የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞችን ረቂቅ አዋጅ - የብቃት ምዘና
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞችን ረቂቅ አዋጅ ትናንት ምሽት በሦስት ተቃውሞና በአራት ድምጸ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል፡፡
አዋጁ የሠራተኞችን የብሄር ሥብጥር፣ ብዝሃነትንና አካታችነትን ያገናዘበና ብቃት ያለው የመንግሥት አገልግሎትና አስተዳደር ሥርዓት ለመገንባት ያለመ እንደኾነ ተገልጧል።
በአዋጁ ውስጥ የተጠቀሰው 'የብሄር ስብጥር' የሚለው ቃል፣ የአናሳ ብሄረሰቦች ተወላጆች በፌደራል ተቋማት የቅጥር ዕድል እንዲያገኙ ማስቻል ዓላማው ያደረገ ነው ተብሏል።
አዋጁ የደመወዝ ጭማሪ፣ እርከን፣ ክፍያ፣ ጥቅማጥቅም፣ ማትጊያ፣ የማበረታቻ ሥርዓት፣ የብቃት ምዘናና የሥራ ሥምሪትን ያካተተ እንደኾነ ተጠቅሷል።
ከፍተኛ ክርክር የተደረገበት ይህ ረቂቅ አዋጅ የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1353/2017 ሆኖ በ3 ተቃውሞ በአራት ድምፀ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል፡፡ #Wazema
@Ethiopian_Digital_Library