TGStat
TGStat
Type to search
Advanced channel search
  • flag English
    Site language
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Sign In
  • Catalog
    Channels and groups catalog Search for channels
    Add a channel/group
  • Ratings
    Rating of channels Rating of groups Posts rating
    Ratings of brands and people
  • Analytics
  • Search by posts
  • Telegram monitoring
የስብዕና ልህቀት

13 Dec 2024, 19:50

Open in Telegram Share Report

#3 ግቦች ደስተኛነትን ይገድባሉ

ከየትኛውም ግብ ጀርባ ያለው ድብቅ ስሌት “አንድ ጊዜ ግቤን ካሳካሁ ደስተኛ እሆናለሁ” የሚል ነው፡፡ ግቦችን የማስቀደም አስተሳሰብ መሰረታዊ ችግር ሌላ ግብ እስክታሳካ ድረስ ደስታን አሽገህ እንድታስቀምጥ የሚያደርግህ መሆኑ ነው፡፡ በዚህ ወጥመድ ብዙ ጊዜ ተደናቅፌያለሁ፡፡ ለዓመታት ደስታ ማለት ለእኔ ወደፊት የማጣጥመው ገና ያልመጣ በረከት ነበር፡፡

ከዚህ ውጪም ግቦች የ “ወይም” (either or) ግጭትን ይፈጥራሉ፡፡ ወይ ግቦችህን ታሳካና ውጤታማ ትሆናለህ ወይ ደግሞ ግቦችህን ማሳካት ያቅትህና በመከፋት ውስጥ ትኖራለህ፡፡ በዚህ መንገድ ደስታ አጥብቦ በሚያይ ጠባብ አረዳድ አዕምሮህን ለሁለት ትከፍላለህ፡፡ ይህ የተሳሳተ አተያይ ነው፡፡ የሕይወትህ ጉዞ የሚጠበቀውን ያህል በትክክለኛው መንገድ የመሄድ እድሉ ዝቅተኛ ነው፡፡ ስለሆነም በእውነታው ብዙ የስኬታማነት መንገዶች እያሉ እርካታን ከአንድ ሁኔታ ጋር ብቻ ማስተሳሰር ተገቢ አይደለም፡፡

ሂደትን የማስቀደም አስተሳሰብ ማርከሻውን ይሰጠናል፡፡ ከውጤቱ ይልቅ በሂደቱ ስትወሰድ ደስተኛ ለመሆን የምትጠብቀው ቀን አይኖርም፡፡ ሂደትህ በአግባቡ እየሄደ እንደሆነ ባየህ በየትኛውም ጊዜ ደስተኛ መሆን ትችላለህ፡፡ ሂደት ደግሞ በአንድ መንገድ ሳይሆን በብዙ አማራጭ መንገዶች ውጤታማ መሆን ይችላል፡፡

#4 ግቦች ከረዥም ጊዜ እድገት ጋር አይጣጣሙም

ግቦችን የማስቀደም አስተሳሰብ “የአሳክቻለሁ” ስሜት (Yo Yo Effect) ይፈጥራል፡፡ ብዙ ሯጮች ለወራት ጠንክረው ይሰራሉ፡፡ ልክ ድል አድርገው ከገቡ በኋላ ግን ልምምድ መስራት ያቆማሉ፡፡ ከዚያ በኋላ ውድድሩ ሊያነሳሳቸው አይችልም፡፡ ድካምህ ሁሉ አንድን ግብ ያማተረ ከሆነ እሱን ካሳካህ በኋላ ሊያነሳሳህ የሚችል ምን ቀሪ ነገር ይኖራል? ለዚህ ነው ብዙ ሰዎች ግባቸውን ካሳኩ በኋላ ወደቀደሙ መጥፎ ልማዶቻቸው ሲመለሱ የምናየው፡፡

ግብን የማስቀመጥ ጥቅሙ ውድድርን ለማሸነፍ ነው፡፡ ሂደትን የመገንባት ጥቅም ግን ጨዋታውን እየተጫወቱ ለመቀጠል ነው። እውነተኛ የረዥም ጊዜ ሀሳብ ግቦች ላይ የተመሰረተ አይደለም፡፡ ሂደት ማቆሚያ ስለሌላቸው መሻሻሎችና ቀጣይነት ስላላቸው ማሻሻያዎች ነው፡፡ እድገትህን የሚወስነው ዋናው ነገርም የአንተ ቁርጠኝነት ነው፡፡


@Human_Intelligence

10.4k 0 26 50
Catalog
Channels and groups catalog Channels compilations Search for channels Add a channel/group
Ratings
Rating of Telegram channels Rating of Telegram groups Posts rating Ratings of brands and people
API
API statistics Search API of posts API Callback
Our channels
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
Read
Blog Telegram Research 2019 Telegram Research 2021 Telegram Research 2023
Contacts
Support Email Jobs
Miscellaneous
Terms and conditions Privacy policy Public offer
Our bots
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot