አባቴ ሁሉ ነገርን መጋፈጥ ይሰብራል ይላል ።
...ጀግና ሁኔታን የሚረዳ ነውም ይላል ።
እኔ የምጋፈጠው ለማሸነፍ ጀግናም ለመሆን አይደለም ሲደርሱብኝ ነበር።
አፈግፍጌ አውቃለሁ።
ያፈገፈኩኝ ግዜ የሚሰማኝ ስሜት መጥፎ ነው።
አባቴ "የማያፈገፍግ ታጋይ በቶሎ ይሞታል" እያለ የውትድርና ገጠመኙን ያጣቅስልኛል።
በሕይወቱ ምድር ላይ እንደኔ የሚጨነቅበት ጉዳይ ያለ አይመስለኝም...
"እሱ ማስረዳት አይችልም... በዛ ላይ ያፈጣል ....ችግር የሚፈታው አንገት ለአንገት በመተናነቅ ይመስለዋል" ይላል ስለ እኔ ሲናገር...
"አንዱ ይገለዋል አጉል ቦታ ይመቱታል የሰው ሰው እጁ ላይ ይጠፋል" ሲል ይሰጋል።
"እኔ በሕይወት የኖርኩት እጅ ሰጥቼ ነው...ይሄው ከዛ በኃላ ያገኘሁት መዓረግ እና ደስታ ይቆጠራል ...?? "
አባቴ ትኩረቱ ስለሆንኩ መሰለኝ...
ልጁ ስለሆንኩ መሰለኝ ...
ስላሳደገኝ መሰለኝ ...
ስለሚያስብልኝ መሰለኝ ...
ከኔ በተሻለ እኔን ያውቀኛል።
ስለእኔ ገምቶ የተሳሳተበት ግዜ አላስታውስም...
"በጠበል አልወጣ ያለ ጂኒ አለበት..." ይላል።
የሆነ ቀን ተሳካልኝ ልጄ ልብ ገዛልኝ ስለቴ ሰመረልኝ ብሎ በመሃበርተኛው ፊት ተናዞ ስለቱን እንዳስገባ የመሃበርተኛው ልጅ አዲሱ ነገረኝ...
ስለት ካስገባበት ቀን ጀምሮ ሳሰላስል ልብ ገዛ እንዳለው አይነት ሰው ሆኛለሁ ።
ደርሰውብኝ ያለፍኳቸው ቀምተውኝ የተውኳቸው ትተውኝ ያለቀስኩበት ሥፍራ ብዙ ነው ።
ምን ብሎ ተስሎ ይሆን ስለቱ የሰመረው...??
ምን አለ አሁን ትልቅ ሕልም እና ሕልሙን መተግበርያ ጥንካሬ ስጠው ብሎ ቢሳልልኝ...
(በአድኃኖም ምትኩ)
(ወግ ብቻ)