"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Religion


🌹«ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን
/አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ።♥ https://t.me/Orthodoxtewahdoc

ሐምሌ 3 በ2014 ዓ°ም ተከፈተ።
📌እግዚአብሔር ቢፈቅድ የቅዱሳኑን ታሪክ እንመማርበታለን ብለን ከፈትነው ቅዱስ እግዚአብሔር ይፍቀድልን አሜን‼
❤የእመ ብርሃን ልጅ🤗

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Religion
Statistics
Posts filter


ስትኖር ለብቻህ አትኑር
የሌሎችን ችግር በመፍታት ኑር
ገንዘብ ካለህ በገንዘብህ ደሃውን በመርዳት ኑር
ጉልበት ካለህ በጉልበትህ ደካመውን በመርዳት ኑር
እውቀት ካለህ እውቀትህን ሌላው በማካፈል ኑር
ሥልጣን ካለህ ለተበደሉት በመፍረድ ኑር
ቤት ካለህ ጎዳና ላይ ወድቆ የሚያድረውን ወንድምህን በማስጠጋት ኑር
ልብስ ካለህ ራቁቱን ላለው ወንድምህ በማልበስ ኑር
ምግብ ካለህ የሚበለው ላጣው ወንድምህ በማብላት ኑር
ገንዘብ ካለህ ለሌላው አካፍል የአንተ ገንዘብ ባንክ ተጨናንቆ ደሃ ሲቸገር
እግዚአብሔር ይታዘብሃል
ጠንካራ ጉልበት እያለህ ደካማውን ወንድምህን ሳትረዳ ስትቀር ጉልበት
የሰጠህ አምላክህ ይመለከትሃል ጠንካራው ጉልበትህ ደካማ ይሆናል አንተም
በጊዜህ አንሱኝ ጣሉኝ ትላለህ የአንተ ጠንካራ ጉልበት ደካማውን ለማሸነፍ
አይደለም የተፈጠረው ደሃውን ለመርዳት ነው እንጂ
እውቀትህ ሌላ ካላስተማርክበት እውቀቱን የሰጠህ ፈጣሪህ እውቀትህን
እንደሚነሳህ አስብ እውቀት ችግር መፍቻ ነው እንጂ ችግር ማምጫ አይደለም
እውቀት ወደብርሃን የሚመራ እንጂ ወደጨለማ የሚወስድ አይደለም የአንተ
እውቀት የዶክትሪት የማስትሪት የድግሪ የዲፕሎማ የመጽሐፍ የቅኔ የድጓ
የአቋቋም የዝማሬ የቅዳሴ እውቀትህ ላላወቁት ለማሳወቅ እንጂ ለመወደስ
ለመከበር ለመፈራት አይደለም
በስልጣንህ የምታዳላ ከሆነ ሰማያዊ ስልጣን ባለው
ፊት ተከሰህ ስትቀርብ መልስ ታጣለህ ስልጣንህ ለተበደለ ፈራጂ ለተቀማ
አስመላሽ የድኀ እንባ አባሽ መሆን አለበት ዛሬ ሰዎች ተከሰው ወደአንተ ፊት
እንደቀረቡ ሁሉ አንተም ተከሰህ በፈጣሪህ ፊት ትቀርባለህና
ልብስህ ቁም ሳጥን ሞልቶ ሻንጣ አጨናንቆ አንተ በሰላሳ ቀን ሰላሳ ልብስ
እየቀየርህ እንዳንተ ገላ ያለው ሰው ራቁቱን ሁኖ ብርድና ሙቀት ሲፈራረቅበት
የማታለብሰው ከሆነ ሰማይን በደመና የሚያለብሰው ምድርን በእሳር የሚሸፍነው
አምላክህ ያዝንብሃል
አንተ ምን ልብላ ብለህ አማርጠህ ትበላለህ በቀን አራት አምስት ጊዜ
ትበላለህ እንዳንተ ምግብ የሚፈልገው ወንድምህ የሚበለው አጥቶ ሲራብ
ትተኸው ስትበላ በዝናብ አብቅሎ በፀሐይ አብስሎ የሚመግብህ አምላክ
የሰጠህን ምግብ ይነሰሃል ታመህ ያየሀውን ሁሉ እንዳትበላ ያደርግሃል
ስትቆርጠው የነበረው ጮማ ስትጎነጨው የነበረው ውስኪ ሁሉ ይቀራል
ገንዘብህ በባንክ እየደለበ ሌላውን ካረዳህበት ስትሞት አብሮህ አይቀበርም
ወደመቃብር ስትወርድ በአንድ ነጭ ነጠላ ተጠቅልለህ ነው ሀብትህ ሁሉ
አይከተልህም እግዚአብሔር ሀብት የሰጠህ አንተ ለዳሀው ሰጥተህ እንድትጸድቅ
ዳሀው ተቀብሎ እግዚአብሔርን እንዲአመሰግን ነው
ሰው ሆይ በትክክለኛው መንገድ ኑር
ለኳስ ሁለት ሰአት ጊዜ ሰጥተህ ለቅዳሴ አንድ ሰአት አልሰጠህም
ለፊልም ረጅም ጊዜ ሰጥተህ ለወንጌል አጭር ጊዜ አጥተሃል
ለኳስ ጨዋታ ተወራርደህ ብር ትሰጣለህ ለቤተ ክርስቲያን ማሰሪያ እጅህ
ይታሰራል
ለፊልም እስፖንሰር ትሆናለህ ለወንጌል ግን አምስት ሳንቲም ለማውጣት
ትቆረቆራለህ
የፊል አክተሮችን አንድ በአንድ ታውቃቸዋለህ የኳስ ኮከቦችን በደረጃ
ትጠራቸዋለህ
ወንጌሉን የጻፉት አነማናቸው ስትባል መልስ ታጣለህ
ሰው ሆይ አንተ ለዘለዓለም በምድር አትኖርም በሰማይ ለመኖር የተፈጠርህ ነህ
ወደምድር ያወረደህ የአባትህ የአዳም የናትህ የሄዋን ኀጢአት ነው እንጂ ሀገርህ
በሰማይ ነው ለተወሰነ ጊዜ በምድር ትቆያለህ ሇላ ከምድር ወደላይ ትወሰዳለህ
በሰማይ በበጎ ቦታ ለመኖር በምድር ሳለህ መልካም ስራ ስራ ከጎንህ
የምታውቀው ሰው ሲሞት ከማልቀስ ባሿገር ነገ አንተ እነደምትሞት ተማርበት
ጎረቤትህ ዛሬ ሲሞት ነገ ተረው የአንተ መሆኑን አትርሳ
ዓለም ጨለማ ናት ወደጨለማ ሳትወስድህ ወደብርሃን ተጉዘህ ቅደማት
የምታልፈው ዓለም እድሜህን በከንቱ ሳትጨርስብህ ማለፏን አውቀህ ቅደማት
ዓለም የዛሬ ናት ዛሬ አስደስታ ነገ ታስለቅስሃለች
ዛሬ አሳይታ ነገ ታሳጣሀለች
ዛሬ አጥግባ ነገ ታስርብሐለች
ዛሬ ሹማ ነገ ትሽርሃለች
ዛሬ አክብራ ነገ ታዋርድሃለች
ዛሬ አሳምራ ነገ ታጠቁርሐለች
ዛሬ አድንቃ ነገ ትንቅሃለች
ዛሬ አጨብጭባለህ ነገ ድንጋይ ትወረውርብሐለች
ዛሬ ከፍ ከፍ አድርጋ ነገ ዝቅ ዝቅ ታረግሃለች
ለአንተ አባቶች አልሆነችም መቃብር ከታቸዋለች ከቀደሙት አባቶችህ ተማር የምታውቃቸው ካንተ ቀድመው የነበሩ ዝነኞች ባለ ሀብቶች አርቲስቶች
የሃይማኖት አባቶች ባለ ስልጣናት ሁሉ መቃብር ውስጥ እንደሆኑ ተረዳ
ስማቸው ከመቃብር በላይ ቀርቷል መልካም የሰሩት በመልካም ስም ክፉ የሰሩት በክፉ ስም ይታወሳሉ
ሰው ሆይ ለሰው ችግር ሳትሆን ሰውን በመርዳት ኑር።

