የሶማሊያ ጦር ባካሄደው የአየር ጥቃት ከፍተኛ የአልሻባብ አዛዥ ተገደለ
ዩሱፍ ዴግናስ በመካከለኛው ሸበሌ ክልል በኤል-ባድ አቅራቢያ እንደተገደለ ተገልጿል። በአካባቢው በመንግሥት ኃይሎች እና ታጣቂዎች መካከል ለቀናት የቆየ ከፍተኛ ግጭት ሲካሄድ ነበር ተበሏል። የመንግሥት ሚዲያዎች እንደዘገቡት ዴግናስ በመካከለኛው ሸበሌ የአልሻባብ* ዘመቻዎችን ያቀነባብር ነበር። የአዛዡ ግድያ ቡድኑ በክልሉ ውስጥ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ እንደሚያሰናክል ተነግሯል፡፡
የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐሙድ በአካባቢ ሚሊሻዎች ከሚታገዘው ብሄራዊ ጦር እና ከአፍሪካ ሕብረት ኃይሎች ጋር በመሆን በቅርቡ በአልሻባብ ላይ “መጠነ ሰፊ ጦርነት” ለማወጅ ቃል መግባታቸው ይታወሳል።
@Ewun_Mereja