.
.
#ክፍል 5⃣ ይቀጥላል .......