መልካም ቀን✝


እለተ አርብ የፍቅር ቀን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጆች ብሎ መስቀል ላይ የዋለበት ቀን ነው እንኳን አደረሳችሁ ።የዓለም መድኃኒት ጌታዬ መድኃኒቴ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ በቀራንዮ በተሰቀልክበት መስቀል እማጸንሃለው። ከመስቀሉ ስር ተደፍታ በምታነባው እናትህ እለምንሃለሁ ከኃጢዓቴ አንፃኝ መተላለፌን አትቁጠርብኝ በእምነት በምግባር አፅናኝ አቤቱ ማረኝ! ምህረትህ ቸርነትህ አይለየን አሜን በእውነት ።🤲🥰✝

719 0 11 2 35

🌷መልክአ መጥምቀ ዮሐንስ✝

ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ ሰላም እልሃለሀ/፫/

በጨነቃችሁ ጊዜ ሁሉ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዩሐንስ አለው ይበላችሁ ከመከራ ስጋ ከመከራ ነፍስ ይሰዉራችሁ።

🥰🙏🥰


✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"📖ምሳ 1፥33☦📚
        
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
📗ስንክሳር ዘወርኃ ጥር ፴/30

ወለተ ሥላሴ ብላችሁ በጸሎታችሁ አስቡኝ
https://t.me/Orthodoxtewahdoc
🌹የያዕቆብ ሌሊት ይሁንልን🕊




አቤቱ አምላኬ ሆይ
የመጠሪያዬን ዘመን አላውቀውምና
ኃጢዓቶቼን አስታውዬ የማይበትን ከፊትህ ተደፍቼ ይቅርታን የምጠይቅበትን አንደበት ስጠ
ኝ🙏


