Posts filter


የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በቀጣይ በሚያካሔደው የአመራር ምርጫ ሕዝበ ሙስሊሙ በንቃት እንዲሳተፍ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ጥሪ አቀረበ

ጠቅላይ ምክር ቤቱ ይህን ጥሪ ያቀረበው በዛሬው ዕለት ካከናወነው ሦስተኛ ዓመት አንደኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ በኋላ ባወጣው የአቋም መግለጫ ነው።

ዛሬ ቅዳሜ ጥር 24/2017 ባካሔደው አስቸኳይ ስብሰባው በገለልተኛ የባለሙያዎች ቡድን ተዘጋጅቷል ያለውን የምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያና የምርጫ ማስፈፀሚያ መመሪያ ሠነድን መርምሮ በሙሉ ድምጽ ማጽደቁንም አሳውቋል።


የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት በመንግስት ስር ሆኖ እንደገና ሊደራጅ መሆኑ ተሰማ

ላለፉት አስርት ዓመታት ከመንግስት ቁጥጥር ውጪ ሆኖ ሲሰራ የቆየው ዩኤስኤይድ ነጻ ዓለም አቀፍ የረድኤት ድርጅት ነበር። የአሜሪካ መንግስት ለዩኤስኤይድ በዓመት ከ70 ቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ እንደሚያደርግ ይታመናል።




''እሁድ ጀምሮ በተካሄደው ውጊያ ቢያንስ 700 ሰዎች ተገድለዋል'' ተመድ

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጦርነቱ ከተቀሰቀሰበት ባለፈው እሁድ ጀምሮ በተካሄደው ውጊያ ቢያንስ 700 ሰዎች መገደላቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ።

ጦርነቱ በምስራቃዊ የአገሪቱ ክፍል በምትገኘው ትልቋ ከተማ ጎማ ተፋፍሟል።

የመንግሥታቱ ድርጅት ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች እንደተናገሩት በሩዋንዳ የሚደገፉት የኤም23 አማጺያን የሰሜን ኪቩ ግዛት መዲና የሆነችውን ጎማን ለመቆጣጠር በተደረገው ፍልሚያ ከተገደሉት በተጨማሪ 2 ሺህ 800 ሰዎች ቆስለዋል።

ጎማን የተቆጠጠሩት አማጽያኑ ወደ ደቡባዊ ኪቩ መዲና ቡካቩ እየገሰገሱ መሆኑ ተነግሯል።


ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትላንትና ፖለቲካ ሲያንቦራጭቁ የነበሩ ሰዎች ለግጭቶች ተጠያቂ ናቸው አሉ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በትናንትናው የብልፅግና ፓርቲ መክፈቻ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር አባቶቻችን ሀገርኛ ሀሳብ አላፈለቁም። በተዋሱት ሃሳብ ሲጨቃጨቁ፣ ሲጋደሉ የኖሩ ስለሆነ፤ አሁንም ያንን ማስቀጠል ይፈልጋሉ ብለዋል።  

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን አባባላቸውን በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ካሉት ግጭቶች ጋር በማስተሳሰር፤ በኦሮሚያ ግጭት አለ። በአማራ ግጭት አለ። በትግራይ ግጭት አለ። በተለያዩ ቦታዎች ግጭት አለ። የእዚህ ግጭት ጠንሳሽ፣ ጨማቂዎች፤ ትላንትና ፖለቲካ ሲያንቦራጭቁ የነበሩ ሰዎች ናቸው ሲሉ አብይ ተናግረዋል።


የሰላም ሚኒስትር የነበሩት ብናልፍ አንዱዓለም በአሜሪካ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆኑ

ህዳር ወር 2017 ላይ ሹመት የተሰጣቸው አምባሳደር ብናልፍ አንዱዓለም በዛሬው ዕለት ቃለመሐላ መፈፀማቸው ተነግሯል።

ይህን ተከትሎ ከፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የሹመት ደብዳቤ እና የሥራ መመሪያ መቀበላቸው ለማወቅ ተችሏል።


