ቸርች እንዴት ነበር?
(How was Church?)
"...መጀመሪያ የሌለው እርሱ ሰው ሆነ!..."
1 ወደ ጢሞቴዎስ 3:16 አማ05
[16] የሃይማኖታችን ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ እርሱም እግዚአብሔር፦ “ሰው ሆኖ ተገለጠ፤..."
✍️ በክርስትና ሕይወት ውስጥ አሳዛኝ ሰው የምንለው ስለ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ትክክለኛ እና ልክ የሆነ እውቀትና እምነት የሌለውን ሰው ነው። ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ማወቅ የክርስትናችን መሠረት እና እግዚአብሔርን መምሰል የምንችልበት ሚስጥር ነው።
ክርስቲያን የምንሆነው ጌታን የተቀበልን ዕለት ሳይሆን በጌታ በኢየሱስ ክርሰቶስ ላይ ባለን መገለጥ ላይ ተመስርቶ ነው።
ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ማንኛውም ሰው የሰው መልክና ቁመና ነበረው፤ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ሰው ተጸነሰ እንደ ሰውም የመወለጃው ወራት በደረሰ ጊዜ ተወለደ።
እንደ ማንኛውም የሰው መልክና ቁመና ይዞ ዕድሜ እየተቆጠረለት በጥበብ፣ በቁመት፣ በሞገስ በእግዚአብሔር እና በሰው ፊት አደገ።
ጌታ ኢየሱስ በዲያብሎስ ተፈተነ፣ በላ፣ ጠጣ፣ ደከመው፣ ታመመ፣ ሞተ እንዲሁም ተቀበረ። ማንኛውም ሰው የሚሆነውን ሁሉ ሆኗል ተፈትኗል ነገር ግን ከኃጢአት በቀር። ከላይ የዘረዘርናቸው ኢየሱስ ምንም እንኳን ዘላለማዊ አምላክ ቢሆንም ፍጹም ሰው መሆኑን የሚያሳዩ ሲሆን ሁሉንም የኃጢአታችንን ዕዳ እንደ እኛ ሰው በመሆን መክፈሉን የሚያስረዳ ነው።
በመጨረሻም ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ የመጣው ከ2017 አመት በፊት መሆኑ አምላክነቱ መጀመሪያ ያለው መሆኑን አያስረዳም። እርሱ መጀመሪያ የሌለው ከዘላለም በፊት የነበረ፣ ያለና የሚኖር አምላክ ነው።
ወደ ቆላስይስ ሰዎች 1:15 አማ05
ሬቨረንድ ተዘራ ያሬድ
ቀን እሁድ 25/05/2017
⛪️ የክብር ሕይወት ቤ/ክ
አዲስ አበባ/ ኢትዮጵያ
መልካም ምሽት!