እነዚህ ካሉህ ተመስገን በል👇🙏🙏
#ሳይንስ ያልሰጠን እና የማይሠጠን ፣ አምላክ ብቻ የሠጠን የማይገዙ ፣ የማይሸጡ በየሰከንዱ የሚያሥፈልጉን ግን የዘነጋናቸው ነገሮች አሉ ፡፡ አስቀይመሃል፣ አይገባህም ሳይባል
በፍትሃዊነት ለሁሉም እየተሰጠ ነው ፡፡ በየሰከንዱ ማመስገን
ይገባናል ፡፡ አላመሰገንክም ተብሎም አይነፈግም፡፡
ምክንያቱም ሁሉም በነፃ እየተጠቀማቸው ስለሆነ፡፡
በየ ሰከንዱ የምንመገበው ንፁህ አየር
በየ ሰከንዱ የምናስወግደውን የተቃጠለ አየር ማስወገጃ ቦታ ፡፡
የምንራመድበት መሬት ፡፡
የመንጠጣው እና የምንተጣጠብበት ውሃ ፡፡
ለቀን የፀሓይ ብርሃን ፡፡
ለሌሊት የከዋከብት እና የጨረቃ ብርሃን ፡፡
በየግዜው አድሱኝ የማይል አካል ፡፡
አንድሰው እንዚህን ካገኘ ያለስስት በነጻ የሠጠውን አምላክ
እያመሰገነ መኖር ይጠበቅበታል
እነዚህን የአምላክ በረከቶች ያጡ በየቤቱ አሉ ፡፡
አየር እያለ መተፈሻ ሳንባ ያጡ ፣
መሬት እያለ መራመጃ እግር ያጡ ፣
ውሃ እያለ ጤነኛ ኩላሊት ያጡ ፣
ውብ ስነፍጥረት እያለ ዓይን ያጡ ፣ወጎኖቻችን ዓሉ ፡፡
ነገር ግን በጤነኛ አካሉ የተሰጠውን በረከት ማጣጣም የተሳነው
የቁም በሽተኛ በየቤቱ ነው ፡፡ እነዚህን ሰዎች ይማርልን ፡፡
ተመስገን አምላኬ ብሎ የሚያመሰግን ፤የለም ብሎ ለማውራት ያስደፍራል ፡፡ የፈለከውን ገንዘብ ቢኖርህ ኦክስጅንን
በፍጹም መግዛት
አይቻልም ፡፡የስልጣኔ ጫፍ ላይ ቢደርሰም ፀሓይን መተካት አይቻልም ፡
ውሃን መፍጠር አይቻልም ፡፡እፅዋትን መፍጠር አይቻልም ፡፡
ጦርነትን መፍጠር ይቻላል ፡፡ የለምን መፍጠር ይቻላል ፡፡
ምክንያት መፍጠር ይቻላል ፡፡ ውሸትንም መፍጠር ይቻላል ፡፡
በነፃ የተሰጠንን እና የናቅናቸውን ግን መፍጠር አይቻልም ፡፡የተጋረደውን ዓይናችንን ገልጠን እንደ ኔትወርክና መብራት ሳያቆራርጥ የሰጠንን አምላክ ብቻ
አንርሳ። እግዚአብሔር ይመስገን
🙏


እግዚአብሔር ወረት የለውም በትላንት ከወደደህ ይልቅ ዛሬን አብዝቶ ይወድሀል። እለት እለት ብትበድለውም እለት እለት ምህረቱ ይበዛልሃል። እለት እለት ጥበቃው አይጎልብህም። የበዛውን በደልህን ኣሳንሶ ጥቂቷን መልካም ስራህን አግዝፎ በቸርነቱ ያኖርሃል። ክብር ምስጋና ለስሙ ይሁን🙏🙏

1.2k 0 14 13 54

Forward from: "ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒
ወር በገባ በ30 ነቢይ ባህታዊ ድንግል  መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ እንዲሁም ወንጌላዊ ቅዱስ ማርቆስ ናቸው።🌷

ወቶ ከመቅረት ካልታሰበ አደጋ ከክፉ ነገር ሁሉ ይሰውሩን።🙏❤


Forward from: "ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒
⛪🌹#ወር በገባ በ30 መጥምቀ መለኮት ዮሐንስ🌹

📌☞ጸሎቱና በረከቱ ለዘአለዓለሙ ከኹላችን ህዝበ ክርስቲያኑ ይሁን፡ ነብይ ሐዋርያ ሰማዕት የሆነ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ያደረገው ተአምር ይኸ ነው፡።
🛐የመጥምቀ ቅድስ ዮሐንስ የበዓሉ መታሰቢያ በዕለተ እሁድ ውሎ በወርሀ ታህሳስ ኹለት ቀን በደብረ አንገች በተከበረ ጊዜ ከቅዳሴ በኃሏ የመጥመቀ መለኮት ዮሐንስ መጽሐፍ ገድልን በንዱ አረጋዊ መነኮሴ አንደበት ይሰሙ ዘንድ ካህናቱና ሕዝቡ ተሰበሰቡ፡፡

☞ያንጊዜም ወደዚህ ጉባኤ አንዲት ሴት ቀረበች፡፡ድምጿ አሰምታ እልል እያለች
ጮኽች፡፡ይህ የክርስቲያን ጉባኤ እስኪታወክ ሕዝብ ኹሉ እርስ በእርሳቸው ይቺ
ሴት ምንድናት ደስታዋ ምንድነው እስኪሉ ድረስ እልልታዋን አልተወችም፡፡ ያመነኩሴ ግን ልብ እንደተሳናት እንደሰከረችም ቁጠራት ዝም ትል ዘንድ ገሠፃት፡፡

