የቅዱሳን ታሪክ


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


በዚህ ቻናል ውስጥ፦
በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ብቻ የሚገኙ ስዕላትን
የቤተክርስቲያን ትውፊት የጠበቁ ስዕላት የአድባራት እና የገዳማት ፎቶዎችን ያገኛሉ

የተለያዩ ስዕለ አድዕኖ ለመላክ
@kidanemiherat_bot

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


Forward from: አምኀ ተዋኅዶ ዘክርስቶስ
#ቃና_ዘገሊላ_በአባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ

ወይን የኾነ የቃና ውኀ በመጭመቂያ ጨምቀው በመጥመቂያ ውስጥ የጠመቁት የልማድ ወይን አይደለም ሙሽራ እንዳያፍር ሰርገኞችም እንዲረኩ የተሰጠ የእግዚአብሔር ልጅ የተዐምራቱ ወይን ነው እንጂ፡፡

የጌታ ኢየሱስ እናቱ ወይን እኮ የላቸውም እባክህ ይህን ችግር አስወግድ ብላዋለችና ጌታ ኢየሱስም አንቺ ሴት ከአንቺ ምን አለኝ ገና ጊዜዬ አልደረሰምና አላት በልቡ ለተከማቸ ፍቅሯ በሚሻል ነገር መለሰላት ስለምድራዊ ወይን ለመነችው እርሱም ከጐኑ ስለሚፈሰው የደሙ ወይን በምሥጢር መለሰ፡፡

ጊዜዬ አልደረሰም ያለው የአባቴን ድንቆች በምገልጥበት ከአንቺም በነሣሁት ሥጋ ረኃብንና ጥምን ጭንቁንም ኹሉ በምቀበልበት ከኀጥአን ጋራ በምቀመጥበት አመንዝሮችንም በማነጻበት ሦስት ዓመታት ቀርተውኛልና ከጐኔ በፈሰሰ የምሥጢር ወይን ምእመናንን አረካቸው ዘንድ የምወጋበት ሰዓት አልደረሰም ተብሎ ይተረጐማል፡፡ ይኽን ስለ ተዐምራቱ ወይን ተናግሮታል የሚል ቢኖር እኔም ጊዜው እኮ ደረሰ ማድረጉንም አላዘገየም እለዋለሁ

ያንጊዜም ውኀውን ቀድተው በስድስቱ የደንጊያ ጋኖች እንዲጨምሩ አዘዘ ባሕርዩም ወይን ወደመኾን ተለወጠ ጋኖች ውኀውን ወይን ወደመኾን የለወጡት አይደለም እርሱ ወደጋኖች እንዲቀዱት ያዘዘውን ውኀ ወይን ወደ መኾን ለወጠው እንጂ ጋኖች ውኀውን ወይን የሚለውጡትስ ቢኾን አይሁድ ዘወትር ኹለት ኹለት ሦስት ሦስት ማድጋ በሚይዙ በእነዚያ ጋኖች ውስጥ የሚያጠሩባቸው አይደሉምን፡፡

የቃና ወይን በኦሪት ሕግ ተመሰለች የጠጧትን አላጸደቀቻቸውምና ነገር ግን በመዓዛዋ ጣፋጭነት ልባቸውን ደስ አሰኘች እንዲሁ ኦሪትም ቀድመው የተቀበሏትን አላጸደቀቻቸውም የእግዚአብሔር ቃል ናትና እርሷን በመስማትም ልባቸውን ደስ አሰኘች ስለዚህም ነገር ጳውሎስ በኦሪት ሕግ መጽደቅ በተሳናቸው ጊዜ እግዚአብሔር ልጁን ላከ ከሴትም ተወለደ በኦሪት ያሉትንም ይዋጅ ዘንድ የኦሪትን ሕግ ፈጸመ አለ፡፡

