አንድ እለት ብስት አየሺኝ ፦
አንቺ የሌለሽ ጊዜ የታመንኩት እምነት ፤ የወደድኩሽ መውደድ የአንድ ቀን ብልግናዬን ቸከቸከው ፤ አንደበቴን ለጎመው !
እስከዛሬ ኖሬ የነገርኩሽን እውነት አከሸፈው፦
አንድ እለት እምነቴን ብበላ ስህተቴ ጮሆ ተጣራ ።ከዚህ ኋላ ምን ብዬ አንቺ ፊት አወራለሁ ?
አንድ ስህተት ..!!
ከዚህ በፊት የሆንኩትን እውነት ሸፈነው ፣ ከዚህ በኋላ ለእኔ ያለሽን ምልከታ ቀየረው
ስህተቴ የነገርኩሽን ፣ ያልኩሽን ፣ ያሳየሁሽን ሃቅ ዳመጠው !
አንድ ስህተት ኑሮዬን አጠየፈው ምልከታሽን አዛነፈው
ምልጃ መላክ አሳነኝ ።
ፀፀት ራሴን እንድጠላው ተጫነኝ ፤ ስህተቴ እንድጠይኝ ገፋሽ ፤ የሆነውን ያወቁ ሁሉ ተጠየፉኝ
ቆይ ፦
ህሊና እንዳለው በዳይ አይነት መሄጃ አልባ ስደተኛ የት ይገኛል !?
ግን ፦
ይሉኝታ ቢስ ሆኜ እንጂ አንዴ ብስት ይባላል !!!