☞ይኽች ሴት ግን አባቴ ካህኑ ሆይ እኔ ልቤ ያዘነበት ሴት ነበርሁ፡፡ዛሬ ግን ለምለም ፍሬ የሌላት ደረቅ ዛፍ በሚሉኝ ጎረቤቶቼ መሳቂያ ለጠላቶቼ መዘባበቻ የነበርኩ ማኀፀኔ የተዘጋ እኔ ባሪያውን በቸርነቱ በጎበኘኝ በወዳጄ በቅዱስ
ዮሐንስ አምላክ በእግዚአብሄር ልቤ ጸንቶል ከብዙ እድሜዬ በኃላ ልጅ ሰጥቶኛል እኔስ ዝም አልልም አለች፡፡

☞ያም መንፈሳዊ አባት መነኩሴ ወደሱ ትቀርብ ዘንድ የምትለውን ሕዝብ ይሰሙ ዘንድ ጠራት ይቺም ሴት ወደ ቤተክርስቲያኑ አደባባይ አደባባይ እልል እያለቾ ከወለደችው ልጇ ጋር ቀርባ አባቶቼ ና ወንድሞቼ እኅቶቼም ሆይ አንድ
ልጅ እንኳን በማጣት ብዙ ዘመን ሳዝን ስተክዝ ኖርሁ ዘመዶቼ ሳይቀሩ ጎረቤቶቼ ኹሉ የደረቀች ዛፍ ይሉኝ ነበር ፡፡

ስለዚህ አምና እንዳ ዛሬው ወደ ወዳጄ መጥምቁ
ቅዱስ ዮሐንስ መጥቼ ተሳልሁ ይኸንን መልኩ ያማረ ደምግባቱ የተወደደ ልጅ ሰጠኝ ድንቅ ተዐምር ለሚያደርግ ለመጥምቀ መለኮት ዮሐንስ እልል እላላሁ በመጥምቁ በቅዱስ ዮሐንስ አማልጅነት ይህን ልጅ ለሰጠኝ ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ ስትል መሰከረች፡፡

☞ይህን የሰሙ ሕዝቡም ኹሉ አደነቁ በማግስቱ ያመነኩሴ ከካህናቲ ጋር ኾኖ ያን ሕፃን አጠመቀው፡፡እርሷም እልል እያለች እየዘመረች ወደ ቤቷ ተመለሰች፡፡ ☞የመጥምቀ መለኮት ቅድስ ዮሐንሰ ጸሎቱ በረከቱ በማላጅነቱ ለምታምኑ ሁሉ ከእናተ ጋር ይኹን፡፡
☞ገድለ ዮሐንስ መጥምቅ
☞ሲራክ ተክለጻዲቅ የተዋህዶ ልጅ
☞. https://t.me/Orthodoxtewahdoc




Forward from: "ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒
☞ወር በገባ በ 30 ታስቦ የሚውለው ወንጌላዊ ቅዱስ ማርቆስ ያደረገውታእምር ይህ ነው፡፡
☞ከእናቱ ማኅፀን ከተወለደ ጊዜ ጀምሮ ፈጽሞ
አይቶ የማያውቅ ሁለት ዐይኖቹ የታወሩ አንድ ሰው ነበር፡፡
☞አንድ ቀን ሰዎች የተመረጠ የወንጌልላዊ ማርቆስ ገናንቱንና የተአምራቱን
ብዛት ሲናገሩ ሰማ፡፡ ሕመማቸው ልዩ ልዩ የሆነ ሕመምተኞችን ሁሉ በየጊዜው
እንደሚያድን፥ በፍጹም ምልጃው ወደ እግዚአብሔር ለሚማፀኑ የዚህ
የእስክንድርያ የአፍሪካ ሀገሮች ሁሉ ሊቀ ጳጳስ የሆነ ሐዋርያ ሰማዕት፥ብፁዕና
ቅዱስ የሆነ የማርቆስ ሥጋ ወደአለበት የሚሄድ ሁሉ እንዲፈውሱ ሰማ፡፡
☞ከዚያች ቀን ጀምሮ ዘመዶቹን ይማልዳቸው ጀመር፡፡ኅይል የሚያደርግ
የወንጌላዊው የቅዱስ ማርቆስ ሥጋ ወደ አለበት ቤተ ክርስቲያን ይወስዱት
ዘንድ፤ በወንጌላዊው በቅዱስ ማርቆስ ጸሎትና ምልጃ ቸርነት ድኅነት ያገኝ
ዘንድ፡፡ እነርሱ ግን ቸል ብለው አልወሰዱትም፡፡
☞አንድ ቀን አባቱን አባቴ ሆይ እንዴ እንደዚህ ጠላኸኝ፡ችላ አልኸኝ ተአምራት
የሚያደርግ ወንጌል የሚያስተምር ብፁዕና ቅዱስ የሆነ ማርቆስ ሥጋ ወደ አለበት
የማትወስደኝ ስለ ምንድ ነው አለው አለቀሰ
☞አባቱም ይህንን የልጁን ቃል በሰማ ጊዜ ልቅሶውን በተመከተ ጊዜ ልቡናው
አዘነ፡፡ መታገሥም አልቻለም፡፡ ከእርሱ ጋር ያለቅስ ጀመረ፡፡
☞አባቱም በነጋታው ማልዶ ተነሣ፡፡ የታመመ ልጁን በአህያ ጭኖ ከታላቅ ልጁ
ጋር ውሰዱኝ ወደአላቸው ቦታ ወሰዶት በሦስተኛው ከቅዱስ ማርቆስ
ቤተክርስቲያን ደረሱ፡፡
☞ከዚያ በደረሱ ጊዜ በዚያች ቀን የእስክንድርያና የግብጽ ኮከብ የሆነ የብፁና
የቅዱስ ማርቆስ ሥጋው ካለበት አሰገቡት፡፡
☞ከዚያም ገብቶ የቅዱስ ማርቆስ ሥጋው ያለበትን ሣጥን ተሳለመ፡፡ ያን ጊዜም
ዐይኖቹ በሩለት የቀኑንም ብርሃን ፈጽሞ አየ፡፡
☞ያዐይኖቹ የዳኑለት ሰዎ ከአባቱና ከወንድሙ ጋር ፈጽሞ ደስ አለው ፡፡ ከዚያ
የነበሩ ያ ዐይነ ስውር እንደዳነ ያዩም ሁሉ በቅዱሳን የሚመሰገን እግዚአብሔር
ፈጽመው አመሰገኑ፡፡
☞እነዚያ የሰበሰቡ ሰዎች ያን ዐይኑ የታወረውን ሰው እግዚአብሔር በባለሟሉ
በወንጌላው በማርቆስ ጸሎት እንዳደነው ባየ ጊዜ የእግዚአብሔር ምስጋናው
አበዙ፡፡
☞ብፀዕ የሚሆን የቅዱስ ማርቆስ ጸሎቱና በረከቱ ከሁላችን ሕዝበ ክርስቲያን
ጋር ይሁን ለዘለዓለሙ አሜን፡፡
☞(ገድለ ወንጌላዊ ቅዱስ ማርቆስ)
☞ሲራክ ተክለጻዲቅ የተዋህዶ ልጅ




