♡❥нαйιƒ_тùве❥♡


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Religion


አሰላሙ አለይኩም ወራህቱላ
# @HANIF_TUBE01 channel;
ለናንተ ለቤተሰቦቹ የሚመጥን ፦
1. 💁 ❲ኢስላሚክ ringtone)
2. ‍₪አስተማሪ 🏰ታሪኮች
3. አዳዲስ〖መንዙማ₯ነሺዳ〗
4.〖ኢስላሚክ ግጥም ]]
📜ċσмιит
👇👇👇👇
@Hanif_8327
#ማሳሰቢያ:– ልክ ከሆንኩ ከአላህ ነው፤ከተሳሳትኩ ከነብስያዬና ከሸይጧን ነውና ስህተቴን ጠቁሙኝ እኔጂ " Leave' አትበሉ 🙏🙏

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Religion
Statistics
Posts filter


'https://t.me/addlist/3agyuIn4l7IxYTg0' rel='nofollow'>🔞🔞🔞🔞🔞❗️😳
   ሙስሊም ሆናችሁ እስከ አሁን ይሄ ቻናል ሳይኖራችሁ ቴሌግራም እየተጠቀማችሁ ነው?😳😳

ሊያመልጣችሁ የማይገባ ሁሌም ሊኖራችሁ የሚገባ ቻናል ነው።

😳ገብታችሁ እዩት በ ቻናሉ ትገረማላችሁ

አሁኑኑ JOIN በሉ በፍጥነት👇👇👇


በአንድ ወቅት የአቢ ወላጅ እናት (አላህ ጀነትን ይወፍቃቸው እና) በህይወት እያሉ ይኖሩበት ነበር የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ ይዞላቸዋል በጊዜው አሁንም አሂልን አስታሟል ክፍሉ ስለዚህ በቂ ነው እራት በልተን ከጨረስን በኋላ አሂልን የማበላው እኔ ወይም ወንድሜ አዝራን ነን ዛሬ እሱ ነበር ያበላው አይኖቹ ወደ እኔ ሲንከራተቱ ቆዩ ዶክተሩ የተለመደ ነው ካለን በኋላ ሲያየኝ አልደነቅም እኔም አየዋለሁ እራቱ ተጠናቀቀ እና አቢ ለአያን ጥቂት የቁርአን አያ ያሰማን ይችል እንደሆነ ጠየቀው እሺ ብሎ ሱረቱል ዩሱፍን እስከ 10ኛው አያ አሰማን በእሱ እየተደመምን እንዳለ ሳናስበው 11ኛውን አያ አሂል ቀጠለው ክው ነበር ያልነው ጭራሽ አላመንም አሂል ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ድምፁን የሰማነው 32ኛው አያ ላይ (ሰደቀሏሁል አዚም) ግራ ገባኝ ምንም አላመንኩም ማንም አላመነም ሁሉም ድንጋጤ ውስጥ ዝፍቅ አለ በዛች ደቂቃ አስታወሰ ብዬ ደስ ብሎኝ



ጠራሁት ስጠራው ግራ ተጋባ እና ወደ ጀርባው ዞሮ ሌላ ሰው እንዳለ አረጋገጠ ለካ አላስታወሰም ስሙን እንኳን አያውቅም ግን የመናገር ችሎታው ተመለሰ ከዛች ቀን በኋላ አቢ መስጂድ ይዞት መሄድ ጀመረ ጥቂት ጥቂት ተግባቡ ከጀሚልም ከአዝራንም ከአያንም በቃ ከሁሉም ጋር ግን ሴት እኛን አያናግረንም ሱብሃን እንዲህ ሆኖ እንኳን አጂ ነብይ እያለ ይመርጣል ማለት እኮ ነው ለእኔም ያለው አመለካከት እንደዛው ነው አያውቀኝም ገረመኝ በፊት ጊዜ ከነበረው እውቀቱ አንድም አልተጓደለም በደንብ ያውቃል ወንድም እና አባቱን ባባ ወንድሜ ብሎ አይጠራም እንደ ባዕድ ሰው በስማቸው ነው የሚጠራቸው አያውቃቸውማ

ሰሞኑን በጣም ከባድ ጊዜ እያሳለፍኩ ነው የመውለጃ ጊዜዬም ዶክተሯ እንደነገረቺኝ ከሆነ ከዚህ ሳምንት የዘለለ ጊዜ የለኝም ደም ግፊቴ ስለጨመረ ከኡሚ እና ከኡዘይማ ጋር ሆስፒታል ሄድን የሚቀሩኝን ቀናት ነርሶች እየተከታተሉኝ እዛው እንዳሳልፍ ተደረገ

Part // 24 (የመጨረሻ ክፍል )
ka 150 like buhala ይቀጥላል••• •••

❥❥нαйιƒღღ🫶


°°°Halal Love Story🌹°°°

Written By Semira°°°

°°°Ahil & Ferah🍂

🌺ክፍል ሀያ ሶስት

Ferah•••የልብ ምት መቆጣጠሪያው ማሽን ይጮኻል ቀኝ እጁን ያዝኩት ይሞቃል

"መቼ ነው የምትነቃው?…ካየሁህ እኮ ሁለት ሳምንት አለፈ አሁንም አላይህም ማለት ነው? አንተን ማየት ተከለከልን ትሰማኛለህ አይደል? አሁን ግን ንቃ ይበቃሃል እስከ መቼ ነው እንዲህ የምትተኛው?……"

እያለቀስኩ ተነስቼ ወጣሁ እና ከኡዘይማ ጋር ቁርስ ማብሰል ጀመርን ኢልሃን ትንሽ ትንሽ መራመድ ጀምሯል ኡሚ(ኡዘይማን) አቢ(አዝራንን)ፉፋ(ፈራህ) ይላል እና እሱም እየተንቀሳቀሰ አብሮን ቁርስ ሰራን ለመብላት ስንዘጋጅ ዶክተሩ መጥቶ ነበር ትልቅ ዶክተር ነው አርያን ይባላል እድሜው በ50ዎቹ ውስጥ ሲሆን በጣም ጎበዝ ነው አብሮን ቁርስ በልቶ አሂልን ለማየት ወደ ክፍሉ ገባ እና አንድ ነገር አለን ጆሮዬም መሰለኝ ምን እንዳለ ልንገራችሁ



ደነገጥን የደስታ ይሁን የሃዘን ሳለቅስ ነበር ብቻ ገባን አዝራን ለጀሚል እና ለዘይድ(ለአሂል እና ጀሚል አባት) ደውሎ ተናገረ ነቅቶ ሳየው አፍ እና አፍንጫው ላይ ሰው ሰራሽ መተንፈሻ ተገጥሞለታል አላመንኩም የእኔ ጌታ ግን ስንት ውለታ ይሁን የዋለልኝ? ተነስቶ መቀመጥ አይችልም ጭንቅላቱ ላይ የነበረውም ባንዴጅ(ፋሻ) አልተፈታም በተኛበት ሁላችንንም ሲያየን ግራ ተጋባ ዶክተሩም

>

አለን እኔ ትንሽ ልቆይ ብዬ ባስቸግርም አቢ ተቆጣኝ እና እሺ ብዬ ወጣሁ ጀሚል ሃሲነት እና ዘይድ መጡ ግን ማየት አልቻሉም ሌሎች ዶክተሮችም ተጨምረው መጡ አዩት እና ሲሄዱ "እንቅልፍ ወስዶታል" አሉን ከተኛባቸው ቀናት በላይ የነቃበት እለት በጣም የሚከብድ ነበር ዶክተሮቹ ያላቸውን እውቀት የሚፈትን ነበር

ከ3 ቀናት በኋላ





አባቱ ነበር ይህን ያለው አሂል ምንም የሚያውቀው ነገር የለም አያስታውስም አይናገርም አይንቀሳቀስም ሁሉም በእንዲህ እንዳለ አንዳንድ ነገር ያስታውስ እንደሆነ ሁላችንም ገብተን እንየው የሚል ሃሳብ ከአቢ ተነሳ እሺ ብለን ገባን እና ወንበር ላይ ተቀመጥን የየራሳችንን ወሬ ጎን ለጎን እናወራለን አሂል አይኖቹ ይንከራተታሉ ከአንዱ ወደ አንዱ አየን እና በመሃል እንቅልፍ ወሰደው ሳንረብሸው ወጣን ይህን ነገር ደጋገምነው ለብዙ ቀናት