ውኀው በቃና ወይን ወደመኾን እንደተለወጠ እንዲሁ የሙሴ በትር በደብረ ሲና ነቢዩ ከፊቱ እስኪሸሽ ድረስ የሚንቀሳቀስ እባብ ወደ መኾን ተለወጠ ኹለተኛም ነቢዩ ጐንበስ ብሎ እስኪያነሣው ድረስ በትር ወደ መኾን ተመለሰ በዚያም በትር በፈርዖንና በታላላቆቹ ፊት ተዐምራትን አደረገ የጌታ ኢየሱስም የደሙ ወይን በወንጌል ሕግ ተመሰለ ማርካትና ማጽደቅን ችሏል መድኃኒታችን ሥጋዬ እውነተኛ የጽድቅ ምግብ ነው ደሜም እውነተኛ የሕይወት ውኃ ነው ሥጋዬን የበላ የእኔን ሥጋ ስለበላ በሕይወት ይኖራል ደሜንም የጠጣ ሞትን አይቀምሰውም ብሏል እኮን ስለወንጌሉም ያመነ የተጠመቀ ሁሉ ይድናል ያላመነ ግን ይፈረድበታል አለ፡፡

የአምላክን እናት ከልጇ ዘንድ ወይንን ወደ መፈለግ ዜና እንመለስ ወይን እኮ የላቸውም ወይናቸው አልቋልና ብላ ስለምን ለመነችው ከውኀ ወይን እንደሚቀዳ ዐወቀችን ወንጌላዊው ዮሐንስ ይኽም ጌታ ኢየሱስ በቃና ዘገሊላ ያደረገውን ተዐምር የመጀመሪያው ነው ክብሩን አሳያቸው ደቀመዛሙርቱም አመኑበት እንዳለ ከዚያን ጊዜ በፊት እንደዚህ አላደረገምና፡፡

ድንግልስ ውኀውን ወይን ወደ መሆን እንደሚለውጠው አላወቀችም ነገር ግን በአብ ጥላ እንደፀነሰችው በልዑል ኃይልም እንደ ወለደችው ታውቃለችና ስለዚህም ድንግል የምሥራቹን ከነገራት መልአክ ዘንድ አባቱ ሰማያዊ እንደኾነ ተረድታለችና ስለወይን ማለደችው ስለዚህም ነገር በልቧ ድንቆችን የሚያደርግ የእርሱ ልጅ እንደ አባቱ ድንቅ ያደርጋልና ደቀ መዛሙርቱ ስለ ወይን አልማለዱትም ለእናቱም እንደነገራት መልአኩ አልነገራቸውምና የዮሴፍ ልጅ ይመስላቸው ነበር ተዐምራትንም ካደረገ በኋላ ከነቢያት አንዱ እንደኾነ እንጂ የእግዚአብሔር ልጅ እንደኾነ አላመኑበትም.....

#እንኳን_አደረሳችሁ_መልካም_በዓለ_ቃና_ዘገሊላ!

#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ!

አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube

Sador Sisay on Youtube

Sador Sisay on Instagram

Sador Sisay on Facebook

Sador Sisay on Tiktok

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏


Forward from: አምኀ ተዋኅዶ ዘክርስቶስ
#ቃና_ዘገሊላ

እኛ ስንጨርስ እሱ የሚጀምር አምላክ ስቡሕ ዘተሰብሐ፡፡

በቃና ሰዎች የተዘጋጁበት ኹሉ አለቀ፡፡ የሰው ዝግጅት ሲያልቅ የማያልቀው የእግዚአብሔር ተአምር ጀመረ፡፡

የማያልቀው ወይን እንዲቀዳ ልጇም ተአምሩን ይጀምር ዘንድ ምክንያት የኾነች "የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች፡፡"

ይኽ ታሪክ የአንድ የሰርግ ቤት ታሪክ ብቻ አይደለም ይኽ የዐለም ታሪክ ነው፡፡ ስድስቱ ጋኖች ስድስት ሺ ዘመናትን ይወክላሉ 5500 ዐመተ ፍዳን ማለት ነው፡፡

በስድስት ሺ የዘመን ጋኖች ውስጥ የነበረው ትንቢትና ተስፋ ሲያልቅ 'እኔ የወይን ግንድ ነኝ' ብሎ የነገረን ጣፋጩ ወይን ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም መወለዱን… ያስረዳል፡፡


