ዒሳ ወፍ ፈጥሯልን?
በቴሌግራም ሰፈር ስዘዋወር "ኢሳ ወፍ ፈጥሯልን?" በሚል ርእስ የተጻፈች መጣጥፍ አየሁ፡፡ የጽሑፉ ዓላማ ኢሳን እንደ ኢየሱስ የሚቆጥሩና የእርሱን አምላክነት በቁርአን ለማረጋገጥ የሚዳዳቸው ወገኖች ለሚያነሱት ሙግት ምላሽ ለመስጠት ታስቦ ይመስላል፡፡
ሱረቱል አሊ-ኢምራን 3 ፥49
ወደ እስራኤልም ልጆች መልክተኛ ያደርገዋል፡፡ (ይላልም)፡- «እኔ ከጌታዬ ዘንድ በተዓምር ወደ እናንተ መጣሁ፡፡ እኔ ለናንተ ከጭቃ እንደ ወፍ ቅርፅ እፈጥራለሁ፡፡ በርሱም እተነፍስበታለሁ፡፡ በአላህም ፈቃድ ወፍ ይኾናል፡፡ በአላህም ፈቃድ ዕውር ኾኖ የተወለደን፣ ለምጸኛንም አድናለሁ፡፡ ሙታንንም አስነሳለሁ፡፡ የምትበሉትንና በቤታችሁ የምታደልቡትንም ሁሉ እነግራችኋለሁ፡፡ የምታምኑ እንደኾናችሁ ለእናንተ በዚህ ውስጥ በእርግጥ ተዓምር አለበት፡፡»
ጸሐፊው ቃላትን በመሰነጣጠቅ ኢሳ እንዳልፈጠረና ከጭቃ በተሠራችው የወፍ ቅርጽ ላይ እፍ ሲልባት አላህ ወፍ እንድትሆን እንዳደረገለት ማሳየትና የሞጋቾቹን ሙግት ስሁት ለማድረግ ተጣጥሯል፡፡ የፈጣሪውን ባለቤትነት ለአላህ ሰጥቷል፡፡ በኢሳና በሙሳ የተሠሩ ተአምራቶችን ለንጽጽር ተጠቅሟል፡፡ ሙግቱ ለሌላ ሙግት ጋባዥና የጠራ ባይሆንም እርሱን ይቆይ፡፡ በተጠቀሰው የቁርአን ታሪክ ላይ ያለው ጥያቄ እንደተባለው ፈጥሯል አልፈጠረም የሚለው ሳይሆን መለኮታዊ መገለጥነቱ ላይ ነው፡፡ መለኮታዊ መገለጥ መሆኑ ላይ የሚነሳውን ጥያቄ ፈች ጽሑፍ ሆኖ ግን አላገኘሁትም፡፡
በአጭሩ ቁርአን መለኮታዊ መገለጥ አይደለም፡፡ ለዚህ የምዕራፍ ስያሜ መለኮታዊ መገለጥ አለመሆኑን ገላጩ ብርሃን ወገግ በማድረግ እዚህ ነኝ ማለት ይጀምራል፡፡ በሁለተኛ ደረጃ 49 ኛው አንቀጽ እንደ ቀትር ፀሐይ ነገሩን ያደምቀዋል፡፡ ነቢዩ ሙሐመድ ኢሳን በተመለከተ ተገለጠልኝ ያሉትንና ያስተላለፉትን አንዱንም በመለኮታዊ መገለጥ አለመቀበላቸው በዚህ ይጋለጣል፡፡ በእርሳቸው ዘመን የነበሩ ሞጋቾቻቸው ይሉት እንደ ነበር በጀሯቼው ይነበብላቸው ከነበረው የወሰዱትን ነው ተገለጠልኝ ብለው በተለያየ ምክንያት ይከተላቸው ለነበረው ሕዝብ ያስተጋቡ የነበረው፡፡ ቁርአን ጀሯቼው ሞልቶ ሲፈስ የተከተበ ነው ማለት ነው፡፡
ሱረቱል አል-ፉርቃን 25 ፡ 4-5
እነዚያም የካዱት ይህ (ቁርኣን ሙሐመድ) የቀጠፈው በእርሱም ላይ ሌሎች ሕዝቦች ያገዙት የኾነ ውሸት እንጂ ሌላ አይደለም አሉ፡፡ በእርግጥም በደልንና እብለትን ሠሩ፡፡ አሉም «የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች ናት፡፡ አስጻፋት፡፡ እርሷም በእርሱ ላይ ጧትና ማታ ትነበብለታለች፡፡»
እንዲህ ከሆነ ከየትኛው መጽሐፍ ላይ እንደ ተነበበላቼውና እነማን እንዳነበቡላቸው ማስረጃህን አምጣው ትሉኝ ይሆናል፡፡ አዎን መካ ውስጥና መዲና በነቢዩ ሙሐመድ ዙሪያና እርሳቸው ጋር ይገናኙ የነበሩ ክርስቲያን የሚባሉ ሰዎች እንደ ነበሩ ቁርአን ይተርካል፡፡ ለዚህ የዚህኛውን የቁርአን አንቀጽ ተፍሲሮች መመርመር ያቻላል፡-
ሱረቱል አን-ነህል 16 ፡ 103
እነርሱም «እርሱን (ቁርኣንን) የሚያስተምረው ሰው ብቻ ነው» ማለታቸውን በእርግጥ እናውቃለን፡፡ የዚያ ወደርሱ የሚያስጠጉበት ሰው ቋንቋ ዐጀም ነው፡፡ ይህ (ቁርአን) ግን ግልጽ ዐረብኛ ቋንቋ ነው፡፡
ከየትኛው መጽሐፍ ለሚለው ደግሞ የሚከተለውን የአዲስ ኪዳን አዋልድ መጽሐፍ የሆነውን የቶማስ ወንጌልን ድርሳን ላስነብባችሁ፡-
Gospel of Infancy Thomas 2 : 4-7
'But when a Jew saw what Jesus was doing while playing on the sabbath day, he immediately went off and told Joseph, Jesus' father: "See here, your boy is at the ford and "has taken mud and fashioned twelve birds with it," and so has violated the sabbath." So, Joseph went there, and as soon as he spotted him, he shouted, "Why are you doing what's not permitted on the sabbath?" "'But Jesus simply clapped his hands and shouted to the sparrows: "Be off, flyaway, and remember me, you who are now alive!" And the sparrows took off and flew away noisily." 'The Jews watched with amazement, then left the scene to report to their leaders what they had seen Jesus doing.
ታዲያ የትኛው ነው መለኮታዊ መገለጡ? ነቢዩ ሙሐመድ ከጠገበው ጀሯቼው የተናገሩት እንጂ ከመለኮታዊ መገለጥ የተቀበሉት አይደለም፡፡ እና ውድ ሙስሊም እህቶችና ወንድሞች ምን እንዳመናችሁ፣ ምን ላይ እንደቆማችሁ፣ ወዴት እየሔዳችሁ እንዳላችሁ አሁን ቆም ብላችሁ የምታስቡበት ሰዓት አይመስላችሁም? አምላኬ የውስጥ ዐይናችሁን ይክፈተው!