Forward from: Tesfaab Teshome
ባቢሎን ይወድቃል!
(ተስፋአብ ተሾመ)
* * *
ሞዐመር ጋዳፊ በሐገር ወዳድነት ጉዳይ አይታመማም። ነገር ግን ለክርክር በማይቀርብ ሁኔታ አምባገነን ነው! ግትር አምባገነን!
ነፃነት ከሰው ልጆች መሰረታዊ ባህሪ መካከል አንዱ ነው። ያለነፃነት መኖርን የሚወድ የለም።ባልሳሳት ጆርጅ ኦርዊል መሰለኝ "ሰዎች ነፃነት አፍቃሪ ነን" ይላል።
የጋዳፊ ልጅ ሰይ.ፍ አሊሰላም የአባቱን አምባገነናዊ አካሄድ አልወደድምና ጥቂት የነፃነት አየር በሐገሩ እንዲነፍስ ፈለገ፤ አባቱ ለዴሞክራሲ የዘጋውን በር እንዲከፍት ጠየቀ። ሰሚ ግን አልነበረም። ዜጎች 'የዴሞክራሲ ያለ' አሉ። ተቃዋሚዎች ወደ አደባባይ ወጡ። ይሄኔ ጋዳፊ ዴሞክራሲ ለጠየቁቱ ጥይት ሰጣቸው፥ ነፃነት የለመኑትን ወደ ወሂኒ ወረወረ። ተቃዋሚዎችን 'የከተማ አይጦች' ብሎ ሰደበ። መገነኛ ብዙሃንን 'የምዕራቡ አለም ተላላኪዎች' ብሎ አኮሰሰ። ግን አልቆየም። ነገር ተገለበጠ በተሳለቀባቸው ዜጎች እጅ ወደቀ። አምባገነኑ ጋዳፊ የውሻ ሞትን ሞተ!
ከሞቱ በኋላ ሊቢያ ለታላቅ ትርምስ ተዳረገች። በውድቀቱ ሐገርን ይዞ ወደቀ!
ሃይለስላሴ የዴሞክራሲ ጥያቄ ለጠየቁት ሁሉ በራቸው ዝግ ነበር። ብርሃኑ ድንቄ የነቀዘ ስርኣታቸውን ሊያሳቸው ሞክሮ መገፋትን አተረፈ። በስደት አለም የባይተዋር ኑሮ ለመኖር ተገደደ። ጃንሆይን ለማንቃት የሞከሩ ሁሉ አድማጭን አላገኙም። ሰውዬው በግትረነታቸው ፀኑ።
የመጨረሻዋ ቀን መጣች። አዛውንቱ ንጉስ ለውርደት ተዳረጉ።
ጓድ መንግስቱ ሰሚ ጆሮ ከሌላቸው አምባገነኖች መሓከል አንዱ ናቸው። ተቃዋሚዎቻቸውን በአደባባይ ረሽነ.ው 'የፍየል ወጠጤ' ብለው የሚሳለቁ ጨካኝ አምባገነን ናቸው። በብዕር የተቿቸውን ወደ መቃብር ለመሸኘት አላመነቱም። ዙፋናቸውን በደም መስዋዕት ሲጠብቁ ከከረሙ በኋላ ጀምበር አቆለቆለች። ይሐኔ መሸሽ ምርጫ ሆነ፤ 'ቆራጡ' መሪ ፈረጠጡ!
ኢህአዴግ የምርጫ ተወዳዳሪዎችን ወደ እስር ቤት የሚወረውር ፥ ተቃዋሚዎችን የሚያኮላሽ ፥ ሐገር ለመጠበቅ የተቋቋመን የደህንነት ተቋም ህዝብን ለመሰለል የሚጠቀም አረ.መኔ ቡድን ነበር። ከነ ትምክህቱ ሲንጎላጅ ጊዜ ከዳው፥ በናቃቸው ተረታ፥ አንዳንዶቹ ለውርደት ሞት ተዳረጉ።
ድንቁ.ርና የአምባገነኖች መታወቂያ ነው። ከጥፋታቸው አይታረሙም፥ ማድመጥ ብሎ ነገር አልፈጠረባቸውም። በደህንነት ተቋሞች እና በጦር መሳሪያ ተማምነው ዜጎችን በማሸማቀቅ ዝንታለም በመንበራቸው የሚቆዩ ይመስላቸዋል። ህዝብን ይንቃሉ። ይህ የወቅቱ ገዢ ብልፅግና አመል ነው።
ከታሪክ የተማርነው ታላቅ እውነት አለ፥ ባቢሎን ይወድቃል !
@Tfanos