Forward from: አምኀ ተዋኅዶ ዘክርስቶስ
#ወናሁ_ተርኅወ_ሰማይ_እነሆ_ሰማይ_ተከፈተ ማቴ፡3፥16

#ሰማይ_የተዘጋ_ቤት_አይደለም እንደ ቤተ መቅደስ መጋረጃ የለውም ነገር ግን በሰውና በእግዚአብሔር መካከል የኀጢአት መጋረጃ የጥንተ አብሶ ተራራ ነበር።

ሰማይም ሳይከፈት ምሥጢራት ሳይገለጡ ዘመናት ተቆጥረዋል ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮርዳኖስ ሲጠመቅ ሰማይ ተከፈተ ድንቅ ምሥጢር ተገለጠ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ከራሱ ላይ ተቀመጠ አብ በደመና አብ የምወደው ልጄ ይህ ነው እረሱን ስሙት አለ ሰማይ ተከፈተ አንድነት ሦስትነት በዮርዳኖስ ተገለጠ የሰማይ መዝጊያው የበደል ደብዳቤ ተቀደደ።

#ሰውና_እግዚአብሔር _አባትና_ልጅ_ሆኑ።

ሰማይ ተከፈተ የመንግሥተ ሰማይ መግቢያ የሆነው የልጅነት ጥምቀታችን በጌታ መጠመቅ ተቀደሰ ኀይል አገኘ።

ሰማያዊ እሳት በዮርዳኖስ ውኀ ላይ በቆመ ጊዜ ውኀው ፈላ እንጅ አሳቱ አልጠፋም።

ለልማዱ በውኋ ላይ አሳት ይጠፋል አይነድም እርሱ ግን የማይጠፋ እሳት ነውና ባሕሩን አፈላው የጥምቀት ውኀ በራሱ ጊዜ ፍል ውኀ ሆነ።

ዛሬ ብዙ ምእመናን ምሥጢሩን ባለማወቅ ልጆቻቸውን ክርስትና ሲያስነሱ ውኀ አሙቀው በፔርሙዝ ተሸክመው ቤተ ክርስቲያን ድረስ ያመጣሉ ቀሳውስቱንም ያስቸግራሉ።

በውኑ ከእናቶቻችን እስቶቭ ከእኅቶቻችን የምድጃ ክሰል ይልቅ የመንፈስ ቅዱስ እሳትነት ውኀውን እንደሚያፈላው ልጃቸው በሙቀተ መንፈስ ቅዱስ እንደሚጠመቅ ዮርዳኖስን መመልከት አልነበረባቸውምን?

የማይጠፋ አሳት ሊያድረበት የተዘጋጀን ሕፃን በሚጠፋ አሳት መለብለብ ከስሕተት በላይነው ሰማይ ሲከፈት መንፈስ ቅዱስ ሲወርድ ልማድ ይቀየራል።

#እንኳን_ለብርሀነ_ጥምቀቱ_አደረሳችሁ

#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ!

አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube

Sador Sisay on Youtube

Sador Sisay on Instagram

Sador Sisay on Facebook

Sador Sisay on Tiktok

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏




Forward from: አምኀ ተዋኅዶ ዘክርስቶስ
#ይህ_የሐዲስ_ኪዳኑ_ታቦት_ግን...

የኦሪት ጽላት እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን የሚያነጋግርበት በደመና ተከናንቦ ለእስራኤል ብቻ በረድኤት የሚገለጥበት ዙፋን ነበር፡፡

ይህ የሐዲስ ኪዳኑ ታቦት ግን የአምላክ ሥጋና ደም የሚፈተትበት ( ጌታችን ) ሥጋዬን የበላ ደሜን የጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው ሥጋዬን ብሉ ደሜን ጠጡ እያለ ያመኑትን የሚጠራበት የምሕረት
ምሥዋዕ ( መሠዊያ ) ነው፡፡

እናም ለታቦት ክብርና ስግደትም የሚደረግለት ለዚህ ነው በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት በታቦታቱ ሁሉ ላይ የተጻፈው ‹‹ አልፋና ኦሜጋ ›› የሚለው የመድኃኔ ዐለም ክርስቶስ ስም ነው።

