የ16ኛው ክፍለ ዘመን ተሐድሶው ሲጀምር
በኦክቶበር 31፣ 1517 ዓመተ እግዚ አንድ ብዙም የማይታወቅ መነኩሴ በአንዲት ትንሽ የጀርመን ዩኒቨርስቲ ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስ ፕሮፌሰር የነበረ ሰው በዩኒቨርስቲው ቅጥር ውስጥ በሚገኘው የቤተ ክርስትያን በሮች ላይ የተወሰኑ አናቅጽት የያዙ ወረቀቶችን ለጠፈ። እነዚያን ወረቀቶች በቤተ ክርስትያን አደባባይ ላይ የለጠፈበት ምክንያት የቤተ ክርስትያኑ አደባባዩ ለዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ እንደ ማስታወቅያ ሰሌዳ ያገለግል ስለነበር ነው።
በለጠፈው ወረቀት ውስጥ 95 አናቅጽት (Thesis)ወይም አረፍተ ነገሮች ሰፍረዋል። የአናቅጽቱ ዋነኛ ትኩረትም ''የኃጢአት ይቅርታ ሰነድ'' ' indulgence የመሸጥ ልምምድ ከጳጳሱ ፍቃድ የተሰጠውና ሰው 'ፑርጋቶሪ'/Purgatory (ነፍስ ወደ ገነትም ሆነ ሲኦል ከመውረዷ በፊት የምትሆንበት ስፍራ) ውስጥ በምድር በሕይወት እያለ ስላጠፋው ስለሃጢያቱ የሚቆይበትን ጊዜ (ወደ መንግስተ ሰማይ ከመግባቱ በፊት) በሚገዛው 'ኢንደልጀንስ' መቀነስ ይችል ስለነበረ ነው። ይህ 'ኢንደንጀልስ' በወረቀት የሰፈረና የቤተ ክርስትያንን ይሁንታ አግኝቶ መግዛት ለቻለ ሁሉ የቀረበ ነበር። ህዝቡም ኢንደልጀንሱን ይገዛ ዘንድ 'ቅቤ አቅልጥ' የሆኑ አሻሻጮች ነበሩ። ህዝቡ ለራሱ፣ ለዘመዱና ለወዳጁ ይገዛ ነበር፣ ለሞቱት እንኳን ሳይቀር።
ሉተር 95 አናቅጽቱን ጽፎ ሲለጥፋቸው ዩኒቨርስቲ ውስጥ ባሉት ፕሮፌሰሮች መሃል ውይይት እንዲፈጥር በማሰብ ነበር። ነገር ግን ዘጠና አምስቱ አናቅጽት ከዊተንበርግ ፕሮፌሰሮች ከባቢ በዘለለ በመላው የጀርመን ግዛቶችና በጠቅላላው የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ዘንድ ታላቅ ሁካታን ለመፍጠር በቃ። በአጭር ጊዜ ውስጥም ብዙ ህዝብ የዚህን መነኩሴ ስም ማወቅ ጀመረ፣ በዊተንበርግ ዩኒቨርስቲ የሥነ መለኮት ዶክተሩን ማርቲን ሉተርን።
ህዝብን በማወክና ባለመታዘዝ ቤተክርስትያን ከሰሰቸው፣ በጀርመን ንጉስ ፊትም ራሱን እንዲከላከልና ያደረገው ሃሰት መሆኑን አውቆ እንዲያስወግድ ታዘዘ። ያደረገው ስህተት መሆኑን ባለመቀበሉ ምክንያት የውጤቱን ስሜት 500 ዐመታትን ተሻግሮ ዛሬ እኛም ይሰማናል።
እነዚህ የተሐድሶው ማኮብኮብያ የነበሩት የተወሰኑ የወረቀት ቁርጥራጮች እንዴት ይህንን የሚያህል ትኩረትና ያልተጠበቀ አስደንጋጭ ውጤት አመጣ ብሎ ማሰብ አስፈላጊ ነው። በተመሳሳይም የማርቲን ሉተር አስተምህሮ ከእሱ በፊት ከተነሱት ከነፒተር ዋልዶ፣ ጆን ዊክሊፍና ጆን ሁስን ከመሳሰሉ ተመሳሳይ አስተምህሮ ከሚከተሉት በላይ ገኖ የወጣበትን ምክንያት መጠየቅ ደግ ሳይሆን አይቀርም። ከሉተር መቶ አመት በፊት የነበረው ጆን ሁስ በተቃውሞ ምክንያት በእሳት ተቃጥሎ እየሞተ በነበረባት ሰዓት "በቀጣይ 100 አመት ውስጥ እግዚአብሔር አንድ ሰው አስነስቶ የማይቆም ተሐድሶን ያቀጣጥላል" ያለው ትንቢት ያለምክንያት አልነበረም።
