#የምላስ_ወለምታ
ሶስት ሰዎች የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው ውሳኔው ተግባራዊ ሊሆን ህዝብ በተሰበሰበበት ሜዳ ከፍ ካለው ቦታ ላይ ተደረደሩ። አሊም፣ የህግ ጠበቃና የፊዚክስ ሊቅ ናቸው።
ገመዱ ተዘጋጅቶ አሊሙን ወደ ፊት አስጠጉት። አንገቱን ከገመዱ በታቸ አጠለቁት። ለመናገር ለምትፈልገው የመጨረሻ ቃል ካለ ተናገር ተባለ።
አላህ አላህ....የሚያድነኝ እርሱ ብቻ ነው" ሲል ተናገረ። ገመዱ አንገቱ ላይ እንደጠበቀ አልሸመቀቅ አለ። ሕዝቡ ተገረመ። የአላህን ስም ጠርቷልና ገመዱን ፍቱለት ተብሎ ተለቀቀ። ነፍሱንም በአላህ ስም ታደገ።
የሕግ ባለሙያው ተራ ደረሰ። አንገቱ ላይ ገመድ ጠለቀ። ለእርሱም የምትናገረው የመጨረሻ ቃል ካለ ተናገር ተባለ። እንዲህም አለ አንደ ኡስታዙ ከአላህ ጋር አልተዋወቅም ግን ፍትሕ እንደሚያድነኝ በሚገባ አውቃለሁ። ፍትሕ ፍትሕ ሲል ጮኸ። ገመዱ በአንገቱ ውስጥ እንደጠለቀ አልሸመቀቅ አለ። ጠበቃውን ፍቱት ስሰ ፍትሕ ተሟግቷልና መሰቀያ ገመዱ እንኳ ነፍሱን ለመንጠቅ አልደፈረችም ተባለ። ጠበቃውም በፍትሕ ስም ነፍሱን አዳነ።
የፊዚክስ ሊቁ ተራ ደረሰ። እርሱም ተጠየቀ መናገር የምትፈልገው የመጨረሻ ቃል አለን? ተባለ።
"እኔ አላህን አንደ ኡስታዙ አላውቀውም። እንደ ጠበቃውም ስለ ፍትሕ አልለፈልፍም። ግን መስቀያ ገመዱ እስካሁን አንገታቸው ላይ ጠልቆ ያልተሸመቀቀው አናቱ ላይ ያለዉ ቋጠሮ ስለጠበቀ ነው" አለ። ገመዱን ሲመለከቱት በትክክል ቋጠሮው በመጥበቁ ምክንያት ነው ያልተሸመቀቀው። ቋጠሮውን አስተካክለው የፊዚክስ ሊቁ አንገት ላይ ገመዱን ሸምቅቀው ገደሉት።
አንዳንዴ እውነታውን እንኳ እያወቅከ ምላስህን መያዝ ይኖርብሀል። ሞኝ መሆን ብልጠት የሚሆንባቸው በርካታ ቦታዎች አሉና አፍህን በመዳፍህ ላይ አድርገህ ዝም በል።
join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group