ከስሙ ጋር ደግሞ በሁሉም ታቦታት ላይ የሚከተለው ጥቅስ በግእዝ ተጽፏል፡፡ ‹‹ ከመ ለስሙ ለኢየሱስ ክርስቶስ ይስግድ ኲሉ ብርክ ዘበሰማያት ወዘበምድር ›› ‹‹ ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ ›› የሚል ነው ፡፡ ፊልጵ 2፥10

በታቦቱ ፊት የሚሰግድ ሰው ለምን እንደሚሰግድ በታቦቱ ላይ የሚጻፈው ይህ ጥቅስ ያስረዳናል ምክንያቱ ‹‹ ጉልበት ሁሉ ለኢየሱስ ስም ይሰግዱ ዘንድ ›› ስለሚገባ ነው ፡፡

የክርስቶስ ሥጋ እንደሚቆረስ ደሙ እንደሚፈስስ የሚያምን ሰው በዚህ መሠዊያ ፊት በፍርሃት ለክርስቶስ ይሰግዳል ፡፡

ሥጋ ወደሙን ‹‹ ተራ መታሰቢያ ብቻ ነው ›› የሚል ሰው ግን በመሠዊያው ፊት እንዲሰግድና መሠዊያውን እንዲያከብር አንጠብቅም ፡፡

የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በታቦቷ ጽፋ ክብር የምትሠጥ የሐዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን ልጆች ስለሆንን እግዚአብሔርን እናመሰግናለን ፡፡

#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ!

አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube

Sador Sisay on Youtube

Sador Sisay on Instagram

Sador Sisay on Facebook

Sador Sisay on Tiktok

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏




Forward from: አምኀ ተዋኅዶ ዘክርስቶስ
#ከገሊላ_ወደ_ዮርዳኖስ

የሔሮድስ ከተማ ገሊላ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የትውልድም የስብከትም አገሩ ናት።

ከገሊላ ነቢይ አይነሣም ዮሐ. 7፥52 የሚል አባባል በአይሁድ ዘንድ የተለመደ ቢሆንም ኢየሱስ ክርስቶስ አይሁድ በማያውቁት መንገድ በገሊላ መምህር ሆኖ ተነሣ።

ሔሮድስ አስጨንቆ ለሚገዛው ሕዝብ “በጨለማ የሚኖር ሕዝብ ታላቅ ብርሃን አየ በሞት ጥላ አገር ለሚኖሩትም ታላቅ ብርሃን ወጣላቸው” ማቴ. 4፥16 የተባለው ቃል ሊፈጸምላቸው አይገባምን?

የአይሑድ ሊቃውንት በመሠዊያው አጠገብ ስለሚኖሩ የእግዚአብሔር ማዳን ቀድማ እንደምትደረግላቸው ያስቡ ነበር እንጅ እሱስ የማዳን ሥራውን የጀመረው በገሊላ ነበር። የማዳን ሥራውን ለሕዝቡ መስጠት የሚጀምረው ”መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ” ብሎ ማስተማር በጀመረበት ጊዜ ነውና ይህንን የመንግሥተ ሰማያት ምሥጢር ማሰማት የሚጀምርባትን ገሊላ ዛሬ ግን ትቷት ወደ ዮርዳኖስ ምድረ በዳ እየሄደ ነው።

በዚያ ቦታ የቆየ ቃል አለውና ያንን ሊፈጽም ይጓዛል።
በኢያሱ ጊዜ በዮርዳኖስ ውኃ ዳር ድንቅ ነገርን እንደሚያደርግ ተናግሮ ነበር ኢያ. 3፥5
ያንን ድንቅ ነገር ሊያሳየን ዛሬ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ሄደ።
ኢያሱ “ሕያው አምላክ በመካከላችሁ እንዳለ....በዚህ ታውቃላችሁ” ብሎ ነበር።

