Forward from: Nejashi Printing Press
የሰይደና ዑሥማን ተቀማጭ ሒሳብ
*******
ሙስሊሞች በስደት መዲና ከደረሱ በኋላ የመዲና ነዋሪ ቁጥሩ ጨመረ፡፡ ቁጥራቸው ብቻ ሳይሆን የዉሃ ፍጆታቸዉም ጨመረ፡፡ የሩማን የጉድጓድ ዉሃ በመዲና ዉስጥ ከሚገኙ የጉድጓድ ዉሃዎች መካከል ትልቁ ሲሆን ባለቤትነቱም የአንድ ይሁዲ ነበር፡፡ ይሁዲው እያንዳንዷን ጠብታ ዉሃ የሚሸጥ ስግብግብ ነው፡፡
ዑሥማን ረ.ዐ ሁኔታዉን ባዩ ጊዜ በቀጥታ ይሁዲው ዘንድ በመሄድ ጉድጓዱን እንዲሸጥለት ጠየቁት፡፡ ፈቃደኛ አልሆነም፡፡
ዑሥማን ሌላ ሀሳብ በማቅረብ ግማሹን ማለትም አንድ ቀን ለሱ አንድ ቀን ለሳቸው በሚሆን መልኩ እንዲሸጥላቸዉ ጠየቁት፤ ተስማማ፡፡ ሰውዬው ይህን ያደረገው ዑሥማን ሀብታም ነጋዴ በመሆናቸው ዋጋ ጨምረው ሙሉዉን ይገዙኛል ብሎ ስላሰበ ነበር፡፡ ግና በሚገርም ሁኔታ የምንጩ ዉሃ እየቀነሰ ሄዶ ሊጠፋ ሁሉ ተቃረበ፡፡ ለካስ ዑሥማን የራሣቸዉን ድርሻ ለሌሎች ተጠቃሚዎች በነፃ ስለለቀቁ ነበር ያ ሊሆን የቻለው፡፡ ሰዎች በዑሥማን ተራ ሄደው ከምንጩ ይቀዳሉ፤ በአይሁዱ ቀን ግን አንዳቸዉም አይሄዱም፡፡ ስለዚህ አይሁዱ ገቢ አጣ፡፡ በዚህን ጊዜ ኪሳራ ዉስጥ እንደገባ ተሰማው፡፡ ድርሻዉንም ሊሸጥለት ተስማማና በሀያ ሺህ ድርሀም ገዙት፡፡ ዑሥማን ምንጩን ሰዎች እንዲጠቀሙበት ለአላህ ሲል ሠጠ፡፡
ከተወሰነ ጊዜ በኋላ አንድ ሶሐባ መጣና የገዛበትን እጥፍ ከፍሎት እንዲሸጥለት ጠየቀው፡፡ “ከዚያ በላይ ተሠጥቶኛል” አሉት ዑሥማን፡፡ “ሦስት እጥፍ ልክፈልህ” አላቸው፡፡ “ከዚያም በላይ ተሠጥቶኛል፡፡” አሉት፡፡ እስከ ዘጠኝ እጥፍ ቢሠጣቸዉም ከዚያ በላይ ተሠጥቶኛል ብለው እንቢ አሉ ዑሥማን፡፡ አይሁዱ በመገረም መዲና ዉስጥ እኔ ከሠጠሁህ በላይ ማነው ሊሠጥህ የሚችል! አላቸው፡፡
ዑሥማንም “አላህ አሥር ዕጥፍ ሠጥቶኛል፡፡” አሉት፡፡
ዑሥማን ይህን ምንጭ የአላህን ዉዴታ ሽተው ከ1400 ዓመታት በፊት ለሙስሊሞች ጥቅም ለገሱ፡፡ ከጊዜ በኋላ ደግሞ በዙርያው ተምር ተተከለ፡፡ በየጊዜው የተለዋወጡ ሙስሊም መንግሥታት ለምንጩና ለተምሩ እንክብካቤ እያደረጉ ትልቅ እርሻ ሆነ፡፡
ከዚያ ምንጭ የበቀለው ተምር ይሸጥና ገቢው ለወላጅ አጥ ሕፃናት እንክብካቤ ይዉላል፤ ሌላው ደግሞ የአውቃፍ ሚኒስቴር በሚያስተዳድረው በዑሥማን ሥም በተከፈተ ሂሳብ ዉስጥ ይቀመጣል፡፡ በዚህ መልኩ የዑሥማን ምንጭ ገቢ እያደገ ሄደ፡፡ በርሱ ገንዘብም በሐረም ዙርያ ቦታ ተገዛና ለእንግዳ ማረፊያ የሚሆኑ ቤቶች ተገነቡ፡፡ ቤቶቹም ትልቅ ገቢ የሚያስገኙ ሆኑ፡፡
ዑሥማን በዚህ መልኩ ባንክ ዉጥ ሂሳብ አላቸው፡፡ በሕይወት ባይኖሩም ከ14 ምዕተ ዓመታት በፊት ከአላህ ጋር የተጀመረ ንግዳቸው ቀጥሏል ፡፡ ምንዳቸው ምን ያህል በዝቶ ይሆን !!
ከሞት በኋላ የሚጠቅም ቀጣይ ሰደቃ ማለት ይኸው ነው!!
https://t.me/NejashiPP