Forward from: "ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒
†✝† እንኳን ለቅዱሳት አንስት ሶፍያ ወአዋልዲሃ: ኦርኒ ወማኅበራኒሃ እና ለሊቁ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †✝†

†✝† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †✝†

†✝† ቅድስት ሶፍያና ልጆቿ †✝†

†✝† በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ታዋቂ ከሆኑ የእናቶቻችን ስሞች "ሶፍያ" ቀዳሚው ነው:: ቃሉ በጥሬው ሲተረጐም "ጥበብ (ጥበበ ክርስቶስ) Wisdom of God" ማለት ነው:: ከጻድቃንና ከሰማዕታት ወገን በዚህ ስም የተጠሩ እናቶች አሉ::

ከእነዚህ መካከል አንዷ የሆነችው በዕለቱ የምናስባት እናት ቁጥሯ ከሰማዕታት ነው:: ዋናው ዘመነ ሰማዕታት ከመጀመሩ በፊት የነበረችው ቅድስት ሶፍያ ከሕግ ትዳር 3 ሴቶች ልጆችን አፍርታለች::

ስማቸውንም:- ጲስጢስ (ሃይማኖት) : አላጲስ (ተስፋ) : አጋጲስ (ፍቅር) ስትል ሰይማቸዋለች:: እንደሚገባም በሥርዓቱ አሳድጋ እድሜአቸው 9 : 10 እና 12 ሲደርስ ለሰማያዊ ሙሽርነት አጭታቸዋለች::

በዘመኑ "ክርስቶስን ካዱ" የሚል መሪ ተነስቶ ነበርና ቅዱሳቱ በመድኃኒታችን አምነው : ጣዖትን ዘልፈው አንገታቸውን ሰጥተዋል:: ክብረ ሰማዕትን : ሃገረ ክርስቶስንም ወርሰዋል::

††† ቅድስት ኦርኒ ሰማዕት †††

††† "ኦርኒ" ማለት በምሥራቃውያን ልሳን "ሰላም" ማለት ነው:: ቅድስቲቱ አርበኛ የዘመነ ሐዋርያት የቤተ ክርስቲያን ፍሬ ስትሆን ተወልዳ ያደገችውም በቀድሞው የሮም ግዛት ውስጥ ነው::

ምንም ዛሬ ያለ ትውልድ ቢዘነጋት ቅድስት ኦርኒ ተወዳዳሪ የሌላት ሰማዕት : ሐዋርያዊት : ድንግል ናት:: እርሷ ውበቷን : ንግሥናዋን : ክብሯን : ሃብቷን : ወጣትነቷንና ያላትን ሁሉ ስለ ፍቅረ ክርስቶስ ሰውታለችና ክብርት ናት::

በ1ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ከሮም ቤተ መንግስት የተወለደችው ቅድስት ኦርኒ እስከ ወጣትነቷ ድረስ ክርስቶስን ልታውቀው አልተቻላትም ነበር:: ምክንያቱ ደግሞ ንጉሡ አባቷ ጣዖትን ማምለኩ ነበር::