ከልደቱ ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ኢየሱስ ክርስቶስ በመካከላችን ሲኖር በጉባኤ፣ በዐዋጅ ነጋሪ ቃል ተለይቶ አልታወቀልንም ነበር፤ ከዛሬ ጀምሮ ግን በመካከላችን የሚኖር እግዚአብሔር እሱ መሆኑን የሚያስረዱ ብዙ ምስክሮች ያሉን ስለሆነ አይተነዋል፤ እናውቀውማለን።

ዐዋጅ ነጋሪው ዮሐንስ “ከእኔ በፊት ነበረ ከእኔም በኋላ ይመጣል” ዮሐ. 1፥30 ብሎ ሲነግረን አብም በደመና ሆኖ “የምወደው ልጄ ይህ ነው” ብሎ የባሕርይ ልጁ መሆኑን ሲያስረዳን፣ መንፈስ ቅዱስም በራሱ ላይ ሆኖ ሲገለጥልን በእርግጥም ሕያው አምላክ በመካከላችን መሆኑን ወደ ዮርዳኖስ ብንወርድ ዛሬ እናውቃለን።

የተስፋይቱን ምድር ሊወርስ የተጠራው ሕዝብ እየመጣ ያለው በዚህ በኩል ነውና ኢየሱስ ክርስቶስ ሊቀበላቸው ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ወጣ።

አባቶቻችንን “በዮርዳኖስ ውስጥ ቁሙ” ብሎ በቀጠረበት ቦታ ለመገኘት ወደ ዮርዳኖስ ሄደ። በደረሰ ጊዜ “ነገ እግዚአብሔር በመካከላችሁ ድንቅ ነገርን ያደርጋልና ተቀደሱ” ኢያ. 3፥5 ብሎ ኢያሱ የቀጠራቸውን ሕዝቦች ቅዱስ ዮሐንስ “ለንስሐ የሚገባ ፍሬን አድርጉ” ማቴ. 3፥8 እያለ ለቅድስና የሚያበቃውን ትምህርት ሲያስተምራቸው አገኘው።

የኢያሱ ጉባኤ መምህሩ ተቀይሮ ትምህርቱ ተገልጦ አገኘው።
ኢያሱ “ተቀደሱ” ብቻ ብሏል እንጅ ምን ቢያደርጉ እንደሚቀደሱ አልነገራቸውም ነበር የቀረውን ትምህርት ደግሞ ዮሐንስ ገልጦ ንስሐ መሆኑን ነገራቸው።

የመቀደስ ዘመን ስላልደረሰ ሰውን የምትቀድስ የንስሐ ጥምቀትም በሰው ፊት ሳትገለጥ ቆይታ ነበርና ዮሐንስ ዛሬ ገለጣት።
አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ዮርዳኖስ ሂዶ ከመላእክት ጉባኤ የተጨመረ እንዳይመስላችሁ፤ ቀራጮችና ጭፍሮች ኃጢአታቸውን እየተናዘዙ ሊጠመቁ ወደ ተሰበሰቡበት ጉባኤ ገባ።
ሕያው ወደ ሙታን ጉባኤ በፈቃዱ ይገባልን? ጻድቁስ በኃጥአን መካከል ቢኖር መልካም ነውን? አወ በከተማ ካሉት ኃጢታቸውን አምነው ከማይናዘዙ ሙታን ይልቅ ኃጢአታቸውን አምነው የሚናዘዙ ኃጥአንን ይወዳልና እነሱ ወዳሉበት መጣ።
የጨረቃ በጨለማ መካከል መውጣት ለሰው ብርሃንን እንደሚሰጥ የክርስቶስም በኃጥአን መካከል መገኘቱ ለኃጥአን ተስፋን ይሰጣል።
ከዮሐንስ በቀር ማንም ሳያውቀው በዚህ ጉባኤ መካከል አደረ።

ቤተ ክርስቲያናችንም ዛሬ ታቦታቱን ከቤተ መቅደስ ይዛ በመውጣት የጌታችንን ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ያደረገውን ጉዞ ታስታውሳለች።
ገዳም ሲሄድ ተከትላው ገዳም የገባች ቤተ ክርስቲያን ወደ መጠመቂያው ስፍራ ሲገባም ተከትላው እንደምትገባ የታመነች መሆኗን ታሳያለች።

