Fana broadcasting ኢስላምን የማይወክል ክህደት ነው ያስተላላፋችሁት፡፡
ገታ ላይ የሚከበረው መውሊድ ብላችሁት ያቀረባችሁት ፕሮግራም ኢስላምን አይወክልም፡፡ ኢስላምን አይወክልም ከምንልበት ምክንያቶች ውስጥ አንዱ፣ ከአላህ ውጭ ያሉ ሙታንን፣ በቦታው ላይ የሌሉ ፍጡራንን ካለሁበት መከራ እና ችግር አውጡኝ ማለት በአላህ ላይ ማጋራት “ሺርክ” ነው፡፡ ይህም ታላቅ በደል ነው፡፡ በአላህ ላይ እያጋራ የሞተ ሰው ዘላለም አለሙን ገሃነም (ጀሃነም) ውስጥ ነዋሪ ነው፡፡ ገነት (ጀነትም) በእርሱ ላይ እርም ናት፡፡
ፋና ቴሌቭዥን ያስተላለፋቸው ሌሎች ጥፋቶችን ለሌላ ጊዜ በሰፊው በአላህ ፍቃድ እናያቸዋለን፡፡ ለአሁኑ የቀብር አስጎብኚ የተባለው ግለሰብ አንድ በጣልያን ወታደሮች እርምጃ ሊወሰድበት የነበረ ግለሰብ የሚከተለውን ንግግር (ኢስላምን የሚቃረን) ተናግሮ ዳነ ይላል፡፡
“የሰይድ ቡሽራ ያለህ ከዚህ በዓት አውጡኝ ብሎ ይጣራል” ተሰወራቸው…….፡፡
በነብያት ሁሉ ሃይማኖት እስልምና ካለሁበት መከራ አውጣኝ፣ ድረስልኝ የሚባለው የፍጡራን ሁሉ ፈጣሪ፣ የማያንቀላፋው፣ የማይተኛው፣ የማይሞተው፣ ህያው፣ ሁሉን በማድረግ ላይ ቻይ የሆነው፣ ከ 7 ሰማያት በላይ ያለው አላህ ብቻ እና ብቻ ነው፡፡ ከዚህ ውጭ ሙታን የሆኑ የገታው ሸህም ይሁን፣ የቦረናውን መጥራት ታላቁ በደል (በአላህ ላይ ማጋራት) ነው፡፡
ሚድያዎች ሆይ! አትድረሱብን፡፡ ይህን ክህደት ነባሩ እስልምና ነው አትበሉን፡፡ ነባሩ የጥንት የጠዋቱ እስልምና ብቸኛው ፈጣሪያችንን አላህን እንጂ ማንንም ፍጡር አይለምንም፡፡ ሙስሊሞች ሆይ! የሙስሊሞች በአል እና ሌሎች ሙስሊሞችን የሚመለከት ፕሮግራሞች ናቸው የሚባሉትን በቴሌቪዥን ሲተላለፉ ከኢስላም ጋር የሚጋጩትን አንጥረን እያወጣን የማያውቁ ሙስሊም ማህበረሰቦች እንደዚህ አይነት ክህደቶችን እንዳይቀበሉ ልናስተምር እና ልናስጠነቅቃቸው ይገባል፡፡
አላህ ይርዳን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts