Forward from: ቁም ነገረኛ Media
‹‹ ግጭቱ ከፈነዳ ከቀጠናው አልፎ ለአውሮፓ መዘዝ አለው›› ተቋሙ‼️
በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መሀል ግጭት ከተነሳ ለቀጠናው ከባድ መዘዝ እንደሚያመጣ አንድ አለምአቀፍ ተቋም አስጠነቀቀ፡፡ ተቋሙ ግጭቱ ከፈነዳ የኢትዮጵያ የውስጥ ቀውስ ይባባሳል ሲልም ተደምጧል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በድንበር እና በባህር በር ጉዳይ አገራቱ ድርድር እንዲያደርጉ ጠይቋል፡፡
ክሊንግዲል የተባለ የኔዘርላንድ የምርምር ተቋም የኢትዮ ኤርትራን ሰሞንኛ ውጥረት አስመልክቶ ማስጠንቀቂያ አውጥቷል፡፡ ተቋሙ ሁለቱ አገራት ወደ ግጭት እንዳይገቡ የአውሮፓ እና አፍሪካ ህብረትን ጨምሮ ኃያላን አገራት ዲፕሎማሲያዊ ጫና እንዲያደርጉ ጠይቋል፡፡
ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ወደ ግጭት ከገቡ ከባድ ቀውስ ሊፈጠር ይችላል በማለት ተናግሯል፡፡ ተቋሙ የአውሮፓ እና አፍሪካ ህብረት ሁለቱን አገራት ችግራቸውን በሰላም እንዲፈቱ የዲፕሎማሲ ስራ እንዲሰሩም ጥሪ አቅርቧል፡፡ ሁለቱም አገራት ተቃዋሚዎችን ከመርዳት ይታቀቡ ያለም ሲሆን፤ በድንበር እና በባህር በሩ ጉዳይ ንግግር እንዲጀምሩ ጠይቋል፡፡
በየካቲት አጋማሽ በኤርትራ ወታደራዊ ግዳጅ መታወጁን ያስታወሰው ተቋሙ፤ ይህም በአገራቱ መሀል ግጭት ሊቀሰቀስ ይችላል የሚለውን መላምት የሚያጠናክር ነው ብሎታል፡፡፡ ግጭቱ ከተቀሰቀሰ በቀውስ ውስጥ ለሚታመሰው የአፍሪካ ቀንድ ቀጠና ተጨማሪ ራስ ምታት ነው ያለ ሲሆን፤ ከቀጠናው አልፎ ለአውሮፓም መዘዝ ይዞ መምጣቱ አይቀርም ብሏል፡፡
ኤርትራ የአብይ ዐሕመድን የባህር በር ፍላጎት እንደ ስጋት ተመልክታዋለች የሚለው የተቋሙ የማስጠንቀቂያ ሪፖርት፤ ከግብጽ ጋር የምታደርገው ግንኙነትም የዚህ ስጋት ውጤት እንደሆነ አንስቷል፡፡
https://t.me/kumengergna