ትራምፕ በብሪክስ አባል ሐገራት ሸቀጦች ላይ 100% የግብር ጭማሪ እንደሚያደርጉ አስጠነቀቁ

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የብሪክስ  አባል ሐገራት የአሜሪካዉን ዶላር ትተዉ በሌላ ገንዘብ ለመገበያየት ከወሰኑ ለዩናይትድ ስቴትስ ገበያ በሚያቀርቡት ሸቀጦቻቸዉ ላይ የ100% የቀረጥ ጭማሪ ለማድረግ አስጠንቅቀዋል።

ትራምፕ ትሩዝ ሶሻል በተባለዉ የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴያቸዉ ባሠራጩት ማስጠንቀቂያ እንዳሉት የብሪክስ አባል ሐገራት ከዶላር ለማፈንገጥ ማሰባቸዉ «ማብቃት  አለበት።

ትራምፕ የብሪክስ አባል መንግሥታትን ለዩናይትድ ስቴትስ «የጠላትነት አዝማሚያ» የሚታይባቸዉ በማለት ወርፈዋቸዋልም።




ኤም 23 ወደ ኪንሻሳ እንደሚገሰግስ አስታወቀ

ትላንት የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ምሥራቃዊ ከተማ ጎማን በአብዛኛው የተቆጣጠሩትና በሩዋንዳ የሚደገፉት የኤም 23 አማጺያን፣ ወደ መዲናዋ ኪንሻሳ ግስጋሴያቸውን እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።

“የነጻነት ግስጋሴያችንን እንቀጥላለን ነው” ያለው የአማጺያኑ መግለጫ፡፡

የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ፊሊክስ ቺሰኬዲ በበኩላቸው ከበድ ያለ ወታደራዊ ምላሽ እንደሚሰጡ አስታውቀዋል።


ደማቁ የአገው ፈረሰኞች በዓል በመከበር ላይ ነው

ደማቁ የአገው ፈረሰኞች በዓል በመከበር ላይ ነው።

85ኛ የአገው ፈረሰኞች ክብረ በዓል በእንጅባራ ከተማ መከበር በተለያዩ ስነስርአቶች እየተከበረ ይገኛል።

አሁን በአገው ምድር እንጅባራ ፈረሰኛው ስታዲየም ትርኢት በማሳየት ላይ ናቸው።

እንኳን አደረሳችሁ!!


የቀድሞው የፓርላማ አባል አቶ ብርሃኑ አዴሎ የኢሰመኮ ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ

በቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የስልጣን ዘመን ለስድስት ዓመት ገደማ የካቤኔ ጉዳዮች ኃላፊ ሆነው የሰሩት አቶ ብርሃኑ አዴሎ፤ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንን (ኢሰመኮ) እንዲመሩ በፓርላማ ተሾሙ። አቶ ብርሃኑ የብሔራዊው የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት፤ ተቋሙን ለአምስት ዓመታት የመሩትን ዶ/ር ዳንኤል በቀለን በመተካት ነው።


ቀሲስ በላይ መኮንን በአምስት ዓመት ጽኑ እስራት እና በ10 ሺህ ብር ተቀጡ

ሐሰተኛ ሰነድ ተጠቅመው ከአፍሪካ ሕብረት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ገንዘብ ለማውጣት ሞክረዋል በሚል የወንጀል ክስ የተመሠረተባቸው ቀሲስ በላይ በአምስት ዓመት እስራት እና በ10 ሺህ ብር እንዲቀጡ ተወስኗል።




ትራምፕ በመወለድ የሚገኝ የዜግነት መብት እንዲቀር ግፊት እያደረጉ መሆናቸው ተሰማ


ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ “በመወለድ የሚገኝ ዜግነት” በመባል የሚታወቀው የዜግነት መብት’ እንዲቀር ወይም እንዲቋረጥ የሚያደርግ ፕሬዝዳንታዊ ማዘዣ ፈርመዋል፡፡

እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ1868 የጸደቀው 14ኛው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ አንድ ሰው የወላጆቹ የዜግነት ሁኔታ ምንም ይሁን ምን በአሜሪካ ግዛቶች ውስጥ እስከተወለደ ድረስ የዜግነት መብቱን የሚያረጋግጥ ሲሆን የሲቪል መብቶች ዋና አካል ተደርጎ ይታያል፡፡