ኢያሱ ታቦቱን የተሸከሙ ካህናት በሰፈር ባለፉ ጊዜ ሕዝቡ እንዲከተል እንዳዘዘ ዛሬ ታቦታችንን ተከትለን እንወጣለን። ወደ መጠመቂያው ስፍራ ደርሰን በድንኳን በተቀመጥን ጊዜ ለመጠመቅ ተራውን ሲጠብቅ ያደረውን ክርስቶስን በዐይነ ሕሊናችን እንመለከተዋለን።
ክርስቲያኖች ሆይ! “ኑ ተከተሉኝ” ብሎ አብረነው እንድንጓዝ ሰለፈቀደልን የምናደርገው ጉዞ መሆኑን እያሰብን እንጓዝ።
ከቤተ መቅደስ ተነሥተን ጉዞ ከጀመርንበት ጊዜ ጀምሮ ከፊት ከፊታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እያየን ልንጓዝ ይገባናል እንጅ በሳቅና በጨዋታ በዘፈንና በእስክስታ እንዳይሆን መጠንቀቅ ይገባናል።

እንኳን ኢየሱስ ክርስቶስን ተከትለን ይቅርና ኤልያስን የተከተለው ደቀ መዝሙር ዕጥፍ ድርብ ጸጋ የተቀበለው በዚህ አሁን ኢየሱስ ክርስቶስ በሄደበት መንገድ አይደለምን?
የእኛማ እንዴታ!
ጸጋ የምናገኝበት በዓል ያድርግልን፤

#ስምዐኮነ_መልአከ

#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ!

አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube

Sador Sisay on Youtube

Sador Sisay on Instagram

Sador Sisay on Facebook

Sador Sisay on Tiktok

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏




Forward from: አምኀ ተዋኅዶ ዘክርስቶስ
#እንኳን_ለከተራ_በዓል_አደረሳችሁ!

#የከተራ_በዓል_ምሳሌያት

በበዓለ ጥምቀት ዋዜማ የታቦታቱ ወደ ወንዝ መውረድና የባሕረ ጥምቀቱ መዘጋጀት ሃይማኖታዊ ታሪክና ምሳሌ አለው፡፡ የቃል ኪዳኑን ታቦት አክብሮ መጓዝና ወደ ወንዝ መወረድ የተጀመረው በአሮን ልጅ በአልዓዛር ጊዜ ነው፡፡ ኢያሱ በሙሴ እግር ተተክቶ ሕዝበ እስራኤልን እየመራ ከዮርዳኖስ ወንዝ ሲደርስ ባሕሩ ከሁለት ይከፈልና ወራጁም ይቆም/ይከተር/ ነበር፡፡ እስራኤል ዘሥጋ ወደ ምድረ ርስት ለመግባት የዮርዳኖስን ወንዝ ሲሻገሩ፡- ድንኳን ጥለው የቃል ኪዳኑን ታቦት በድንኳን ውስጥ አድርገው ሌዋውያኑ በዙሪያው፣ ካህናቱ ደግሞ በውስጥ ኾነው እግዚአብሔርን እያመሰገኑ አድረው በማለዳ ተሻግረዋል /ኢያሱ 3÷8-9/፡፡ ካህናቱ የቃል ኪዳኑን ታቦት አክብረው የወንዙን ዳርቻ በረገጡት ጊዜ እንደ ክረምት ማዕበል ይወርድ የነበረው ውኃ ግራና ቀኝ ተከፍሎ እንደ ግድግዳ ወደ ላይ ቆሟል፡፡

ሕዝቡ ተሻግሮ እስከሚያበቃ ታቦተ ጽዮንን ያከበሩት ካህናት ከወንዙ መሐል ይቆሙ ነበር፡፡ በዚህ መሠረት ‹‹ወተጠምቃ እገሪሆሙ ለካህናት›› ይህም ‹‹የካህናት እግሮቻቸው የዮርዳኖስን ውኃ በመርገጣቸው እንደ ጥምቀት ሆናቸው›› በሐዲስ ኪዳነ ጌታችን ለመሠረተው ሥርዐተ ጥምቀት ምሳሌ ነበር፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን የጥምቀትን ዋዜማ ከተራ ብላ የጠራችው ከዚህ በመነሣት ነው፡፡

