አሜሪካዊቷ ወጣት ማንበብና መፃፍ ሳልችል ከ12ኛ ክፍል ብቁ ነሽ ብሎ አስመርቆኛል በሚል ትምህርት ቤቷን ከሰሰች
የ19 ዓመቷ የኮነቲከት ወጣት በመሠረቱ መሃይም እንደሆንኩኝ እየታወቀ “በክብር” እንድመረቅ በመፍቀዱ ያስተናራትን የሕዝብ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ ክስ መስርታለች።ባለፈው ሰኔ፣ አሌይሻ ኦርቲዝ ከሃርትፎርድ የህዝብ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በክብር ተመርቃ የኮሌጅ ስኮላርሺፕ አግኝታለች።
አሁን ላይ ግን የቀድሞ ትምህርት ቤቷን በቸልተኝነት ያለኝን እውቀት ሳይረዳ በማስመረቁ ለስሜታዊ ጭንቀት ተዳርጌያለው ስትል ክስ መስርታለች ነው። የ19 ዓመቷ ወጣት እርሳስ በእጇ መያዝ እንደማትችል እና የማንበብ ችሎታዋ ከአንደኛ ክፍል ተማሪ ጋር እኩል እንደሆነ በመግለጽ የህዝብ ትምህርት ተቋሙን ትምህርቷን ችላ በማለቱ እንደሆነ የክሳ ዝርዝር ያሳያል። በፖርቶ ሪኮ የተወለደችው አሌይሻ ገና በለጋ ዕድሜዋ የመማር ችግር እንዳለባት አሳይታለች።
በ5 ዓመቷ ወደ አሜሪካ ከሄደች በኋላ ትምህርቷን ቀጠለች። ትምህርት ቤቷን እና በጉዳይዋ ላይ የተሾመው ልዩ አስተማሪ ለምረቃ አንድ ወር ሲቀረኝ እንኳን ብዙም እርዳታ እንዳልሰጧት ትናገራለች፣ አሌሻ ኦርቲዝ ማንበብና መፃፍ ሳትችል እንዴት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን በክብር ልትመረቅ ቻለች የሚለው ግን አነጋጋሪ ሆኗል። በዚህም ሳያበቃ የኮነቲከት ዩኒቨርሲቲ ስኮላርሺፕ አግኝታለች።
የስማርት ስልክ አፕሊኬሽኖችን ተጠቅማ ጽሁፍ ወደ ንግግር እና ንግግር ወደ ጽሑፍ በመተርጎም የኮሌጁን ማመልከቻ እንኳን ለመሙላትና ለመፃፍ ተጠቅማለች። የኮሌጅ ተማሪ መሆን ግን ፍጹም ከዚህ የተለየ ሁኔታ ነበር። አሌሻ እየተቸገረች መሆኗን አምና በየካቲት ወር መጀመሪያ ላይ ትምህርት መከታተል እንዳቆመች ተናግራለች። ለአእምሮ ጤና ህክምና እረፍት መውሰድ ያቋረጠች ሲሆን በቅርቡ ወደ ክፍል እንደምትመለስ ተስፋ አለኝ ትላለች።
አሌሻ የቀድሞ ትምህርት ቤቷን የከሰሰችው በደረሰባት ችግር የትምህርት ቤቱ አስተዳደር እንዲጠየቁ ስለፈለገች ነው። “እነሱ የሚያደርጉትን አያውቁም እንዲሁም ግድ የላቸውም” በማለት ሌሎች ወጣቶች ትምህርታቸውን እንዳይሰረቁ ክሱ እንደሚረዳቸው ተስፋ አድርጋለች።
NB.If it's in our country what do you think family🤔
✨ Share with your friends
@Freshman_Remedial_Exams