ዛሬም አንድ አዲስ ነገር አለ አለን ዶክተሩ ከአልጋው ተነስቶ መቀመጥ ይችላል በቀን ለ01:00 ብቻ ይሁን ይህም አንድ የአላህ(ሱብሃነሁ ወተአላ) ተአምር ነው በቀን ለ01:00 እየተቀመጠ ይውላል ግን ወዲያው ነው እንቅልፍ የሚወስደው ሳምንት ከሳምንት ለውጥ አለው ግን ትኩረታችን ሁሉ ወደ እሱ ስለሆነ የእኔን እርግዝና ችላ ብለነዋል አንድ ቀን ከኡዘይማ ጋር ለክትትል ሄደን 6ኛ ወር ማገባደጃው ላይ እንደሆነ እና ሴቶች መሆናቸውን ተነገረን በጣም ደስተኛ ነበርን በእሱ ስንደሰት ደግሞ የአሂልን መጥፎ ዜና ሰማን ለተከታታይ ሁለት ቀናት እንቅልፍ አይወስደውም ነቅቶ እያለቀሰ ነው የሚያድረው ቀንም ለሊትም ኢላሂ በብዙ መንገድ ነው የተፈተንኩት አንዳንድ ጊዜ ሃራም ነገሮችን እየሰራሁ መቆየት እፈልጋለሁ ሀሊቁን የተበቀልኩ እየመሰለኝ መለስ እልና ደግሞ አልቅሼ ማረኝ የምላሴን ሳይሆን የቀልቤን እላለሁ

ግራ ገባን የሆነውን አይናገር ቢናገር ለራሱ የሚያስታውሰው ነገር የለም ምን ሊያስለቅሰው ይችላል? ከጂን ጋር ተያያዥነት ሊኖረው ይችላል ተብሎ አያን አንድ ለሊት አቢ አንድ ለሊት አዝራን አንድ ለሊት ጀሚል አንድ ለሊት እያደሩ ይቀሩለት ጀመር ትንሽ መረጋጋት ጀመረ ትንሽ እንቅልፍ ማግኘት ቻለ ከአንድ የስነልቦና ሃኪም የተነገረን አሂል ለማስታወስ ቀጣዮቹ 2ወራት ለእሱ አስፈላጊ እንደሆኑ ነው ማስታውስ ሲችል የመናገር ችሎታውም ይመለሳል የሚል እምነት አላቸው የመጀመሪያውን ወር አገባደደ አሁን ያለው ለውጥ ደግሞ ትንሽ ትንሽ መንቀሳቀስ ችሏል ግን እንደጨቅላ ብዙም ተረጋግቶ በእግሮቹ አይቆምም ይደክመዋል ትንሽ ነገርም ያስደነግጠዋል አሁን የሰውን ስሜት እየተላበሰ ነው

ከ1 ሳምንት በኋላ ጁሙዓ ቀን

ሁሉም ጁሙዓ መስጂድ ለመሄድ እየተዘጋጀ ነበር እኔ አልሄድም እዚሁ እሰግዳለሁ አልኳቸው እና አሂል ወደ ሚተኛበት ክፍል ገባሁ እስከ ዛሬ እንዳለሁም እንደ ሌለሁም የማያውቀው ሰው ስገባ አፈጠጠብኝ አየሁት እና እንዳይደነግጥ ባላየ ወደ መስኮቱ ሄድኩ እና መጋረጃዎቹን መቀየር ጀመርኩ ያን ሁሉ ስሠራ እያየኝ ነው ክፍሉን ማፅዳት ጀመርኩ ተቀምጦ የነበረ ቢሆንም ደከመው መሰለኝ ተኛ እንቅልፍ ግን አልወሰደውም

ትራሱን ሳስተካክልልለት ፈገግ አለ በፈገግታ መለስኩለት እና ወጣሁ ይህን ክስተት ለመናገር እንዴት እንደቸኮልኩ ለአቢ ነበር ቀድሜ የነገርኩት በጣም ደስ ብሎት ለዶክተሩ ነገረው ሚስቱን ማስታወስ ጀመረ ብሎ ግን የዶክተሩ ምላሽ አይደለም ነበር ብሽቅ ነው ያልኩት በየትኛውም ታማሚ ላይ ያዩት እንደሆነ እና ምንም አዲስ ነገር እንዳልሆነ ነገረን ድጋሚ ተስፋዬ ተበጫጨቀ ብላችሁ ይቀላል በቃ መቼም አያስታውሰኝም ማለት ጀመርኩ ህይወት ቀጠለ ምግብም ተመርጦ ይሰጠዋል የእኔም መውለጃ ጊዜ ተቃርቧል የአሂልም ቁስል ስለደረቀ በጭንቅላቱ ላይ የነበረው ባንዴጅ(ፋሻ) ተፈታለት ባያስታውሰንም በጣም ብዙ ለውጥ ማየት ጀመርን አንድ ምሽት ላይ እራት እሱ ክፍል ለምን አንበላም ብዬ ሃሳብ አነሳሁ እንዲያገግም የተሰጠው ክፍል በጣም ሰፊ ነው


Part // 23 loading .....🥰👍👌❤

❥❥нαйιƒღღ🫶


Forward from: 𝕞𝕦𝕛𝕠 amin official
Video is unavailable for watching
Show in Telegram
ቀለበትሽን 💍በ mujo amin
ምርጥ ግጥም Lyrics video


📱ለስልኮ የሚሆን ምርጥ ኢስላሚክ ጥሪ 🎙🎙

ተጋበዙልኝ‼ 🥰🥰

መልካም ቀን 🤎🤎
JOIN US ❯❯ нαйιƒ_тùве

❥❥нαйιƒღღ🫶


°°°Halal Love Story🌹°°°

Written By Semira°°°

°°°Ahil & Ferah🍂

🌺ክፍል ሀያ ሁለት

Ferah•••ቀዶ ጥገናው ከተጀመረ 07:00 ሆነ ሶስቱን ሰዓት በዱዓ አሳለፍኩት አዝራን እና ጀሚል ከሄዱበት ፕሮሰሱን ጨርሰው ተመለሱ ጀሚልም ለሃሲነት ወደ ቤት እንድትወስደኝ አዘዛት እኔ ግን አልሄድም አልኩ ቢያንስ መጨረሻውን ሳላይ እንደማልሄድ ተናገርኩ ግን ወሲያ ስላለው እንድሄድ ነገሩኝ እሺ እንጂ ምርጫ አልነበረኝም መኖሪያ ቤት ስንደርስ ልብሶቹን ለመሳኪኖች እንድንሰጥ ነበር ወሲያው እያለቀስኩ ልብሶቹን አወጣን ግን አንድ ልብሱን አልሰጥም አልኩኝ በእሱ ላይ በጣም የምወደው ጀለቢያ ነበር ሃሲነት እሺ ብላኝ እሱን ጀለቢያ ብቻ ትተን የቀረውን ሰጠን አድርሰን ስንመለስ ቀዶ ጥገናው እንዳለቀ ጀሚል ደውሎ ነገረን

ግን ዶክተሮቹ ለ72:00(ለ3 ቀናት) እንደማይነቃ ነገሩን እንደማይነቃ ልበላችሁ እንጂ እንደማይነቃ ያውቃሉ እኛም እናውቃለን ግን አላህ አለ በእሱ መኖር ያመነ ደግሞ በእሱ ተስፋ ሊኖረው ይገባል አሂልን ማገገሚያ ክፍል አስገቡት መሸ ገብቶ ማየትም አይቻልም ማናገርም አይቻልም በመስታወት ከማየት ውጪ ምንም ማድረግ አይቻልም



አለኝ አቢ ነበር ያለኝ እሺ ብዬው ከጎኑ ተቀመጥኩ እና ጭንቅላቴን ይደባብሰኝ ጀመረ እንባዬ ዳግም ፈለቀ



ሲል አበረታኝ









አለኝ በሹክሹክታ









አለ እሺ እሺ ብለው ሄዱ ጀሚልም አብሮን ትንሽ ቆይቶ ሄደ አቢ እና እኔ ቀረን እኩለ ለሊት አለፈ





ለሊት 09:00 ሆነ





እለዋለሁ



ብሎኝ አግዳሚ ወንበር ላይ ጋደም አለ አላህ ከአቢ ቀልብ ይጠብቀኝ በጣም አደከምኩት እኔ አሂልን በመስታወት አሻግሬ እያየሁ ነው ማየቱ አይጠቅምም ለይል መስገድ ይሻላል ብዬ ባዶ ክፍል እንዲሰጡኝ ጠየቅኳቸው እቃ ማስቀመጫ ክፍል ነበር

