ኢትዮጵያዊው ወጣት ትንሳኤ አለማየሁ የ 2023 IAF young space leaders (ወጣት የሕዋ መሪዎች) መካከል አንዱ ሁኖ ተመረጠ
IAF young space leaders በስራ ዘመናቸው ለጠፈር ምርምሮች አስተዋፅዖ ለሚያደርጉ ወጣት የሕዋ መሪዎች እውቅና የሚሰጥበት መርሃ ግብር ነው።
ትንሳኤ ዘርፉን መቀላቀል ለሚሹ ተማሪዎች እና ወጣት ባለሙያዎች የመነሳሳት ስሜት የሚፈጠር እና በአርአያነት ምልክት ሆኖ ቆሟል ተብሎለታል።
ትንሣኤ በዘርፉ ላበረከታቸው ልዩ አስተዋፅዖዎች እ.ኤ.አ. በ2022 ከዓለም አቀፉ የጠፈር ተመራማሪዎች ፌደሬሽን (አይኤኤፍ) የተበረከተውን ተስፋ የተጣለባቸው ስፔስ መሪዎች ሽልማትን፣ ከ30 አመት በታች የአፍሪካ ስፔስ ኢንዱስትሪ ሽልማት - በ2021 ከስፔስ ኢን አፍሪካ እና ከSGAC የግሎባል ግራንት ፕሮግራም ሽልማትን፣ በ2019 ደግሞ ከኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ የወጣት ሕዋ አምባሳደርን ጨምሮ ሌሎች ብዙ ሽልማቶችን እና እውቅናዎችን ሲያገኝ ቆይቷል።
ትንሣኤ ዓለማየሁ አሊ በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የሜካኒካል ኢንጂነሪንግ በላቀ ውጤት የተመረቀ ሲሆን በአፍሪካ ስፔስ ሳይንስ እና ኢንጂነሪንግ እውቅናን እያካበተ ሰው ነው።
በአሁኑ ጊዜ በበጎ ፈቃደኝነት ለስፔስ ጀነሬሽን አማካሪ ምክር ቤት (SGAC) የአፍሪካ አስተባባሪ በመሆን እያገለገለ የሚገኝ ሲሆን ትንሣኤ ቀጣዩን የጠፈር ባለሙያዎችን በማብቃት ወሳኝ ሚና ይጫወታል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት ወጣት ሆኗል። በSGAC ካለው የሥራ ድርሻ በተጨማሪ በቅርቡ CubeSpace የተባለ በዓለም መሪ የሳተላይት ADCS ማምረቻ ድርጅትን በመቀላቀል የሽያጭ መሐንዲስነት እየሰራ ሲሆን፣ የድርጅቱን የንግድ እያሳደገ ይገኛል ተብሎለታል።
https://www.iafastro.org/news/the-iaf-is-proud-to-introduce-the-2023-iaf-young-space-leaders.html