ከላይ ላነሳናቸው ጥያቄዎች መልሱ የሚገኘው በወቅቱ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያንና ምዕራብ አውሮጳ የነበሩበት ነባራዊ ሁኔታ ውስጥ ነው። በ15ኛው ክፍለ ዘመን የተከወኑ ሁነቶች ተሐድሶ እውን እንዲሆን በር ከፋች ነበሩ። ሶስት መሠረታዊ ነገሮች ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል።
የመጀመሪው የእውቀት ከቤተ ክርስትያን ቁጥጥር ውጪ መሆን ነው። የእውቀር መስፋፋት ቤተክርስቲያን በእውቀትና ትምህርት ላይ የነበራት ሙሉ ተጽእኖ እንድትነጠቅ አድርጓታል። በዚያ ላይ የማተሚያ ማሽን መገኘቱ እውቀት በቀላሉ ተደራሽ እንዲሆን አስተዋጽኦው ከፍ ያለ ነበር። በርግጥ ተሐድሶው የተቀጣጠለው በታተሙ ወረቀቶች ነበር።
ሁለተኛው የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊዉ የሃይል ሚዛን ለውጥ ማድረጉ ነው። አውሮጳ የተለያዮ የንግድ መስመሮችን ያገኘችበትና ሃብት በብዛት ወደ መንግስታት የገባበት ወቅት ነበር። መንግስታት ከሮም ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በላይ በለጠጋ በመሆናቸውና ሃብታቸውን ማጋራት ባለመፈለጋች ኢኮኖሚያዊ ቅራኔ ነበራቸው። ተሐድሶው የተራ የቤተክርስቲያን አገልጋዮች ብቻ ሳይሆን የገናና መንግስታትና የመሃከለኛ መደብ ልሂቃን ጥያቄ ጭምር በመሆኑ ስኬትን አገኘ።
ሦሥተኛው ምክንያት የቤተክርስትያን መሪዎች ከእረኝነት ይልቅ አምባገነን ገዢነታቸው ማየሉ ተሓድሶው እንዲሳካ መደላድል ፈጥሯል። ቤተክርስቲያን ትኩረቷን ከመንፈሳዊ አገልግሎት ይልቅ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ አድርጋ ነበር። በመንፈሳዊነት ስም ገንዘብ መሰብሰብ ባህልና ልማድ ሆኖ ነበር።
ስለዚህ…የነዚህን ምቹ አጋጣሚዎችን ስናይ እንዲያው ዝም ብሎ አጋጣሚ ሳይሆኑ መለኮት ቤተ ክርስቲያንን ከወደቀችበት ለማስነሳት ጽዋው እንደሞላ ያሳየናል። ነገሮችን እያሰናሰኘ ሁኔታዎችን እያስማማ ተሓድሶውን በትክክለኝ ጊዜ አምጥቷታል። ለዚህም ነው ይህ ተሐድሶ እግዚአብሔር በትክክለኛው ጊዜ ለቤተክርስትያን የላከው ነው የሚባለው። በዚህም ተሐድሶ ምክንያት እግዚአብሔር የመላ አለሙን ፊት ቀይሮታል።
የእኛም ዘመን የመላሸቅ ጥልቀት ተሓድሶን እንድንሻ የሚያደርገን ይመስለኛል። እኛም ተሐድሶ ያሻናል!
#ተሐድሶ
#ክርስትና
#የትሩፋን_ናፍቆት
አማኑኤል አሰግድ
@meleket_tube