ከ2 ቀን በኋላ አሂል አልነቃም

ዶክተሮቹ እንደሞተ ነገሩን 😩😩😩 ቅስሜ ስብርብር አለ መቋቋም አልቻልኩም በዚህ ሰዓት እርግዝናውም እየፈተነኝ ነበር ምግብ በልቼ አይስማማኝም በጣም ፈተነኝ አቢ እንድረጋጋ ቢመክረኝም አልቻልኩም በቃ ሁሉም ነገር ፈተነኝ አቢ

ሲለኝ



እኔን ሲያየኝ ሁሉም ማልቀስ ጀመረ የልብ ምት መቆጣጠሪያው ማሽን ሲጮህ ጆሮ ያደነቁራል በዚህ መሃል አንድ ህንዳዊ ዶክተር የሆነ ነገር አለን



አለን የዛን ሰዓት ትንሽ ተረጋጋሁ መረጋጋት ባይሆንም እንዲድን ቢያንስ ዱዓ ማድረግ እችላለሁ እውነትም ምንም ተስፋ የለውም ጀሚል እንዲህ የሚሉን ጀናዛውን ላለመስጠት ነው ይላል ኡዘይማም እንደዛው የሁሉም ሃሳብ አይድንም ነው በዚህ ሰዓት አቢ አንድ ውሳኔ ሰጠ
.

በቃ የግል ዶክተር እንቅጠርለት እና ተጨማሪ ቀን የሚፈልግ ከሆነ እኛ እንንከባከበዋለን አለ ጥሩ ውሳኔ ነበር አቢን አመሰገንኩት እኔ ሁልጊዜ ነው የማመሰግነው ሃያቱን ያቆይልኝ :::አሚን:::

ቤት ወሰድነው እና ሁለት ዶክተሮች ተቀጠሩለት በጣም ውድ ነው እሱ ያለበት ክፍል መግባት አይቻልም አንድ ነርስ አለ እሱ ብቻ ነው አይቶ ነው ደህና ነው ደህና አይደለም የሚለን ከዛ ውጪ ምንም የለም ከቀን ወደ ቀን የሰውነቱ ግለት ይጨምራል ግን አይነቃም ኮማ ውስጥ ከገባ 6ቀን ሲሆነው አንድ አስደሳች ነገር ተነገረን የልብ ምቱ ተመልሷል አልሃምዱሊላህ ብለን ሳንጨርስ ከመጠን በላይ ምቱ ከሚገባው በላይ መምታት ጀመረ ተባልን ድጋሚ ማልቀስ ጀመርኩ

ዶክተሮቹ መጥተው አዩት እና ወደ መግሪብ አካባቢ ምቱ እንደተስተካከለ ተነገረን ከተኛ 14ተኛ ቀኑን ይዟል ሱብሂ ሷላት ሰግጄ ሁለት ሱራ ከቀራሁ በኋላ ከክፍሌ ወጣሁ ሁሉም ከመኝታ ክፍሉ አልወጣም ቀስ ብዬ አሂል ወደ ተኛበት ክፍል አመራሁ ከዶክተር ውጪ እሱን ገብቶ ማየት አይቻልም ነበር ግን የዛን ቀን ላየው ገባሁ እና ክፍሉን ቆለፍኩት

Part // 23 ka 100 like buhala ይቀጥላል••• ••• •••

❥❥нαйιƒღღ🫶

589 0 6 7 104

🥰ኸሚስ ሙባረክ 🥰

>> ይገርመኛል መድከሜ    
በዛብኝ ስጋ ደሜ
ላልጨርሰው አሕትሜ    
አለቀብኝ ቀለሜ
ብራናዬ መክተብያ       

★አላ ሀዲል በራያ

   ☞#ሰላተላ  #ወሰለም ×➋


>> የአላህ ያ ሰመድ        
ሰላት ሰላም አውርድ
በዘይኔ በኛ ዉድ        
በአስሀባ ዘመድ
አጉርፍባቸው ሀያ 🥁🥁

JOIN US ❯❯ нαйιƒ_тùве

❥❥нαйιƒღღ🫶


.
በህይወት ከባዱ ነገር ሰው መላመድ።
እጅግ በጣም ከባዱ ደሞ
የለመድከውን ሰው ማጣት💔

🌚🌜መልካም ምሽት🌛 🌚
JOIN US ❯❯ нαйιƒ_тùве

❥❥нαйιƒღღ🫶




የእኔ ስራ ማልቀስ ብቻ ሆነ ለምን አልነገረኝም? ለካ ሊነግረኝም ሰዓት አልሰጠሁትም







አልኩት እና ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ ጀሚልም







ምንድነው የምሰማው ይህን ያህል ተስፋ የሚያስቆርጥ ነገር ነው? አቢ ሳይቀር እንባውን ጠርጎ ወደ መርከዙ ሄደ ኡዘይማም ኢልሃን አስቸግሯት ልታስተኛው ሄደች አዝራን እና ጀሚል ሊፈርሙ ሄዱ ኡሚ ኑርን ትምህርትቤት አልሸኘሁም ብላኝ ሄደች ሁሉም ሲሄዱ አንድ ነገር ይሉኛል ለ10:00 የሚቆይ ቀዶ ጥገና ስለሆነ ተመልሰሽ መጥተሽ ታይዋለሽ እዚህ አትሁኚ ግን አልቻልኩም

ምን ያህል ማደንዘዣ ይወጉት ይሁን? ማታ እንደምን ሆኖ ይሁን? እስኪ ልናደድ ማታ ባነሳለትስ ስልኩን? ምንድነው የሚጎድልብኝ? ውርደት መሰለኝ ስልክ ማንሳት? እ…… እና አሁን ክብር ነው? እስኪ ልናደድ ምናለ ባናግረው? ዝም ብለውስ? ምን ነበረበት አያገባኝም ሲለኝ ዝም ብለውስ? ግን ልክ ነው ሁሉም የአላህ ቀድር ነበር ለእኔ ብሎ ራሱን ገደል የሚከተው አሂል አሁን በማደንዘዣ ሃይል ውስጥ ተኝቷል ሁሉም ተስፋ ቆርጧል ትቶኝም ሄዷል በአስታማሚው ወንበር ላይ ቁጭ እንዳልኩ ዙሁር አዛን አለ ተቀያሪም ዶክተር እየገባ ነበር እንዳልኳችሁ ለ10:00 የሚቆይ ቀዶ ጥገና ስለሆነ በየ05:00ቱ ሽፍት ይደራረጋሉ እኔም ለአንዲት ነርስ የምሰግድበት ቦታ እንድትጠቁመኝ ጠየቅኳት

Part 22 ka 100 like buhala ይቀጥላል••• ••• •••

751 0 3 21 122

°°°Halal Love Story🌹°°°

Written By Semira°°°

°°°Ahil & Ferah🍂

🌺 ክፍል ሀያ አንድ

ከዚህ በኋላ ተራኪዋ Ferah ብቻ ናት

ferah•••ከአላህ በታች በአሂል ላይ የነበረኝ ተስፋ አንድ በአንድ ተመናመነ የዚህን ያህል ጨካኝ መሆኑን አላውቅም ነበር ከዚህ በላይ ጥላቻውን ሊያሳየኝ አይችልም "ስለተፈጠረው ልጅ ምን አገባኝ?" እኮ ነው ያለኝ ቀና ብዬ እንባዬን ጠረግኩ እና ፈገግ እያልኩ



አልኩት እሱም ቢሆን ወዲያው ከነበረበት ሃሳብ ወጥቶ



ብሎኝ ሄደ የውስጤን በውስጤ አፍኜ ምንም እንዳልተፈጠረ ቁርስ በልተን ወደ ስራ ሸኘሁት ግን እየቆየሁ ስመጣ ያላቸውን ነገሮች ማስተንተን ጀመርኩ ድንገት ተነስቼ በሻንጣ ልብሶቼን ያዝኩ እና ወጣሁ የቀድሞ ቤተሰቦቼ ጋር ማለት ነው ስደርስ ናፍቀውኝ እንደሆነ የመጣሁት ነገርኳቸው ሁሉም ጥሩ ጥሩ በሚል ተቀብሎኝ ሲንከባከቡኝ ዋልኩ አቢ ከመርከዙ ሲመለስ እንደመጣሁ ሲያይ ደስ ያለው ቢሆንም አልተዋጠለትም እና አሂልን አስፈቅጄ እንደመጣሁ ነገርኩት ከአንድ ቀን በላይ ግን እዚህ መቆየት እንደማልችል ነገረኝ

