ፈልገህ አትረበሽ!
ተረጋግተህ መመሰጥ ስትፈልግ የሚረብሽህ ነገር አታጣም፤ ውስጥህን ለማዳመጥ ስትመቻች ትኩረትህን የሚበትን ነገር አይጠፋም፤ የህይወትህን ከፍታና ዝቅታ፣ ክብደትና ቅለት ለመረዳት ስትሞክር ውስጣዊና ውጫዊ ጫናዎች ፋታ ያሳጡሃል። የምርታማነትህ ዋነኛ መሰናክል መረበሽ፣ መረጋጋት አለመቻልና ትኩረት ማጣት እንደሆነ አስተውል። እንኳን ፈልገህ ይቅርና አለም እራሷ መረጋጋትህን አትፈልገውም፤ ተመስጦህ አይመቻትም፤ ከእራስህ ጋር በጥሞና መነጋገርህ አያስደስታትም። ስትረጋጋ ውስጥህን ትመለከታለህ፣ ፍላጎትህን በሚገባ ትለያለህ፣ ለአለም ጫጫታም ጊዜ የሚሰጥ ማንነት አይኖርህም፣ በእራስህ አለም የእራስህን አስደሳች ሁነት ትፈጥራለህ። እራሳቸውን የሚያዳምጡ ሰዎች ሰዎችን የማዳመጥና የመረዳት አቅማቸው ከፍተኛ ነው።
አዎ! ጀግናዬ..! ፈልገህ አትረበሽ፤ መርጠህ ጫጫታ ውስጥ አትግባ፤ በፍቃድህ ውስጣዊ ሰላምህን አትጣ። ለአለም ክስተት ትኩረት እንደምትሰጠው ለእራስህም ትኩረት ስጥ፣ ሌላው ሰው ሲያወራ እንደምታዳምጠው ውስጥህን የማዳመጥ ብርታት ይኑርህ፣ ለአለም ጫጫታ ምላሽ ለመስጠት እንደምትሯሯጠው የውስጥ ጥያቄህን ለመመለስ ጊዜ ውሰድ። ከየትኛውም ሃላፊነት የሚበልጠው ሃላፊነት እራስን የማወቅና እራስን የመግዛት ሃላፊነት ነው። በምታየው፣ በምትሰማው፣ በምታደርገው የምትረበሽ ከሆነ የመቀየር ሙሉ መብት አለህ። በተረበሸ አለም አንተም ለመረበሽ እራስህን አሳልፈህ እየሰጠህ እንዴትም እራስህን ልታገኘው አትችልም። ትኩረትህን ለማግኘት አለም ምንያክል ገንዘብ ፈሰስ እንደምታደርግ ብታውቅ ዋጋው በገባህ ነበር። ስትረጋጋ፣ ውስጥህን ስትረዳ፣ ለውስጣዊ ሰላምህ ዘብ ስትቆም ከአለም የእስር ሰንሰለት መውጣት ትችላለህ።
አዎ! ማንም ፈጣሪውን ያውቀውና ይከተለው ዘንድ አስቀድሞ እራሱን ማወቅና መረዳት ይጠበቅበታል። በጠፋች አለም እራስህን ለማጥፋት አትፋጠን፤ በተረበሸ አለም እራስህን በፍቃድህ ለመረበሽና ለማወክ አትንደርደር። ለእራስህ ጊዜ ካልሰጠህ ልትረጋጋ አትችልም፤ ውስጥህን ካላዳመጥክ ወደእራስህ ልትመለስ አትችልም፤ የግል አቋም ከሌለህ፣ በእራስህ አቅጣጫ ካልተመራህ ማንም ሲመራህ የምትመራ፣ ማንም የነገረህን የምታምንና በየትኛውም ጊዜያዊ ጫጫታ የምትሸበር ትሆናለህ። ብዙ ሃላፊነት እንዳለብህ አስብ፣ እንዲሁ እንደ ዋዛ ትኩረትህን አሳልፈህ መስጠት እንደሌለብህ ተረዳ። እራስህን ለማዳን ብለህ ከሚረብሹህ ነገሮች ፈቀቅ በል፣ ለውስጣዊ ሰላምህ ስትል ከእየአቅጣጫው ከሚመጡ ማዕበሎች እራስህን ጠብቅ።