ጊዜዬ እስኪደርስ
ጊዜዬ እስኪደርስ ወደ አንተ መምጫየ
ለንስሐ አብቃኝ አቤቱ ጌታየ /2/
ብርሃኔ መድኃኒቴ ተስፋህ ይመልሰኝ
ጥፋቴን ደምስሰህ ይቅርታ አድርግልኝ
ተስፋዬ እረዳቴ አንተ አትጣለኝ
አምላኬ አታጥፋኝ ከሲኦል አድነኝ
መኃሪ ይቅር ባይ ምሕረትህ ይጎብኘኝ
ከኃጢአት ፍላጻ ጸጋህ ይታደገኝ
አዳኜ መድሃኒቴ ሰላምን ላክልኝ
የፅድቅ ደጆችህን በፍቅር ክፈትልኝ
አቤቱ ምህረትህ በእኔ ላይ ይሁን
ተጨነቅሁ አምላኬ ስጠኝ ሰላምን
ከክፉ እንድሸሽ አድነኝ እኔን
በጎ እንድሰራ ምራኝ መንገዱን
ሕይወት ሞት ድኅነትን መኖራቸውን ባውቅም
ኃጢአት ውድቀት ጥፋት አያዘናጋኝም
ስርየት እንደማገኝ ተስፋ ቢኖረኝም
ትምክህቴ አንተ ነህ በሌላ አልመካም
የበደሌ ብዛቱ የሚያስከፋም ቢሆን
በሥጋ በደምህ እጠብ ኃጢአቴን
ወደ አንተ እጮሀለሁ አደራ ነፍሴን
በሰማያዊው ቤት አኑር ሕይወቴን
ሊቀ መዘምራን መልዐከ ሰላም ታደለ ፊጣ
• ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች •
🔔 ሼር 📍
ቶሎ ቶሎ እንድንለቅ ሪያክሽን እንዳይረሳ ❤️
🟡➪ @Name33O
🟡➪ @Name33O
ጊዜዬ እስኪደርስ ወደ አንተ መምጫየ
ለንስሐ አብቃኝ አቤቱ ጌታየ /2/
አዝ
ብርሃኔ መድኃኒቴ ተስፋህ ይመልሰኝ
ጥፋቴን ደምስሰህ ይቅርታ አድርግልኝ
ተስፋዬ እረዳቴ አንተ አትጣለኝ
አምላኬ አታጥፋኝ ከሲኦል አድነኝ
አዝ
መኃሪ ይቅር ባይ ምሕረትህ ይጎብኘኝ
ከኃጢአት ፍላጻ ጸጋህ ይታደገኝ
አዳኜ መድሃኒቴ ሰላምን ላክልኝ
የፅድቅ ደጆችህን በፍቅር ክፈትልኝ
አዝ
አቤቱ ምህረትህ በእኔ ላይ ይሁን
ተጨነቅሁ አምላኬ ስጠኝ ሰላምን
ከክፉ እንድሸሽ አድነኝ እኔን
በጎ እንድሰራ ምራኝ መንገዱን
አዝ
ሕይወት ሞት ድኅነትን መኖራቸውን ባውቅም
ኃጢአት ውድቀት ጥፋት አያዘናጋኝም
ስርየት እንደማገኝ ተስፋ ቢኖረኝም
ትምክህቴ አንተ ነህ በሌላ አልመካም
አዝ
የበደሌ ብዛቱ የሚያስከፋም ቢሆን
በሥጋ በደምህ እጠብ ኃጢአቴን
ወደ አንተ እጮሀለሁ አደራ ነፍሴን
በሰማያዊው ቤት አኑር ሕይወቴን
ሊቀ መዘምራን መልዐከ ሰላም ታደለ ፊጣ
• ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች •
🔔 ሼር 📍
ቶሎ ቶሎ እንድንለቅ ሪያክሽን እንዳይረሳ ❤️
🟡➪ @Name33O
🟡➪ @Name33O