የፕሬዝደንት ትረምፕ ትዕዛዝ ታዲያ በአስፈጻሚው አካል ሥልጣን እና በሕገ መንግሥት ማሻሻያው ዙሪያ ሕጋዊ እና ፖለቲካዊ ክርክሮች ቀስቅሷል።


የዓለማቀፉ ገንዘብ ድርጅት ለአገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ተጨማሪ ብድር አጸደቀ

የዓለማቀፉ ገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ)፣ ኹለተኛውን የኢትዮጵያ የተራዘመ ብድር ግምገማ በማጠናቀቅ ለአገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሃ ግብሩ ትናንት ተጨማሪ 248 ሚሊዮን ዶላር ብድር አጽድቋል።

ድርጅቱ ለኢትዮጵያ 3 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ብድር ባለፈው ሐምሌ ካጸደቀ ወዲህ፣ እስከ ትናንት የለቀቀው ብድር 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል።

መንግሥት ለማኅበራዊ ሴፍቲ ኔት መርሃ ግብሮች የሚሠጠው ድጎማ ከተጠበቀው በታች መኾኑን በግምገማ ሪፖርቱ የገለጠው ድርጅቱ፣ ለጉዳት ተጋላጭ ለኾኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች የሴፍቲ ኔት ድጋፎችን ማጎልበት ያስፈልጋል በማለት መክሯል።

ድርጅቱ፣ የነዳጅ ዋጋ የመንግሥትን ወጪ ሙሉ በሙሉ ሊመልስ በሚችል ደረጃ መስተካከል እንዳለበትም ምክረ ሃሳቡን ለግሷል።


በደቡብ ሱዳን በተከሰተ የአውሮፕላን አደጋ የ20 ሰዎች ህይወት አለፈ

በደቡብ ሱዳን ዩኒቲ ግዛት አነስተኛ አውሮፕላን ተከስክሶ የ20 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ። አውሮፕላኑ ከግዛቷ ተነስቶ ወደ ደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባ በማቅናት ላይ እያለ መከስከሱን የግዛቱ ኮሙኒኬሽን ሃላፊ ጋትዌች ባይፓል መግለጻቸውን ሬውተርስ ዘግቧል።


አምነስቲ ''በአማራ ክልል ያለውን የዘፈቀ የጅምላ እስር የሚያስቆም አስቸኳይ አለም አቀፍ እርምጃ ያስፈልጋል›› አለ

በአማራ ክልል ያለውን የዘፈቀ የጅምላ እስር የሚያስቆም አስቸኳይ አለም አቀፍ እርምጃ እንደሚያስፈልግ ዓለም አቀፉ የመብቶች ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል አሳሰበ፡፡

በክልሉ መንግስት መር የዘፈቀደ የጅምላ እስር መፈጸም ከተጀመረ ድፍን አራት ወራት ተቆጥረዋል ያሉት የድርጅቱ የምስራቅና ደቡብ አፍሪካ ዳይሬክተር ቲገሬ ቻጉታ በክልሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በጅምላ እየታሰሩ ባለበት ሁኔታ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዝምታ ከማሳፈርም በላይ ነው፡፡

የኢትዮጵያ የልማት አጋሮች አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የመብት ተሟጋቾች ጭምር በጅምላ ታፍሰው በግፍ የታሰሩት ሁሉ እንዲለቀቁ ተጽዕኗቸውን ተጠቅመው ግፊት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡




የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ከትራምፕ ጋር በኋይት ሀውስ ሊገናኙ ነው

ኔታንያሁ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ትራምፕ በዓለ ሲመት ከፈጸሙ በኃይት ሀውስ የሚያገኟቸው የመጀመሪያው የውጭ ሀገር መሪ ይሆናሉ ተብሏል።


የጎፋ ተፈናቃዮች ሰብአዊ ድጋፍ አለማግኘታቸውን የተናገሩ ሰዎች መታሰራቸው ተሰማ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ የተፈናቀሉ 627 አባወራዎች በቂ ሰብአዊ ድጋፍ አለመድረሱን ለብዙኅን መገናኛ የገለጹ ስምነት ሰዎች ለእስር መዳረጋቸውን ቤተሰቦቻቸው እና የወረዳው ነዋሪዎችን ዋቢ ባደረገበት አሜሪካ ድምፅ በዘገባው አመልክቷል።

20 last posts shown.