የድሬዳዋ መካነ ኢየሱስ ማህበረ ምዕመናንን ወቅታዊ ሁኔታ በመሚመለከት ከኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ የተሰጠ መግለጫ
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ፤ የድሬዳዋ ማህበረ ምዕመናን የቤተ ክርስቲያን ህንጻና ሌሎች ተያያዥ ህንጻዎች ያሉበትን ይዞታ ለሌላ አገልግሎት ለማዋል በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ካብኔ የተላለፈው ውሳኔ ቤተ ክርሰቲያናችንን ብቻ ሳይሆን መላውን ህዝበ ምዕመን በእጅጉ አስደንግጧል፡፡ እናም ውሳኔው እንደገና እንዲጤን ቤተ ክርስቲያኒቱ ከተለያዩ የመንግስት አካላት ጋር ብርቱ ክትትል በማድረግ ላይ ትገኛለች፡፡ የከተማው አስተዳደርም በተለይም ክቡር ከንቲባው ሁኔታውን በጥንቃቄና በሃላፊነት ስሜት እየተከታተሉ ሲሆን ከቤተ ክርስቲያኒቱ አመራር ጋርም ለመምከር ቀጠሮ ተይዟል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ጉዳዩ የማይመለከተውና በየትኛም መንገድ ድርሻ የሌለው አንድ አካል፤ ችግሩ መፍትሔ እንዳገኘ አድርጎ በዛሬው ዕለት በራሱ ማህበራዊ ገጽ (Facebook) የተሳሳተ መረጃ አውጥቷል፡፡ ይህን የፈጸመው አካል ይህንን ስህተት በአስቸኳይ እንዲያርም ጥብቅ ማሳሰቢያ የደረሰው መሆኑን እየገለጽን ቤተ ክርስቲያኒቱ እስከምታውቀው ድረስ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ምንም ዓይነት ውሳኔ ያልተሠጠ መሆኑንና ለወደፊትም ቤተ ክርስቲያኒቱ በራስዋ አሠራር ኦፊሴላዊ መረጃ እስከምትሰጥ ድረስ ህዝበ ምዕመኑ በትዕግስትና በጸሎት እንዲጠባበቅ እናሳስባለን፡፡
እግዚአብሔር አገራችንን ይባርክ፤ ይጠብቃትም!
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ
@meleket_tube