ቁማር በኢስላም የተከለከለ ነው። ሐራም የሚሆነው ህፃናት ሲፈፅሙት ወይም በቀጥታ በስሙ ሲቀርብ ብቻ አይደለም። ስሙ ቢቀያየርም ቁማር ሐራም ነው። ሎተሪ ቁማር ነው። አንድ የሎተሪ "እድለኛ" በ10 ብር ትኬት የ 1,000,000 ብር የሚወስደው ሰርቶ አትርፎ ሳይሆን ከሱው መሰል ተስፈኞች የለቀሙትን ነው አሳልፈው የሚሰጡት። ኢንሹራንሱም ተቀራራቢ አሰራር ነው የሚከተለው። አንድ ባለ መኪና ኢንሹራንስ በገባ በወሩ አደጋ ገጥሞት በኢንሹራንስ ድርጅቱ የ500,000 ብር ጥገና ቢያስደርግ ከሱው ብጤ ተስፈኞች የለቀሙትን ነው ወጭ የሚያደርጉት። ሌላኛው እድሜ ልኩን ሲከፍል ኖሮ ምንም ነገር ካልገጠመው አምስት ሳንቲም ሳይጠቀም ይቀራል። የጤና መድህኑም እንዲሁ ነው።
ባይሆን ኢንሹራንስም ይሁን ጤና መድህን ላይ እንዲገባ የተገደደ ሰው ወንጀል የለበትም። ወንጀሉን አስገዳጁ አካል ይሸከመዋል።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
ባይሆን ኢንሹራንስም ይሁን ጤና መድህን ላይ እንዲገባ የተገደደ ሰው ወንጀል የለበትም። ወንጀሉን አስገዳጁ አካል ይሸከመዋል።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor