Forward from: ገድለ ቅዱሳን
🕊
[ † እንኳን ለአባታችን ታላቁ ቅዱስ በርሱማ ሶርያዊ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †
[ † 🕊 ታላቁ አባ በርሱማ 🕊 † ]
† ታላቁ [THE GREAT ይሉታል] አባ በርሱማ በሶርያ ቤተ ክርስቲያን ምንኩስናና ገዳማዊ ሕይወትን ያስፋፋ አባት ነው::
በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን ምድረ ሶርያን ጨምሮ በብዙ ቦታዎች የቅድስና ሕይወትን ያስፋፋው ቅዱስ በርሱማ ለቤተ ክርስቲያን ምሰሶ ከሆኑላት አበው አንዱ ነው:: እርሱ ከተጋድሎው ብዛት ለ54 ዓመታት ያለ እንቅልፍ ቆይቷል::
በእነዚህ ዘመናትም ግድግዳ ላይ ጠጋ ብሎ ከማረፉ በቀር መቀመጥን እንኩዋ አልመረጠም:: በመዓልትም በሌሊትም በፍቅር አብዝቶ ስለ ራሱና ስለ ሕዝቡ በመጸለዩ የብዙዎቹን ነፍስ ወደ ሕይወት ማርኩዋል::
ገዳማትን ከማስፋፋትና ደቀ መዛሙርትን ከማብዛቱ ባለፈ በስብከተ ወንጌልም የተመሰከረለት አባት ነበር:: በ፬፻፴፩ (431) ፬፻፳፫ (423) ዓ/ም በኤፌሶን በተደረገው የቅዱሳን ጉባኤ ላይ ከተገኙ ሊቃውንትም አንዱ ነው:: በቅድስና ሕይወቱ የተገረመው የቁስጥንጥንያው ንጉሥ [ትንሹ ቴዎዶስዮስ] የንግሥና ቀለበቱን እና ማኅተሙን ሸልሞታል::
ቅዱሱም የዋዛ አልነበረምና በንጉሡ ማኅተም እያተመ "ተፋቀሩ" የሚሉ ብዙ አዋጆችን ወደ መላው ዓለም ልኩዋል:: በ፬፻፶፩ [451] ፬፻፵፫ (443) ዓ/ም በኬልቄዶን ፮፻፴፮ [636] ሰነፍ ዻዻሳት ጉባኤ አድርገው አባ ዲዮርስቆሮስን እንደ ገደሉት ሲሰማም ወደ ቤተ መንግስት ሒዶ ከሃዲዎቹን [መርቅያንና ሚስቱ ብርክልያን] በአደባባይ ዘልፏቸዋል::
ስለ አዘነባቸውም ተቀስፈዋል:: ታላቁ ቅዱስ አባ በርሱማ ፀሐይን ማቆሙን ጨምሮ በርካታ ተአምራትን ሠርቶ በዚህች ቀን ዐርፏል::
† ቸር አምላኩ ከበረከቱ ይክፈለን::
[ † የካቲት ፱ [ 9 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. አባ በርሱማ ሶርያዊ [ለሶርያ መነኮሳት ኁሉ አባት]
፪. አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ [ኢትዮዽያዊ] የመነኮሱበት በዓል
፫. ቅዱስ ዻውሎስ ሶርያዊ [ሰማዕት]
፬. ቅዱስ ዼጥሮስ ሰማዕት
[ † ወርሐዊ በዓላት ]
፩. "318ቱ" ቅዱሳን ሊቃውንት [ርቱዐነ ሃይማኖት ዘኒቅያ]
፪. የብሔረ ብፁዐን ጻድቃን
፫. አባ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ [ኢትዮዽያዊ]
፬. ቅዱስ ዞሲማስ ጻድቅ [ዓለመ ብፁዐንን ያየ አባት]
† " ምን ይዤ ወደ እግዚአብሔር ፊት ልምጣና በልዑል አምላክ ፊት ልስገድ? የሚቃጠለውን መስዋዕትና የአንዱን ዓመት ጥጃ ይዤ በፊቱ ልምጣን ? እግዚአብሔርስ በሺህ አውራ በጐች: ወይስ በእልፍ የዘይት ፈሳሾች ደስ ይለዋልን? . . . ሰው ሆይ! መልካሙን ነግሮሃል:: እግዚአብሔርም ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው? ፍርድን ታደርግ ዘንድ: ምሕረትንም ትወድ ዘንድ: ከአምላክህም ጋር በትሕትና ትሔድ ዘንድ አይደለምን?" † [ሚክ.፮፥፮] (6:6)
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