ንግሥት እናቷ ምንም ክርስቲያን ብትሆንም ስለ ክርስትና ልትነግራት አልደፈረችም:: ይህን ብታደርግ የሚደርስባትን መከራ ታውቃለችና:: ግን ደግሞ ውስጥ ውስጡን ትጸልይላት ነበርና ፈጣሪ መንገዱን ሊከፍት ጀመረ::

መምለኬ ጣዖት አባቷ ሰው እንዳያያት ቤተ መንግስት ሠርቶ : 12 ሞግዚቶችን መድቦ ጣዖት ከፊቷ አቁሞ ለዘመናት ዘጋት:: የሚገርመው ግን መልኳን እንዳያይ በበር ሆኖ የሚያስተምራት ፈላስፋ ተቀጥሮ ነበርና የዚህ ሰው ማንነቱ ነው::

መምለኬ ክርስቶስ ደግ ሰው ነበርና ፈሊጥን ይሻላት ገባ:: በዚህ መካከል ቅድስት ኦርኒ ራዕይን ታያለች:: የቤቷ መስኮቶች ተከፍተው ሳሉ በስተምሥራቅ ነጭ ርግብ : የዘይት (የወይራ) ዝንጣፊ ይዛ ገብታ : ከማዕዷ ላይ ጥላው ወጣች::

እርሷን ተከትሎ ቁራ በምዕራብ ገባ:: እባቡን ማዕዷ ላይ ጣለው:: በ3ኛው ደግሞ ንስር ገብቶ አክሊል ትቶላት ወጣ:: ቅድስቲቱም እየገረማት አረጋዊ መምህሯን "ተርጉምልኝ" አለችው::

††† እርሱም:-
"•ርግብ=ጥበብ (መንፈስ ቅዱስ)
•ዘይት=ጥምቀት
•ቁራ=ክፉ ንጉሥ
•እባብ=መከራ
•ንስር=ድል ነሺነት (ልዑላዊነት)
•አክሊልም=ክብረ ሰማዕታት ነው" ብሎ ተርጉሞ : ክርስቲያን ሆና ይህ ሁሉ እንደሚደረግ ነግሮ ተሰናበታት::

እርሷም ስትጸልይ ቅዱስ መልአክ ተገልጦ አጽናናት:: ያጠምቃትና ያስተምራት ዘንድም ሐዋርያው ቅዱስ ጢሞቴዎስን ልኮላታል:: ሐዋርያውም የቤተ መንግስቱን ግድግዳ ሰንጥቆ ገብቶ : ለሰማያዊ ሙሽርነት የሚያበቃ ትምህርትና ጥምቀትን ሰጥቷት ሔዷል::

ቅድስት ኦርኒም የአባቷን ጣዖታት ቀጥቅጣ ሰብራ ከአባቷ ጋር ተጣላች:: እርሱም "እገድላታለሁ" ብሎ በእንስሳት ጅራት ላይ ጸጉሯን ሲያስር እንስሶቹ ደንብረው : እጁን ገንጥለው መሬት ላይ ጥለው ገደሉት:: ቅድስት ኦርኒ ግን ጸሎት አድርሳ አባቷን ከሞት አስነሳችው:: እጁንም ቀጠለችለት::

በዚህ ምክንያት በዚያች ዕለት ብቻ አባቷና 30,000 የከተማው አሕዛብ አምነው ተጠምቀዋል:: ቅድስት ኦርኒ ግን ኃይለ መንፈስ ቅዱስ ታጥቃ ክርስትናን ሰበከች:: ብዙም ተሰቃየች:: ንጉሡ ዳኬዎስ : ልጁና ሌሎች 2 ያህል ነገሥታት በእሳት : በአራዊት : በግርፋትና በጦር ፈትነዋታል::

እርሷ ግን ሁሉን በኃይለ ክርስቶስ ድል ነስታለች:: ሙታም የተነሳችበት ጊዜ አለ:: በመጨረሻም በዚህች ቀን ወደ ሰማያዊ ርስት (ገነት) ተመስጣለች:: በዘመነ ስብከቷ ካሳመነቻቸው ባሻገር 130,000 የሚያህሉ ሰዎች ለሰማዕትነት እንዲበቁም ምክንያት ሆናለች::

††† ቅዱስ ጐርጐርዮስ ታኦሎጐስ †††

††† ቅዱሱ:-
•የዘመነ ሊቃውንት ፍሬ:
•የእንዚናዙ ኤጲስ ቆጶስ:
•የቁስጥንጥንያ ፓትርያርክ:
•የጉባዔ ቁስጥንጥንያ (በ381 ዓ/ም) 3ኛ ሊቀ መንበር:
•ባለ ብዙ ድርሳን:
•የቂሣርያ (ቀጰዶቅያ) ኮከብ:
•ብሩህ ገዳማዊ:
•መልካም እረኛ የነበረ አባት ነው::
መጽሐፈ ቅዳሴውን ጨምሮ በጻፋቸው ብዙ መጻሕፍትና በስብከቱ ከሊቃውንት ወገን "ታኦ(ዎ)ሎጐስ" ተብሎ የተጠራ እርሱ ብቻ ነው:: ትርጉሙም በግዕዙ "ነባቤ መለኮት" ማለት ነው:: በአማርኛም "አንድነትን : ሦስትነትን የተናገረ (ያመሠጠረ) እንደ ማለት ነው:: ቅዱሱ ዛሬ ዕረፍቱ ነው::

