🔷 በከባድ ኢንደስትሪዎች
ለሰው ልጅ እጅግ አደገኛ በሆኑ፣ ድግግሞሽ በሚበዛባቸው አድካሚ የከባድ ኢንደስትሪ ስራዎች ውስጥ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስን ዕውቀት የሚጠቀሙት ሮቦቶች የማይተካ ሚና ይጫወታሉ፡፡ ስለሆነም የሰው ልጆችን ከአደጋ ይታደጋሉ፣ ስህተት ስለማይሰሩ እና ስለማይደክማቸው ከፍተኛ ውጤት ያስመዘግባሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት በመኪና ምርት፣ በማዕድን ማውጣት ስራ እና ትላልቅ የፋብሪካ ማሽኖችን በሚያመርቱ ኢንደስትሪዎች ውስጥ ከፍተኛ አገልግሎት በመስጠት ላይ ናቸው፡፡
🔷 በትራንስፖርት
ሹፌር አልባ መኪኖች ራሳቸውን በራሳቸው የሚያንቀሳቅሱ፤ የተሰጣቸውን ትእዛዝ ተቀብለው ሰውንም ሆነ ዕቃ የተፈለገው ቦታ የሚያደርሱ፤ ተሰሳስተው አልያም ደክሟቸው በቸልተኝነት አደጋን የማያደርሱ መኪኖች የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የምርምርና ዕውቀት ውጤቶች ናቸው፡፡ ምንም እንኳን በአሁኑ ጊዜ በስፋት ለጥቅም ባይውሉም በGoogleX ፕሮጀክት በመሰራት ላይ ያለው አሽከርካሪ አልባ መኪና ተጠቃሽ ነው፡፡ ይህ መኪና ‹‹ጉግል ሹፌር›› የሚባል ሶፍትዌር የተገጠመለት ሲሆን የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ዕውቀትን ተግባራዊ በማድረግ የተሰራ ሶፍትዌር ነው፡፡ መኪናው በአሁኑ ወቅት በሙከራ ላይ ይገኛል፡፡
የሥነ ምግባር እና የፍልስፍና ጥያቄዎች
አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን የሰው ልጅ አስተሳሰብ፣ ባህሪ እና ጠባይ ለማሽኖች የሚያላብስ የሳይንስ ዘርፍ እንደሆኑ መጠን፤ ከዚህ ጋር ተያይዞ በዛ ያሉ የሞራል፣ የስነምግባር እና የፍልስፍና ጥያቄዎችን ማስነሳቱ አልቀረም፡፡ ከፍልስፍና ጥያቄዎቹም ውስጥ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ሶስቱ በዋነኛነት ተጠቃሽ ናቸው፡-
1. ማሽኖች የሰው ልጅ ሊፈታቸው የሚችላቸውን ችግሮ በሙሉ የመፍታተት አቅም ይኖራቸዋልን? ወይስ ማሽኖችን ‹‹ሰው›› የማድረግ ጥረት ገደብ አለው?
2. የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስን ባህሪያት የተላበሱ ማሽኖች አደገኛ ሊሆኑ ይችላሉን? በስነ-ስርአት እና ወግ ባለው መልኩ ጥቅም ላይ እንዲውሉ፤ ብሎም በምንም አይነት መልኩ ከቁጥጥር ውጭ የሆነ ባህሪ እንዳይላበሱ ማድረግ ይቻላልን?
3. ማሽኖችን ልክ እንደ ሰው ባለአእመሮ እና ባለህሊና ማድረግ ይቻላልን? እንደ ሰው ልጆችስ መብት ይኖራቸዋል? አውቀው እና በራሳቸው ተነሳሽነት ተንቀሳቅሰው በሰው ልጅ ላይ ጉዳት ማድረስ ይችላሉን?