አለኝ እሺ እንጂ ምን መልስ አለኝ "እሺ" አልኩት ሻንጣ መያዜ በተመሳሳይ ኡዘይማ ስትመለከት ደስ አላላትም ፈራህ ተጣልታችኋል አይደል? ብላ አስጨነቀቺኝ ለእሷ ብቻ ለማንም እንዳትናገር አስጠንቅቄ ነገርኳት ከሀ እስከ ፐ አዘነች ግን ትቼው መምጣት እንዳልነበረብኝ በብዙ መንገድ ነገረቺኝ



በማለት መከረቺኝ ተኝቼ ነበር በአልጋው ጫፍ ላይ ተቀምጣ ነው ይህን ያለቺኝ ቀጣዩን ለህሊናዬ የቤት ስራ ሰጥታው ሄደች መሽቷል እሷ ከተለየቺኝ ብዙም ሳይቆይ ስልኬ ጠራ አየሁት አሂል ነው ጭራሽ ከደወለ እንዳያገኘኝ ስልኩን ዘጋሁት እና ተኛሁ ስልኩ ዳግመኛ ሳይጠራ ዝግ እንደሆነ ጎህ መቅደድ ጀመረ ፈጅርን ሰገድኩ እና ተኛሁ ብዙም እንቅልፍ ሳይወስደኝ ኑር መጥታ ቀሰቀሰችኝ አሂል ደውሎ ስለሆነ ያነሳችውን ስልኳን እየሰጠቺኝ እሷም ስላለች እንቢ ልል አልቻልኩም ተቀብያት እንድትወጣ ነገርኳት ሄደች

አልኩት





ከዛ ትንሽ የሳቅ ድምፅ ሰማሁ እና ስልኩን ደጋግሜ አየሁት ቅጥል ነበር ያልኩት



ሳላስጨርሰው ጣልቃ ገብቼ





ብሎኝ ከት ከት ብሎ ሳቀ እርር… ነበር ያልኩት



አልኩት መጀመሪያ የነበረው ረጅም ሳቅ ወደ ረጅም ለቅሶ እየተቀየረ



ውስጤ ተረበሸብኝ እና አልጋው ላይ ተረጋግቼ ተቀመጥኩ



እንባ እየተናነቀኝ ሻንጣዬን ማዘጋጀት ጀመርኩ





ስልኩ ተዘጋ የሆነውን ለመጠየቅ ስላልቻልኩ እያለቀስኩ ነበር ስልኩም አይሰራም እንዲሁ ልብሶቼን እየሰበሰብኩ ሣለቅስ አቢ መጥቶ በሩን አንኳኳው ስከፍትለት





አቢ የተናገረው ጥያቄ ሳይመለስልኝ አዝራን መጥቶ



አለን አሁን አሂልን አይደለም እንዴ ያናገርኩት? ግራ ገባኝ ለካ ቀዶ ጥገና ክፍል ከመግባቱ በፊት የመጨረሻውን ነው ያናገረኝ አቢ እና አዝራን ባለሁበት ትተኝ ሲሄዱ ኡዘይማ መጣች ከልክ በላይ እያለቀስኩ ነበር አረጋግታኝ አብረን ሄድን ወደ ቤት ስንደርስ የበሩ እጀታ ላይ ደም ይታያል የቤቱ ወሳኝ ሊነኩ የሚችሉ እቃ መገልገያዎች ላይ በሙሉ በቃ አልቅሼ አላበቃሁም ሊያስፈልጉ የሚችሉ ልብሶችን ይዘን ሄድን እውነትም አሂል surgery ክፍል ነው እንዴት ገባ መቼ ገባ? ለእኔም ጥያቄው አልተመለሰልኝም ማንም እንደተጣላን አያውቅም ሁሉም የሚለው ለፈራህ ይዳንላት ነው ቢድንም እኮ ተፋተናል

ጀሚልም ያፅናናኝ መስሎት አሂል ያልተረከልኝን ሁሉ ይነግረኝ ጀመር


°°°Halal Love Story🌹°°°

Written By Semira°°°

°°°Ahil & Ferah🍂

🌺ክፍል ሀያ

Ahil•••ከትላንቱ ምሽት ጀምሮ(ልጅ እንዳለኝ ከተነገረኝ ቀን ጀምሮ) ልክ እንዳልሆንኩ ጠንቅቄ አውቃለሁ ይገባኛል ጨካኝ ነህ እንደምትሉኝም ሳልዋሽ የምነግራችሁ ነገር እኔ ልጅ እንዲኖረኝ አልፈልግም አጭር ቃል "የማላሳድገው ልጅ ምን ይሰራልኛል?"- "እኔ ከሞትኩ በኋላ ፈራህን ማን ሊያገባት ነው?"-"ንገሩኝ በእኔ ምክንያት የ23 አመቷ ሴት ብቻዋን ልትቀር ነው?" አሁን የእኔን ልጅ(ለካ መንታ ናቸው የኔን ልጆች በሚለው ይስተካከልልኝ) የሚቀበለው ሰው ማነው?! ህይወቷን እንዳበላሸሁት ነው የተሰማኝ እኔ እንዲህ እንድትሆን አልፈልግም ምክንያቱም አይገባትማ…አይገባትም ለእሷ ይህ ሁሉ አይገባትም ከአጠገቤ ሂጂ ብላትም ስትርቀኝ ትናፍቀኛለች በቃ ችግር ነው ሁሉም ነገር ችግር ነው ትላንት እና ዛሬም ምን ያህል እንዳስከፋሁአት አላውቅም ግን ኢላሂ ከቀልቧ ጠብቀኝ እያልኩህ ነው የግል ዶክትሬን ሳናግረው 4 ቀዶ ጥገናዎችን ታደርጋለህ ግን እተርፋለሁ ብለህ አታስብ ብሎኛል

ዛሬም እንደተለመደው የሰሞኑን አዳዲስ ወንድሞቼን ቁርዓን በጥቂቱ አሳፍዤ ወደ ቤት መጣሁ ካገባሁ በኋላ አንድ ድክመቴን ልንገራችሁ? ቤት ከገባሁ ለኢሻ መውጣት አልችልም ያው ብዙ የሚያስቀሩኝ ነገሮች አይጠፋም ፈራህን በራሱ ቶሎ መለየት አይቻልም ስለዚህ አሱር አዛን ሲል እገባለሁ እስከ ኢሻ እቆያለሁ እንዳልኳችሁ ከሁለቱ ሰዎች ጋር ኢስላማዊ ነገሮችን በመነጋገር እንቆያለን ለዛ ስለሆነ ስገባ ማምሸቴ የተለመደ ነው በዚህ ጉዳይ ከፈራህ ጋር ተነጋግረን አናውቅም ፈራህ ሁልጊዜ ምን ስታደርግ እንደማገኛት ልንገራችሁ ደግሞ ካርቶን ፊልም ስታይ ህፃንነት በእሷ አበቃ እንደቁም ነገር ደግሞ እከሊት እከሌ እያለች አሻንጉሊት ፊልም ትተርክልኛለች ግርም ነው የሚለኝ ሰው እንዴት ቅርፅ በሌለው አሻንጉሊት ይታለላል? ወሏሁ አዕለም ወደ ውስጥ ስገባ



አለቺኝ



ልክ ይሄ ሸይጧን የላከው ሰው አለ አይደል? እንደዛ ነው የሆንኩት ምንም አላለቺኝም





ብያት ወደ መኝታ ክፍል ሄድኩ የተናገርኳት ንግግር ለእኔ በራሱ ከባድ ሆኖብኛል እራቱን ሳትበላ መጣች ልብስ ለመቀየር የሸሚዜን ቁልፍ እየፈታሁ ነበር



