ግቦችን እርሳቸውና በሂደቱ ላይ አተኩር
የተለመደው አረዳድ በሕይወታችን ውስጥ የምንፈልጋቸውን ነገሮች ለማሳካት፣ ብዙ ጭንቀት የሌለበት ዘና ያለ ሕይወትን ለመኖር እና ውጤታማ ሕይወትን ለመምራት ቁልፉ ነገር ሊተገበሩ የሚችሉ ግቦችን ማስቀመጥ ነው” የሚለው ነው፡፡
እኔም ለብዙ ዓመታት ልማዶችን የምቃኝበት መንገድ ይህ ነበር። እያንዳንዳቸው ሊደረስባቸው የሚቻሉ ግቦች ናቸው፡፡ ለምሳሌ በትምሀርት ቤት ውስጥ ማምጣት ስላለብኝ ውጤት ግብ አስቀምጣለሁ። በቢዝነሱ ውስጥ ላገኘው ስለምፈልገው ትርፍ፣ በጂም ቤት ላነሳው ስለምፈልገው ክብደት ወዘተም እንደዚያው፡፡ በተወሰኑት ውጤታማ መሆን የቻልኩ ቢሆንም በአብዛኞቹ ግን አልተሳካልኝም፡፡ በሂደት ያገኘሁት ውጤት ካስቀመጥኩት ግብ ጋር ያለው ግንኙነት ውስን መሆኑን ተረዳሁ፡ ከዚያ ይልቅ ያመጣኋቸውን ውጤቶች ጨምሮ ሁሉም ነገሮች ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው ከሂደቱ (system) ጋር እንደሆነ አወቅሁ፡፡
በስርዓታዊ ሂደት (system) እና በግቦች (goals) መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው? ይህንን ልዩነት ለመጀመሪያ ጊዜ የተማርኩት ከ “ዲልበርት ኮሚክ” ጀርባ ካለው ካርቶኒስት ከስኮት አዳምስ ነው፡፡ ግቦች ልታሳካቸው የምትፈልጋቸው ውጤቶች ናቸው፡፡ ስርዓታዊ ሂደቱ ግን ወደእነዚህ ውጤቶች የሚመራህ ሂደት ነው፡፡
👉አሰልጣኝ ከሆንክ ምናልባት ግብህ ውድድሩን ማሸነፍ ሊሆን ይችላል። ሂደትህ ደግሞ ተጨዋቾችን የምትመለምልበት መንገድ፣ ልምምድ የምታሰራበት መንገድ፣ ምክትል አሰልጣኞችህን የምትጠቀምበት መንገድ ወዘተ... ናቸው፡፡
👉ሥራ ፈጣሪ ከሆንክ ግብህ ባለ ብዙ ሚሊዮን ዶላር ቢዝነስ መገንባት ሊሆን ይችላል። የምርትን ሀሳቦች የምትፈትንበት መንገድ፣ ሰራተኞችን የምትቀጥርበት ሁኔታ፣ የማርኬቲንግ ስራውን የምትመራበት መንገድ ወዘተ ደግሞ የሂደቱ አካል ይሆናሉ፡፡
👉ሙዚቀኛ ከሆንክ ደግሞ ግብህ አዲስ ሙዚቃ መስራት ሊሆን ይችላል፡፡ የምትሰራቸው _ ልምምዶች ብዛት፣ አስተያየቶችንና ምክሮችን ተቀብለህ የምትተገብርበት ሁኔታ ወዘተ... ግን ሂደቶቹ ናቸው፡፡
አንድ ጥያቄ ደግሞ እናንሳ፡፡ ግቦችህን ሙሉ በሙሉ በመተው ሂደቱ ላይ ብቻ ብታተኩር ውጤታማ መሆን ትችላለህ? ለምሳሌ አንተ የቅርጫት ኳስ አሰልጣኝ ብትሆንና ውድድሩን የማሸነፍ ግብህን ሙሉ በሙሉ ረስተህ ቡድንህ በየቀኑ የሚሰራው ተግባራዊ ሥራ ላይ ብቻ ብታተኩር ውጤት ልታመጣ ትችላለህ?
እኔ ልታመጣ እንደምትችል አስባለሁ።
የተሻለ ውጤት ይዞ ማጠናቀቅ ነው፡፡ የጨዋታ ጊዜዎችን ማሳለፍ ግን የሚያበቃው እውነተኛው መንገድ በየትኛውም ስፖርት ውስጥ ግቡ የውጤት ሰንጠረዥን እያዩ ሙሉ ትርጉም የለሽ ነው፡፡ ለውጤታማነት በየቀኑ ለመሻሻል መጣርና ልዩነት ማሳየት ነው፡፡ የ3 ጊዜ የሱፐር ቦል አሸናፊው ቢል ዋሽ እንዳለው “ውጤት ለራሱ ይጨነቃል፡፡” ለሌሎች የሕይወት ዘርፎችም እውነታው ይሄው ነው፡፡ የተሻለ ውጤት ማምጣት ከፈለግክ ግቦችን መደርደርን ችላ በልና ሂደቱ ላይ አተኩር፡፡
ምን ማለቴ ነው? ግቦች ምንም ጥቅም የላቸውም እያልኩ ነው? በፍፁም! ግቦች አቅጣጫን ለማስቀመጥ በጣም ጠቃሚ ነገሮች ናቸው፡፡
ለውጥ ለማምጣት በጣም የሚጠቅመን ግን ሂደት ነው፡፡ በቂ ስርዓት ሳትቀርዕ ያስቀመጥካቸው ግቦች ላይ ብቻ በማውጠንጠን ጊዜ ማሳለፍ ብዙ ችግሮች ይፈጥራል፡፡
ለምሳሌ...
ይቀጥላል...
Atomic habit
ጄምስ ኬለር
የስብዕና ልህቀት
@Human_Intelligence