ከላይ በተነሱት ጥያቄዎች ዙርያ የተለያዩ ሙሁራን የየራሳቸውን ፅሁፍ እያቀረቡ በንድፈ-ሀሳብ ደረጃ የተከራከሩ ሲሆን፤ ጥያቄዎቹ ምላሽ ሊያገኙ የሚችሉት በጊዜ ሒደት ብቻ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት የተለያየ ጥግ ይዘው ጥያቄዎቹን ለመመለስ የሞከሩም ሆኑ የሚሞክሩ ምሁራን ትክክለኛነታቸው የሚረጋገጠው በዘርፉ የተፈጥሮ እድገት ሂደት ውስጥ ብቻ ይሆናል ማለት ነው፡፡ እዚህ ጋር ሳይጠቀስ የማይታለፈው አንደኛው ጥያቄ ከሞራል ጋር የተገናኘው ነው፡፡ የሰው ልጆች ከአደጉበት ባህል፣ ከኖሩበት ዘመን ጋር በማቆራኘት ስለ ሞራል ምንነት ትርጓሜ ሲሰጡ ይታያል፡፡ በዚህም የተነሳ በተለያዩ የህይወት ውሳኔዎቻቸው ላይ ይህ የሞራል ግንዛቤ የራሱን አስተዋፅኦ ያሳድራል፡፡ ሞራል የጊዜ እና የባህል ተፅዕኖ ስለሚበዛበት አንድ ወጥ የሆነ ሞራላዊ ምንነት ለማሽኖች እንዲላበሱ የሚደረገውን ምርምር በዛው ልክ ወጥ ያልሆነ እና ውስብስብ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ ይሁን እንጂ ከላይ በተነሱት ፅንሰ-ሀሳባዊ የፍልስፍና ጥያቄዎች ዙርያ የሚደረጉት ምሁራዊ ክርክሮች እና ትንታኔዎች አሁንም ድረስ እንደቀጠሉ ናቸው፡፡
ከሞራል እና ስነ-ምግባር ጋራ የሚነሱ ጥያቄዎች እና በምሁራን የሚሰጡ ትንታኔዎች አከራካሪ፣ መሳጭ እና የሰውን ልጅ የወደፊት እጣ ፈንታ የሚወስኑ ስለሚሆኑ፤ በቀጣይ በዚህ ድረ-ገፅ የተለያዪ ፅሁፎችን በትንታኔ መልክ ለማቅረብ ይሞከራል፡፡
🔷 ማጠቃለያ
ብልህ እና እንደ ሰው ልጅ የሚያስቡ ቁስ አካላትን ለመፍጠር የሚደረገው ሳይንሳዊ ምርምር እና ዕውቀት ወደፊት የሰውን ልጅ የአኗኗር ስልት በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቀይር የማያጠራጥር ነው፡፡ አደጋን የሚቀንሱ፣ ጤንነትን የሚያሻሻሉ፣ ከፍተኛ ምርትን የሚያስገኙ፣ ወዘተ ጥቅሞችን እየሰጡ የሚገኙ እና ወደፊትም በላቀ ጥራት እና ውስብስብነት የሰውን ልጅ ህይወት የሚያቀሉ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ውጤቶች በዚህ አጭር ዕሁፍ ለመዳሰስ መሞከር ‹‹አባይን በጭልፋ›› እንደ መዝገን ይሆንብኛል፡፡
በዚህ ዘርፍ አያሌ እና ተነግረው የማያልቁ ግኝቶች፣ በምርምር ላይ ያሉ ዕውቀት፣ በዘርፉ ላይ የተነሱ እና የሚነሱ ጥያቄዎች፣ ወዘተ በመረጃነት ይገኛሉ፡፡በመሆኑም በዚህ ድረ-ገፅ ከዘርፉ ጋር ተያያዥ እና ጠቃሚ ናቸው የምንላቸውን ዜናዎች፣ አርቲክሎች(መጣጥፎች)፣ ፖድካስቶችን የምናቀርብ ሲሆን፤ የዘርፉን ውስብስብ ዕውቀትና ልምድ የሚያንፀባርቁ የምሁራን ክርክሮችን ጭምር በየጊዜው በቀላል አገላለፅ ለማቅረብ እንሞክራለን፡፡