አለቺኝ ባልሰማ ዝም



ፀጥ አልኳት





በዛች ቅፅበት የማላውቃትን ፈራህ ሆነችብኝ መጮህ ጀመረች



ብላኝ ሄደች እና ተመልሳ መጥታ የአልጋውን ልብስ ለብሳ ተኛች





አለቺኝ ቀስ ብዬ እኔም ገብቼ ተኛሁ እንቅልፍ ከየት ይምጣ? ፈራህ ግን ሳይወስዳት አይቀርም ብዬ ሳልጨርስ ዞረች ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወስዷታል ዛሬ የሰራሁት ነገር ልክ አይደለም ፀፀቱን አልቻልኩትም ፈራህ ምን ያህል አዝናብኝ ይሆን? ለፈጅር የነቃሁት እንዲሁ በሃሳብ ስንገላታ ነው

ዛሬን በፈራህ ሳልቀሰቀስ ተነሳሁ ሻወር ወሰድኩ እና እንድትነሳ ቀሰቀስኳት



ብላ ሌላ ሰጠችኝ መጥፎ ሆኖ ሳይሆን እሷ ያልሰጠቺኝን እንድለብስ አትፈልግም ነው ነገሩ ተግባብተናል እሺ ብዬ እሷ ያለችውን ለበስኩ እና ወደ መስጂድ አመራሁ በእያንዳንዱ እርምጃዬ ልክ አላህ እድሜ እንዲሰጠኝ ቢሰጠኝስ ምን እንደሚጎድልበት እየጠየቅኩት አመራሁ ስደርስ አንድ ጀናዛ ሊሰገድበት መጥቷል ከጀናዛው ጋር ተፋጠጥኩ የኔ እስከሚመስለኝ ነበር የደነገጥኩት ከምሽቱ 02:45 አካባቢ ነው የሞተው ይላሉ ኢሻ ሷላትን በእዚሁ መስጂድ ውስጥ ሰግዶ ወደ ቤቱ ለመሄድ መንገድ ሲጀመር ድንገተኛ የልብ ህመም ነበረበት ቤቱ ሳይደርስ ሞተ እያሉ ሲያወሩ ሰማሁ እና ፈራህን ያስቀየምኳት ደርሶ ትዝ አለኝ ለምን እንኳን እንዲህ እንደማደርግ ሳልነግራት እኔስ እንደዚህ ወንድሜ ብሞት ኢላሂ በእሷ አትፈትነኝ በቃ ምን እያሰብኩ እንደሆነ አሁን ስገባ እነግራታለሁ ብዬ ወሰንኩ

ሰግደን እንደጨረስን ሱና ሷላት ብቻ ሰግጄ ቁርዓን ሳልቀራ ወደ ቤት ከነፍኩ ጀናዛውን ካየሁ በኋላ በጣም ነበር የፈራሁት በድጋሚ ፈራህን የማገኛት አልመሰለኝም 🔛ወንድሜ አንድ ነገር ልንገርህ? በየትኛውም ጉዳይ ላይ ከማርፈድ ተጠንቀቅ ቤት ስደርስ ፈራህ ቁርስ እየሰራች ነው



አለቺኝ ስለጀናዛው ነገርኳት እና ስለማስበው ለመናገር







እንደ እብድ ሆነች





ያለወትሮዋ እና ያለልምዷ ንግግሬን አቋርጣ በየመሃል እየገባች ታናድደኝ ጀመረ









አልኩ የሚጎዳ ቃል እንደተናገርኩ አውቃለሁ ግን በልጁ ፍፁም ልስማማ አልችልም ቀጥሎ ምንም አላለቺኝም ፀጥ አለች አንገቷን ደፋች እንባዋ ሲረግፍ ይታየኛል "ፈራህ" ብዬ ስጠጋት ወደ ኋላ ሸሸች ግራ አጋባኋት ብቻ ኢላሂ ከቀልቧ ጠብቀኝ እላለሁ ግን ደግሞ በአንድ በኩል ለራሷ ህይወት አለማሰቧ ያናድደኛል

ραят// 21 ka 100 like buhala ይቀጥላል •••🫶🫵🫰

❥❥нαйιƒღღ
🫶


*🥀 Ahil & ferah 🥀* "የተሰኘው ታሪካችን እንዴት አያቹት🤔 ?¿
Poll
  •   {በጣም አሪፍ ነዉ} 🥰
  •   [ምንም አይልም] 😍
122 votes


°°°Halal Love Story🌹°°°

Written By Semira°°°

°°°Ahil & Ferah🍂

🌺 ክፍል አስራ ዘጠኝ

Ferah•••ከተናገርኩ በኋላ ቤቱ በጫጫታ የሚሰማኝ አልነበረም አቢ እና ጀሚል አሂልን እያረጋጉ ዝም አሉኝ



ስላቸው በድጋሚ ፀጥታ ሰፈነ



አልኩ በቃ እራቱ የደመቀው ከዚህ ጊዜ በኋላ ነው አሂል ግን ደስተኛ አይመስልም እንዲሁ እነሱ እየተንጫጩ አምሽተው ከለሊቱ 05:00 አካባቢ ሁሉም ሄዱ አሂል አሁንም እንደቆዘመ ነው ሁኔታውን ሳየው ተናደድኩ ጭራሽ ሳሎን የነበሩትን እቃዎች በማነሳሳት ያግዘኛል ስል እሱ ቀድሞውንም መኝታ ክፍል ተኝቷል በቤተሰቡ መሃል ልጅ አለህ ሲባል መቆዘሙ እና መሰላቸቱ ሳያንስ ገና ትቶኝ ተኝቷል ምንም አላለኝም በቃ እስከዚህ ነው ፍቅር? በቃ ከአንድ ሰው ውጪ ማስተናገድ አይችልም ቆይ እሱ ልጅ አይፈልግም? አዎ አይፈልግም ይሆናል ለዛ ነው እንዲህ በማሰላሰሌ ሲወሰውሰኝ የነበረውን ሸይጧን ያስደሰትኩት ስለመሰለኝ የተመገብንባቸውን እቃዎች እንኳን ሳላነሳ እኔም ሄጄ ተኛሁ ጀርባ ለጀርባ እንደተኛን ጎህ እየቀደደ ፈጅር አዛን አለ ሰዓቱን ጠብቄ ተነሳሁ እና ቀሰቀስኩት



እሺም እምቢም ሳይለኝ ተነስቶ ወደ ሻወር ክፍል ገባ ግራ ገባኝ ቆይ ምን ነካው? ጀለቢያውን አውጥቼ ጠበቅኩት ቢያንስ ጀለቢያውን ሲቀበለኝ ያናግረኛል ብዬ ነበር ነገር ግን ፀጥ እንዳለ ተቀብሎኝ ለብሶ ወጣ በቃ ቅር ቅር እያለኝ ፈጅርን ሰገድኩ እና ቁርስ ለመስራት ወደ ታች ወረድኩ እሱን እየሰራሁ የማታዎቹን እቃዎች ማነሳሳት ጀመርኩ በጣም ደክሞኝ ነበር እንደተለመደው ሰዓቱን ጠብቆ መጣ ቁርስ በላን ድጋሚ የስራ ልብሱን መተኮስ ጀመርኩ ስጨርስ አዘጋጀሁለት ለብሶ ሄደ ቻው ብዬ ተሰናብቼው ጥቂት ጋደም አልኩ ግን የምን እረፍት? ከየት ሊመጣ ስራ ስፈታ ከተኛሁበት ተነስቼ የቁም ሳጥኑን ልብሶች ማመነቃቀር እና ዳግም ማስተካከል ጀመርኩ በዚህ መሃል አንድ የታሸገ ወረቀት ወደቀ ምንም ትኩረት አልሰጠሁትም

ማስተካከሉን ተያያዝኩት በዚህ መሃል ኑር ዛሬ ትምህርት ስላልነበራት እኔ ጋር መጥታ ማሳልፍ ትችል እንደሆነ ደውላ ጠየቀችኝ እንደምትችል ነገርኳት እና የታሸገውን ወረቀት ወዳገኘሁበት ቦታ ለመመለስ ወስኜ እንዳለ ከፍተሽ እይው የሚል ነገር በከባዱ ወተወተኝ እኔም ቀስ ብዬ ከፈትኩት በመጀመሪያ አሂል ኢብኑ ዘይድ ኢብኑል ዚርዋ የሚል ረጅም ስም አለ የአሂል ስም ከነአያቱ ማለት ነው ቀጥሎ የሆነ በx-ray ፎቶ የተነሳ ነገር ነው የትኛው የሰውነት ክፍል እንደሆነ አልገባኝም ግን ከውስጣዊ የሰውነት ክፍል ውስጥ የአንዱ ነው ድንገት የሆነ ችላ ያልኩት ንግግር ትዝ አለኝ "ብንጋባ በራሱ በሃያት ለመቆየት ከሁለት አመት የዘለለ ጊዜ የለኝም" ምን ለማለት ፈልጎ ይሁን እንደዛ ያለኝ? ህመሙንስ እስከአሁን ለምን አልነገረኝም? እኔስ ምን አስቤ ነው እስከ አሁን ያልጠየቅኩት?