††† አምላከ ቅዱሳን ከበረከታቸው ይክፈለን፡፡
በመጽናታቸውም ያጽናን፡፡

††† እንዲህ ኃጢአታችን ጽዋዑን ሞልቶ በተረፈበት በዚህ ዘመን አንዲት ሰዓትም ውድ የሆነች የንስሃ ዕድሜ ናት:: እግዚአብሔር ግን ደግ ነውና ይሔው ጥርን አስፈጸመን:: ባይገባን ነው እንጂ በዚሕች ወር ውስጥ ሚሊየኖች በደዌ የአልጋ ቁራኛ ሁነዋል::

ሚሊየኖችም ለንስሃ ሳይበቁ እንዲሁ አንቀላፍተዋል (ሙተዋል):: እስኪ እርሱ አምላካችን ቀሪውን ዘመን ደግሞ ለንስሃና ለመልካም ሥራ ባርኮ ይስጠን::

††† ወርኀ ጥርን በቸር ያስፈፀመ አምላከ ቅዱሳን ወርኀ የካቲትን እንዲባርክልን እንለምነው::

††† ጥር 30 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅድስት ሶፍያና ሦስቱ ሰማዕታት ልጆቿ (ጲስጢስ አላጲስና አጋጲስ)
2.ቅድስት ኦርኒ ሰማዕት ( (በ5 ነገሥታት እጅ የተሰቃየች : የሐዋርያው ጢሞቴዎስ ተከታይና ወደ ብሔረ ሕያዋን የተነጠቀች እናት)
3.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት
4.አባ አክርስጥሮስ
5.አምስቱ ደናግል ሰማዕታት (ጤቅላ: ማርያ: ማርታ: አበያ: ዓመታ)
6.ጻድቃነ ዴጌ (የተሠወሩበት)
7.አባ ሚናስ ሊቀ ጳጳሳት
8."130,000" ሰማዕታት (የቅድስት ኦርኒ ማኅበር)

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ማርቆስ ዘአንበሳ
2.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
3.አባ ሣሉሲ ክቡር

††† "ለእናንተም ጠጉርን በመሸረብና ወርቅን በማንጠልጠል ወይም ልብስን በመጐናጸፍ በውጭ የሆነ ሽልማት አይሁንላችሁ:: ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ::" †††
(፩ጴጥ. ፫፥፫)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††






