በ2017 ዓ/ም መማር ለምትፈልጉ አመልካቾች በሙሉ
#Ethiopia | በአንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በቀን በመደበኛ መርሃ ግብር በመንግስት ስኮላርሺፕ እና በግል በመጀመሪያ ዲግሪ በ2017 ዓ/ም መማር ለምትፈልጉ አመልካቾች በሙሉ፤
በ2017 ዓ/ም በቅድመ ምረቃ መደበኛ መርሃ ግብር በትምህርት ሚኒስቴር ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምደባ እንደማይኖር ይታወቃል።
በመንግስት ስኮላርሺፕ እንዲሁም በግል ከፍላችሁ በዩኒቨርሲቲያችን መማር ለምትፈልጉ በሙሉ የአ.አ.ዩ የሚያወጣውን የመግቢያ ፈተና (UAT) እንዲሁም ሌሎች መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባችኋል፡፡
በዚህም መሠረት በዩኒቨርሲቲያችን ድረ ገጾች
(www.aau.edu.et ወይም https://portal.aau.edu.et) ላይ የተመለከቱትን ዝርዝር የማመልከቻ መስፈርቶች በማሟላት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
• የመመዝገቢያ ቀናት እስከ መስከረም 8/ 2017 ዓ.ም ድረስ ይሆናል
• የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀናት ወደፊት በ ዩኒቨርሲቲያችን ዌብ ሳይት፤ የምዝገባ ፖርታል እንዲሁም በማህበራዊ ትስስር
ገጾች ላይ የሚገለጽ ይሆናል::
አ.አ.ዩ ሬጅስትራር