ወረቀቱን እንደያዝኩ ወደ ድርጅቱ መገስገስ ጀመርኩ ለኑር ደውዬ እንዳትመጣ ነገርኳት እና ወደ ቀድሞው ጉዞዬ ቀጠልኩ ስንት ሰዓት እንደደረስኩ አላህ ይወቅ ብቻ መድረሴን አስታውሳለሁ ወደ አሂል ቢሮ ገባሁ አልነበረም ፀሐፊውን ስጠይቀው

>

ከሁለቱ ቃላት ውጪ በደንብ አልሰማሁትም ነበር ወደ ስብሰባው ስሄድ ከእንግዶቹ ጋር ጨርሰው የስንብት እየተጨባበጠ ነበር እነሱን ሸኝቶ ሲዞር ተገናኘን እንዳላየኝ ሆኖ ወደ ቢሮው ሄደ ተከተልኩት ቢሮው ከገባ በኋላ



አለኝ "እውነት ይህ አሂል ነው?"



ተኮሳትሮ ተመለከተኝ ጥቂት ለማሰብ በሚመስል ዝም ካለኝ በኋላ





አልኩት ወረቀቱን እያወጣሁ ወዳለሁበት ተጠግቶ ነጠቀኝ እና ወረቀቱን ቀዳዶ ወደ ትናንት የወረቀት አካላት ቀየረው ደነገጥኩ



አልኩት ግራ እየገባኝ



"ምን እያለ ነው? እንዴ! ምንድነው የሚለው? ስራ አናዶት ይሁን? በቃ ልሂድ እውነትም የምንኖረው ለመቀበር ነው"



አልኩት እና ከት ብዬ ሳቅኩ የሚስቅ መስሎኝ ፀጥ አለ እንዴት እንዳፈርኩ ስቅቅ ነው ያልኩት እና ፈገግ እያልኩ





አለኝ ከቢሮው በሩን ከፍቼ እየወጣሁ በድጋሚ "ቻው" አልኩት የምጠብቀው ትንሽ አውርተን ትሄጃለሽ ፣ ትንሽ ቆዪ ፣ አትሂጂ የሚሉ ቃላትን ነው



ስለው ባለበት ሳይንቀሳቀስ



አለኝ ምን እንደምጠብቅ ታውቃላችሁ? ከአሁን አሁን መጥቶ እንደተለመደው ግንባሬን ይስመኛል ግን የለም እሱን ከተለየሁ በኋላ ብቻዬን "ቻው"-"ቻው" እያልኩ ወደ መኪናዬ ገባሁ የአሂል ፀባይ ፍፁም የማላውቀው እና የማልረዳው ሆኗል ራሴን ብዙ ጊዜ ከግጭት ለማራቅ እየሞከርኩ ቢሆንም የአሂል ነገር ግን ከቀን ወደ ቀን እየተለወጠ መጥቷል

ραят// 20 ka 50 like buhala ይቀጥላል •••
🫶🫵🫰

❥❥нαйιƒღღ🫶

917 0 4 10 61

   [ ገፀ ሰማይ ላይ . . .]
ኮከብ ተዘርቶ ብርሀን ሲታጨድ
  ልቤን አድርጋት የፍቅር አፀድ ፡
እንደ ጨረቃ. . .
በፅልሙ መሀል ሙት ነፍሴ ትንቃ ፡
:
ይሄም ያልፋል . . .
ይገፈፋል እንዳልነበር
ይዘከራል እንደ "ነበር" !
ብለህ በላት
ሲያጥራት ተስፋ ፡
ልቤን ያዛት ፡
ከእዝነት እቅፍ እንዳ'ጠፋ ።

ሲገፈፍ ፅልሙ ስትርቅ ጨረቃ
ፀሀይ ስትፈግግ ከውኑን አድምቃ ፡
ትፈንድቅ ሩሄ. . .
ይልቀቃት አዚም ድካም ህመሙ ፡
ባ'ንተ አይደለም ወይ
ፅልመት ተረትቶ ብርሀን የሞላው አለሙ!
:
🌞መልካም ቀን ⛅🌤

JOIN US ❯❯ нαйιƒ_тùве

❥❥нαйιƒღღ🥀


°°°Halal Love Story🌹°°°

Written By Semira°°°

°°°Ahil & Ferah🍂

🌺 ክፍል አስራ ስምንት

Ahil•••ከመስጂድ ተመለስኩ እና ወደ ቤት ስገባ ብዥ ይልብኝ ጀመር ለሊት ፈራህ ጋር ስናወራ አድረን አልተኛንም ድክምክም እያለኝ መኝታ ክፍል ገባሁ ፈራህን ነቅታ አገኛታለሁ ብዬ ነበር እንቅልፍ ወስዷታል ቆይ ምን አይነት ምቀኛ ቢሆን ነው ገና ያንን አንደበቷን ሰምቼ አልጨረስኩም እኮ ልቀሰቅሳት ፈለግኩ ግን አሳዘነቺኝ እና ተውኩት ከአንሶላው እግሯ ወጥቶ ስለነበር ሳለብሳት



አለቺኝ በትንሹ ነቅታ ሳቅ እያለች



አልኳት አሁንም በእንቅልፏ እንዳዘንኩ ነኝ ምን ብትለኝ ጥሩ ነው?





አልኳት ባልገባው ኮስተር ብላ





አልኳት ሃሳቧን እንዳትቀይር ፈርቼ ሳልዋሽ የምነግራችሁ ነገር ቢኖር "ና" ስትለኝ እኔን አልመሰለኝም ነበር ከዛማ አላንገራገርኩም (የኔ የዋህ) ለማንኛውም መለስ ብዬ እንቅልፏን አመሰገንኩት ደግሞ……በቃ ይህን ያህል ሰፍ አትበሉ ቀጣዩ የባል እና የሚስት ወሬ ነበር 😄😄

ከ2 ሳምንታት በኋላ

እንደአጋጣሚ የአንሃንን እና የአያንን የኒካህ ፕሮግራም ነበር እነሱን መብሩክ አልን ጀሚልም ከሃሲነት ጋር ሰርጓል

ከ6 ወራት በኋላ

ባባ ደግሞ ወደ ኮሎምቢያ ሄዷል ሁለተኛ ድርጅት አቃቁሟል አንዳንድ ስብሰባ እየበዛበት ስለሆነ እዛው ለመቀጠል አስቧል የእኛ ድርጅት ደግሞ አላህ ከፈቀደ የጋዜጣ ህትመቱ ባለበት ሆኖ ወደ ቲቪ እና ወደ ራዲዮ የዜና ስርጭት ለመቀየር መንገድ ላይ ነን ግን በዚህ መሃል እያመመኝ ተቸግሬያለሁ ለመኖር ይቀርሃል ከተባልኩት ጊዜ የቀረኝ ከ7 ወራት እያነሰ ነው በፊት ጊዜ(ፈራህን ሳላውቃት በፊት) መሞትን አልፈራም ነበር ብቻ የፈጠረኝን በመልካም ነገር ለመገናኘት የመሞቻዬን እለት የሚጠባበቅ ሰው ነበርኩ አሁን ግን ፈራሁ ፈራህን መለየት ምናለ የሆነ ከሞት ጋር የሚቀርብ ምርጫ ቢኖር? ከምሞት እና ፈራህን ከምለይ ያንን ስቃይ የተሞላበትም ህይወት ቢሆን እመርጥ ነበር ግን ምንድነው የማወራው እላለሁ እየደጋገምኩ በዚህ ሰዓት ከፈጠረኝ ጋር ላለመጣላት ትግል ውስጥ ነኝ መኪና እያሽከረከርኩ ስለነበር እጠነቀቃለሁ