የንስሐ ጸሎት (በቅዱስ ኤፍሬም)
ምን ዓይነት ጊዜ ነው
ጌታዬ ሆይ! ይቅር በለኝ ወደ አንተ በንስሐ እመለስ ዘንድም ብርታትን ስጠኝ፡፡ እንደ ቅዱስ ፈቃድህ በቅድስና እመላለስ ዘንድ ወደ አንተ መልሰኝ፡፡ የአጋንንት መኖሪያና ጎሬ የሆነውን ልቡናዬን እባክህ ቀድሰው፡፡
ጌታዬ ሆይ! እኔ ከአንተ ዘንድ ለራሴ ይቅርታን እጠይቅ ዘንድ የማይገባኝ ጎስቋላ ሰው ነኝ፡፡ በተደጋጋሚ ንስሐ ለመግባት ቃል እገባና ለራሴ የገባሁትን ቃል መጠበቅ ተስኖኝ ዋሾ ሆኜ እገኛለሁ፡፡ አንተ ከወደቅሁበት የኃጢአት አዘቅት በተደጋጋሚ ብታወጣኝም እኔ ግን በገዛ ፈቃዴ በደጋጋሚ በኃጢአት ተሰነካክዬ እወድቃለሁ፡፡ ስለዚህም ጌታዬ ሆይ! በራሴ ላይ እፈርዳለሁ በመተላለፌ ከአንተ ዘንድ የሚመጣብኝን ቅጣት ሁሉ በጸጋ እቀበላለሁ፡፡ አምላኬ ሆይ! ስንቴ ጨለማ የወረሰውን ልቡናዬን በጸጋህ ብርሃንህ አበራኸው? እኔ ግን ተመልሼ ወደ ተናቀውና ከንቱ ወደሆነው አስተሳሰብ ተመለስሁ፡፡ ይህን ባሰብኩ ቁጥር ሰውነቴ በፍርሃት ይርዳል፡፡ ነገር ግን የኃጢአት ፈቃዴ አይሎ በኃጢአት አዘቅት ውስጥ በተደጋጋሚ እወድቃለሁ፡፡
ጌታ ሆይ ለእኔ ያሳየኸኝን የቸርነትህን ብዛት ዘርዝሬ ልጨርሰው እንዴት ይቻለኛል? እነዚህ ጸጋዎችህን ለእኔ ለማይገባኝ ሰው ሰጠሃቸው፤ ነገር ግን በስንፍናዬ በከንቱ አጠፋዋቸው፡፡ አንዳች ፍሬ ሳላፈራም ዘመኔን ጨረስኩት፡፡ አንተ በበረከቶችህ ሞላኸኝ እኔ ግን ለቸርነትህ አመፃን በብድራት መለስኩብህ ፡፡
ነገር ግን ጌታ ሆይ! እንደ ታጋሽነትህና እንደ ርኅራኄህ መጠን ፍሬ አፍርታ እንዳልተገኘችው የበለስ ዛፍ ለዘለዓለም ነቅለህ እንዳትጥለኝ እለምንሃለሁ፡፡ ለዘለዓለም ሕይወት የሚያበቃ ፍሬን ሳላፈራ በዘለዓለማዊ እሳት እንዳታጠፋኝ እማጸንሃለሁ፡፡ ጌታዬ ሆይ! ለፍርድ በመጣህ ጊዜ አንተን ለመቀበል ሳልዘጋጅ እንዳልገኝ ጠብቀኝ፡፡ ድንገት በመጣህ ጊዜ የዘይት ማሰሮዬ ሞልቶ መብራቴን ከዘይቴ ጋር ይዤ እገኝ ዘንድ እርዳኝ፡፡ የሰርግ ልብሴን ሳልለብስ በመገኘቴ ከሰርግህ ቤትህ ወደ ውጭ እንዳልጣል አድነኝ፡፡ አንተ ርኅሩኅ ጌታና ሰውን የምትወድድ ነህና ምህረትህ በእኔ ላይ ትብዛ፡፡ ጌታ ሆይ! ለፍርድ በመጣህ ጊዜ ነፍሴ በኃጢአት ተዳድፋና ከጸጋህ ተራቁታ እንዳትገኝ የንስሐ እድሜን ስጠኝ፡፡
ጌታ ሆይ! ጻድቅ በጭንቅ የሚድን ከሆነ የእኔ ከንቱና ኃጢአተኛ ሰው መጨረሻ ምን ይሆን? ወደ ሕይወት የምታደርሰው መንገድ ቀጭንና ጠባብ ከሆነች በቅምጥልነት የምኖረውና ለዓለማዊ ደስታ የምተጋው ሰው እጣ ፈንታዬ ምን ይሆን? ነገር ግን ጌታዬና መድኀኒቴ እንዲሁም ለእውነተኛ አምላክ እውነተኛው ልጁ የሆንክ ጌታዬ ክርስቶስ ሆይ! እንደ ፈቃድህና አንተ ለእኔ እንደምትመኛት ምኞት እንድኖር አብቃኝ፡፡ በአንተ ጸጋ ብቻ እንዳው በከንቱ በሰውነቴ ውስጥ ያደረውን የኃጢአት ፈቃድ አውጥተህ ጣልልኝ፡፡ ጌታዬ ሆይ እኔን ታድነኝ ዘንድ ፈቀድ፡፡ እጅግ ርኅሩኅና መሐሪ ለሆንከው ጌታ ምስጋና ይሁን ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለሙ አሜን!
ትርጉም በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
እግዚአብሔር ለንስሀ ሞት ያብቃን አሜን በእውነት😔


"ዛሬ_በዓለ_ወልድ_ነው_29
በዓለ ወልድ ማለት ወር በገባ በ 29ኛው ቀን የሚከበር በአል ነው። የስሙ ትርጓሜም የወልድ በአል ማለት ነው።ይህም ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዲያብሎስን ስራ ለማፍረስ፣የሰውን ልጅ ነፃ ለማውጣት ሲል ከእናታችን ከድንግል ማርያም መጋቢት 29 ቀን የተፀነሰበት ታህሳስ 29 ቀን የተወለደበት ቅዱስ እለት ስለሆነ በየ ወሩ ይታሰባል።እኛን ለማዳን እንደ ሰው ዘር ብሄር ሳይል ለኛ ሀጢያት እርሱ ዋጋውን ሊከፍል ሊገረፍ ሊሞትልን ወደዚህች ምድር መጣ ቅዱስ በዓለ ወልድ ከክፉ ጥበቃው አይለየን🙏

1.6k 0 26 11 59

Forward from: "ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒
መልክአ ኢየሱስ📚

አምላከ ምድር ወሰማያት፡፡
የሰማይና የምድር አምላክ ሆይ፤ የባሕርና የቀላያት አምላክ ሆይ፤ የፍጥረቱ ሁሉ አምላክ ሆይ፤ የቀደሙ የአባቶቻችን አምላክ ሆይ፤ የመላእክት አምላክ ሆይ፤ የነቢያትና የሐዋርያት አምላካቸው ሆይ፤ የጻድቃንና የሰማዕታት አምላክ ሆይ፤ አቤቱ ሁላችንን ማረን ይቅር በለን፡፡ በደላችንንም አታስብብን፡፡ የእጅህ ሥራዎች ነንና፡፡የእኔንም የአገልጋይህን የወለተ ሥላሴን እንዲሁም ሙሉ የጥምቀት ልጆች በደላችንን ፋቅልን አጥፋልን አሜን፡፡


✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"📖ምሳ 1፥33☦📚
        
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
📗ስንክሳር ዘወርኃ ጥር ፳፱/29

ወለተ ሥላሴ ብላችሁ በጸሎታችሁ አስቡኝ
https://t.me/Orthodoxtewahdoc
🌹የያዕቆብ ሌሊት ይሁንልን🕊

20 last posts shown.