የእጅ ስልኬ ድንገት ጠርቶ ከሃሳቤ አባነነኝ እራሷ ናት የዋኋ ፍቅሬ ፈራህ air paduን ጆሮዬ ላይ ሰካሁት



አልኳት



ሳላስጨርሳት



አልኳት እያዘንኩ



አለቺኝ



አልኳት እና ተሰነባብተን ስልኩ ተዘጋ ያመሸሁት መስጂድ ውስጥ ነበር ሰሞኑን የተዋወኳቸውን ሁለት ሰለምቴዎችን እያስቀራሁ ገና ከቢሮ ስወጣ ያስጠነቀቀቺኝ ቢሆንም አረፈድኩባት ግን ይህን እያሰብኩ ወዲያው ደርሼ ነበር ሙሉ ቤተሰቡ ተገኝቷል ይቅርታ እየጠየቅኩ ገባሁ የምቀይረውን ልብስ ፈራህ አስቀምጣ ጠበቀቺኝ ታውቃላችሁ ከተጋባን ጊዜ ጀምሮ የልዑል ወይም የንጉሥ ህይወት ነው የምኖረው ማለት እችላለሁ ከቁም ሳጥን ልብስ መርጬም ሆነ አውጥቼ አላውቅም ፈራህ ይኸው ብላ ከተፍ ትላለች ምን ላምጣ? ምን ልውሰድ? ምን ጠፋህ ምን ሆንክ? ኧረ ሌላም ሌላም ያ!አላህ ገና እኮ ከእሷ ጋር የጀመርኩትን ህይወት በቅጡ አላጣጣምኩትም አትውሰደኝ እያልኩ እንዳለ



አለቺኝ ከሳሎኑ ተመልሳ መጥታ አሁንስ ልክ ናት በጣም ዘገየሁባቸው ግን ለእኔም ምን እንደሆነ አልገባኝም ፈራህ ሳታስፈቅደኝ ድንገት ተነስታ ዛሬ እራት ይኖረናል በጊዜ ና አለቺኝ መጣሁ ምንድነው ነገሩ አልገባኝም ብቻ ሁሉም ወደ ተሰበሰበበት ሳሎን ሄድኩ እና ከአዝራን እና ከአያን መሃል ተቀመጥኩ



አለቺኝ እጇ ላይ የታሸገ ወረቀት ይታየኛል ስጨርስ



አለቺኝ ሁሉም እያዳመጠ ነው ቀና ብዬ በስስት ቃኘኋት



አለቺኝ በዚህ ሰዓት ምንም ነገር ለማወቅ ጉጉት ውስጥ አይደለሁም እንዳታዝንብኝ ብዬ እንጂ



አልኳት የመጀመሪያው ፈገግታዋ ትንሽ ዳመነ እንድታዝን ሳላደርጋት አልቀረሁም ምን አይነት ሰው ነኝ? የራሴን ስሜት ለመጠበቅ የእሷን ጎዳሁት የታሸገ ፖስታ ነበር ከፈተችው እና እየሰጠቺኝ



ραят// 19 ይቀጥላል •••🫶🫵🫰

❥❥нαйιƒღღ
🫶


°°°Halal Love Story🌹°°°

Written By Semira°°°

°°°Ahil & Ferah🍂

🌺 ክፍል አስራ ሰባት

Ferah••• ያላልኩት የለም ግን ዝም አንድ ሰው እንኳን እሺ ሊለኝ ሊያዳምጠኝ ፈቃደኛ አይደለም ለእኔ ግን ራበኝ ሆዴ ጮኸ ተንጫጫ ማለት እችላለሁ









እየቀለዱብኝ ነው እንዴ? አናደዱኝ እና ወደ ማዕዱ ክፍል ራሴ ብቻዬን ሄድኩ አብሳዮቹ ሰርተው ሄደዋል ቀንሼ መብላት ጀመርኩ እየበላሁ እንዳለ የሆነ የመኪናዎች ድምፅ ከውጪ ይሰማኛል ግን ትኩረት አልሰጠሁትም መብላት ቀጠልኩ ስለምግቡ ባልነግራችሁ ይሻላል በጣም ነው የሚጣፍጠው እሱን እያጣጣምኩ እንዳለ ኑር ወዳለሁበት መጣች









እሺም እምቢም ሳትለኝ ሄደች ኡዘይማ መጣች





እሷም ሄደች የአላህ ምግቡ እንዴት ነው የሚጥመው የጥጋብ እንዲሁ ስበላ ስበላ አቢ መጣ ፈራሁ በጣም ነው የፈራሁት ቆይ ኑር እና ኡዚ ግን ምን ነክቷቸዋል? ያልኳቸውን በሙሉ ለአቢ ነገሩት እንዴ? እንባዬ መጣ



አልኩት እየፈራሁ







ሲለኝ የሚያወራው ቀልድ ይሁን እውነት አልገለፅ አለኝ በደንብ ሳየው ግን ከጀርባው አንድ ሰው አለ አቢን ተከልሎ የመጣ ድምፄን ዝቅ አድርጌ



አልኩት በሹክሹክታ





ብዬ ጮህኩ ስደነግጥ የሚመጣልኝ ቃል ነው ከተከለለበት የአቢ ጀርባ ወጥቶ ሳየው ደንግጬ ፊቴን ወደ መስኮቱ አዞርኩ ጀርባዬን ሰጥቻቸው መለፍለፍ ጀመርኩ ያየሁት አሂልን ነው? አይ…አይደለም ግን አሂል ነበር የኔው አሂል ነበር



ተመልሼ ዞርኩ እራሱ ነው



እስከ መጨረሻው ጀርባዬን ሰጥቻቸው ማልቀስ ጀመርኩ



አቢ ነው ያለኝ ፊቴን ታጥቤ ከተረጋጋሁ በኋላ አሂል



አለኝ ፈገግ እያለ ዛሬ ገና ፈገግ ሲል አየሁት እኔም ፈገግ ስል አቢ



አለን እየተሳሳቅን ውደ ሳሎን ሄድን እና ሁላችንም አውፍ ተባብለን የቀረበውን ምግብ ተመገብን ሳልነግራችሁ የረሳሁት ደግሞ ኒካህ ከመታሰሩ በፊት ሁለት የአቢ ጓዶች መጥተው ነበር ዱዓ ተደርጎልን ኒካህ ታሰረ በሁለተኛው ሳምንት ደግሞ ሰርጋችን እንዲሆን ተቆርጦ ተለያየን አቤት የቀኑ መርዘም አቤት የለሊቱ መርዘም አያልቅም ወደ ድርጅቱ ተመልሷል ግን ከመጋባታችን በፊት አልጀመረም እያለ እያለ ቀኑ ለማለቅ ሶስት ቀናት ሲቀሩት የሰርግ ቀሚስ ለመግዛት ወጣን ኡሚ አብራን ስለነበረች ምንም ማውራት አልቻልንም እንዲሁ ተያይተን ተለያየን

አሁን ያለሁት በሰርጌ እለት ላይ ነው ዙሁር ሷላት ከሰገድን በኋላ መሽራው አሂል መጣ በጥሩ ሁኔታ ተዘጋጅቶ አበቃ እና እንደ ሴት ወግ አቢኧና ኡሚን ኑርን እና ኡዚን እንዲሁም ለእኔ ሁለተኛ አባቴ የሆነውን አዝራን ስለይ ተለቃቀስን ግን የምፅናናው በምን እንደሆነ ታውቃላችሁ? አሁንም እየሄድኩ ያለሁት እንደዚህ አይነት ቤተሰብ ከአላህ ጋር ወደ ምፈጥርበት ቦታ ነው ይህ ቤተሰብ ዳግም በእኔ እና በአሂል ቤት ውስጥ ለመፈጠር የሚያግደው ምንም ነገር የለም የሰርጉን ምሽት ልብሶቻችንን ቀይረን ለሊቱኑ ሙሉ ማለት እችላለሁ ስናወራ ስናወራ አነጋን የባጡን የቆጡን ኮሎምቢያ ስላሳለፋቸው ህይወት እናቱን በትንሹ እንዴት እንደሚያስታውሳት ስናለቅስ ስንስቅ ፈጅር አዛን አለ ሁለታችንም ሰክረናል ማለት ይቀላል አይኖቻችን የጋለ እና ሲበራ የኖረ አምፑል ታውቃላችሁ የዛን ያህል ሲቅበዘበዙ ነበር እንደምንም መስጂድ ስገድ ብዬ
አሂልን ከአዲሱ መኖሪያ ቤታችን አስወጣሁት እኔም ሱና ሳልጨምር የሞት ሞቴን ሰግጄ ተነጥፎ ባልተበላሸው አልጋ ላይ ሄጄ ተኛሁ ቀጣዩ ተግባር የእንቅልፍ ነበር

ραят// 18 ይቀጥላል •••🫶🫵🫰

❥❥нαйιƒღღ🫶


PART = 17&18

Loading ......👍❤🥰

JOIN US ❯❯ нαйιƒ_тùве

❥❥нαйιƒღღ🫶


የዑለሞች ድንቃድንቅ ንግግሮች
───────────
ኢብኑ_ቁዳማህ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : -

«አብዛሃኛዎቹ ሰዎች የጠፉት የሰዎችን ወቀሳ በመፍራትና ሙገሳቸውን በመሻት መሆኑን አውቃለሁ። ሁሉም እንቅስቃሴያቸው የሰዎችን ውደታ በሚገጥም መልኩ ሆነ፤ ሙገሳቸውን መሻትና ወቀሳቸውን መፍራት! ይህ ከአጥፊ ነገሮች መካከል ነው። መታከም ይገባዋል።»

📚 ۞ مختصر منهاج القاصدين【212】۞

🌚መልካም ምሽት 🌗
JOIN US ❯❯ нαйιƒ_тùве

❥❥нαйιƒღღ🫶


°°°Halal Love Story🌹°°°

Written By Semira°°°

°°°Ahil & Ferah🍂

🌺 ክፍል አስራ ስድስት

Ferah•••ዛሬ ከሆስፒታል የምወጣበት ቀን ነው አቢ ያመጣልኝን ልብስ ቀይሬ አብረን ወጣን ስለአሂል ምንም አላለኝም አልተቆጣኝም በቃ እኔም በአሂል መሄድ ባዝንም በሚሄድበት ሁሉ ስኬታማ እንዲሆን በሰገድኩ ቁጥር ዱዓ ማድረጉን አልረሳሁም ከአቢ ውጪ ሊወስደኝ ማንም አልመጣም ወደ ቤት ከደረስኩ በኋላ ግን ተመለሰልኝ ኡዘይማ እና ኑር ከአንሃን ጋር ኡሚንም ጨምሮ ቤቱን ማስዋብ ተያይዘዋል



አልኳቸው በእውነቱ ሶስት ቀን ሆስፒታል ለገባ ሰው ይህ ሁሉ አይገባም እየመጡ ሳሙኝ እና በቃ እንዲሁ ደስ ስላለን ነው አሉኝ እሺ ብዬ በጣም ስለናፈቀኝ ኢልሃንን ከአዝራን ተቀበልኩት እና እሱን ማጫወት ጀመርኩ ኪችን ውስጥ ከዚህ በፊት የማላውቃቸው ሁለት ሴቶች ምግብ ያበስላሉ





አለኝ አያን አያንም ከእኛ ጋር መኖር ጀምሯል ብዙ አዲስ ነገር እያየሁ ነው ገረመኝ ከጠዋቱ 02:10 ላይ ፀጉሬን የምትሰራኝ ሴት መጣች እንዳልጠራኋት ልቤ ያውቃል ስጠይቃት ኡዘይማ እንደጠራቻት ነገረቺኝ ግራ እየገባኝ ወደ መኝታ ክፍሌ ወሰድኳት ተሰራሁ ስጦታ ነው ብሎ አቢ የሆነ ነጭ ቀሚስ ሰጠኝ









አለኝ



ጭራሽ ፀጉራችንን እየተሰራን እንዳለ ኑር አያን እና አንሃን ኒካህ እንደሚያደርጉ ምናምን ነገረቺኝ ደስ አለኝ እንዳልኳችሁ በሶስት ቀን ውስጥ መአት ነገር ነው ያመለጠኝ

🍂 🍂 🍂

Ahil•••ከቁሙ መልበሻ መስታወት ፊት ለፊት እየለበስኩ ነው ባባ እና ጀሚል ግን ከጨረሱ ቆይተዋል እኔን ነው እየጠበቁ ያሉት በእነዚህ ቀናት ውስጥ የሆነውን ሁሉ መናገር አልችልም ፍፁም ህልም ነበር የሚመስለው የመጀመሪያው ነገር የጀሚል እጮኛ ሃሲነት ልትመረቅ ነው ለሰርግ ሲጠብቁ የነበረው የእሷን ትምህርት ነበር በዚህ ጀሚል ተደስቷል ዛሬም ወደ ምንሄድበት ቦታ አብራን ለመሄድ ፈልጋለች አልከለከልናትም ስለጨረስኩ ሁላችንም ተያይዘን ወጣን ጀሚል እና ሃሲነት በአንድ መኪና እኔ እና ባባ ደግሞ በሌላ መኪና ከቀናት በፊት ስለተፈጠረው ነገር ስነግራችሁ

ከሆስፒታሉ ወጥቼ አግዳሚ ወንበር ላይ እንደተቀመጥኩ ሃጂ ሱለይማን መጥተው ከአጠገቤ አረፍ አሉ



አሉኝ በዝምታ የተኛውን የNeeraj ሃይቅ በጥልቀት እየተመለከቱ



አልኳቸው በረጅሙ እየተነፈስኩ



በልቤ"ለምንድነው? እንዳልገባው ሰው የሚጠይቁኝ (በሚል ዘወር ብዬ አየኋቸው) ትላንት ማታ ልጄን አልፈቅድልህም ማለታቸውን ረስተውት ነው?"አልኩኝ ይበልጥ ከፋኝ



አሉኝ ፈገግ ብለው እያዩኝ ፈገግታቸው ከፈራህ ፈገግታ ጋር ይመሳሰላል አሁን ይህን የማስተውልበት ሰዓት አይደለም አልኩ ለራሴ





አላህ ሆይ¡! ምንድነው የላክብኝ ለምን እዚህ ተቀመጥኩ እስከማለት ደረስኩ እሳቸው ጋር ግን አይደለም መበሳጨት ከፈገግታ ውጪ ፊታቸው ላይ አይነበብም ውስጤ ያለውን እንድናገር መንገድ እየሰጡኝ ስለመሰለኝ ለማስረዳት መሞከር ጀመርኩ ነገሮች ይቀየራሉ ብዬ ሳይሆን አለመናገሬ ህመም እንዳይሆን ብዬ ነው ስናገር ፊታቸውን ላለማስተዋል ወደ ሃይቁ ዞርኩ



ዘወር ብዬ ፊታቸውን ለመረዳት ሞከርኩ ከቀድሞው እርጋታቸው ሳይወጡ



አሉኝ



ስላቸው ዞረው አዩኝ እና ፈገግ አሉ እኔ ግን መናገር ቀጠልኩ



ከዚህ በላይ መቀጠል ስላልቻልኩ ለመሄድ ተነሳሁ ዝም አሉኝ ጥቂት ከተራመድኩ በኋላ ግን



አሉኝ ጮክ ብለው ሊያናድዱኝ ነው እንዴ የሚፈልጉት ወንድነቴን ሲፈታተኑት ታወቀኝ እርር አልኩ ቀጥለው



አሉኝ አይ ጆሮዬ አቃጭሎብኝ ነው ብዬ ንግግራቸውን ችላ በማለት ወደ መኪናዬ መራመድ ቀጠልኩ



አሉኝ በድጋሚ አሁን አልቻልኩም ዘወር አልኩና



አልኳቸው



አይኖቻቸውን እያየሁ ፀጥ መልሰው



ግራ አጋቡኝ የፕሮፌሰር ቃል ነው የሚጠቀሙት





አሉኝ ከወንበሩ እየተነሱ ከሩጫ ባልተናነሰ ተራምጄ አቀፍኳቸው እቅፋቸው ውስጥ ገብቼ አለቀስኩ አረጋጉኝ እና ተቀምጠን ብዙ አወራን ግን ስለዚህ ነገር ፈራህ ልታውቅ እንደማይገባ ነገሩኝ ሙፋጃዓ(surprise) ነው በቀጣዩ ቀን ከባባ ጋር ተነጋገሩ

እና ይህን ይመስላል እየሄድን ያለነው ከፈራህ ጋር ኒካህ ለማሰር ነው እሱን ደግሞ አታውቅም የኔ የዋህ ለጥርጣሬ አልተፈጠረችም ይሄኔ ምን ብለው አሳምነዋት ይሁን ??????

💍 💍 💍

ραят// 17 ka 70 like buhala ይቀጥላል •••🫶🫵🫰

❥❥нαйιƒღღ
🫶

20 last posts shown.