ጌታችን በተጠመቀ ጊዜ የዮርዳኖስ ወንዝ የላይኛው ሸሽቶ ወደ ላይ ተመልሶ ሽቅብ ፈሷል፡፡ የታቹም ወደ ታች ሸሽቷል፡፡ የላይኛው ፈሳሽ ተቋርጦ እንደ ክምር ተቆልሎ ቀርቷል።ቅዱስ ዳዊት የተመለከተውም ይህንኑ ነው። ከአዳም ጀምሮ እስከ ክርስቶስ ድረስ በዘር ይወርድ የነበረው ፍዳ መርገም በክርስቶስ ቤዛነት ተቋርጦ ፤ የታቹም ፈጽሞ መድረቁ ኀጢአተ አዳም የመጥፋቱ ምሳሌ ነው፡፡ እስራኤል ፈለገ ዮርዳኖስን ተሻግረው ወደ ኢያሪኮ መሔዳቸው ምእመናን በጥምቀት ከኀጢአት ቍራኝነት ተላቀው እግራቸውን ወደ ልምላሜ ገነት ወደ ዕረፍተ መንግሥተ ሰማያት አቅንተው ለመሔዳቸው ምሳሌ ነው፡፡ ኢያሱ የጌታ፣ እስራኤል የምእመናን፣ ዮርዳኖስ የጥምቀት፣ ምድረ ርስት የገነት መንግሥተ ሰማያት ምሳሌ ነው፡፡

ታቦቱን አክብሮ የሚሔደው ካህን የቅዱስ ዮሐንስ፣ታቦቱ የጌታችን፣ ባሕረ ጥምቀቱ የዮርዳኖስ ወንዝ፣ ታቦታቱን አጅበው የሚሔዱትና በዓሉን የሚያከብሩት ምእመናን ወደ ቅዱስ ዮሐንስ እየመጡ የንስሐ ጥምቀት ሲጠመቁ የነበሩት ሰዎች ምሳሌዎች ናቸው፡፡ ታቦታቱ በጥምቀት ዋዜማ ከመንበራቸው ወደ ጥምቀተ ባሕር መውረዳቸውና በዚያ ማደራቸው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ በፈለገ ዮርዳኖስ ከማታው ጀምሮ መውረዱንና ተሰልፎ ተራውን ሲጠብቅ ማደሩን ያጠይቃል፡፡ ‹‹ጥምቀት የሞቱና የትንሣኤው ምሳሌ ነው፡፡ ከኃጥአን ጋር ተቆጥሮ እንዲጠመቅና እንዲሰቀል የተጻፈውን ቃል ንስሐና ጥምቀት የማያስፈልገው ሲሆን ነገር ግን ፍጹም ኃጥእ መስሎ በዮሐንስ እጅ ጥምቀትን ለመፈጸም በማየ ዮርዳኖስ ተጠመቀ፡፡››
ጌታችን የተጠመቀበት ወርኀ ጥር በእስራኤላውያን ዘንድ የዝናብ፣ የበረዶ ወራት ነው፡፡ ከወንዝ ዳር ያለ መጠለያ መዋልና ማደር አይቻልም፡፡ በመኾኑም ከዮሐንስ ለመጠመቅ የሚሄዱ ሰዎች ሁሉ በዮርዳኖስ ዙሪያ ድንኳናቸውን ተክለው ያርፉ ነበር፡፡ በዚህ አንጻር ዛሬም በባሕረ ጥምቀት ዙሪያ ድንኳኖች ዳሶች ይጣላሉ፡፡

በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች በተለይ በአክሱም የንግሥት ሳባ መዋኛን ‹‹ማይ ሹም›› በጎንደር ዐፄ ፋሲል ያሠሩት ባሕረ ጥምቀት፣ በላስታ ቅዱስ ላሊበላ ያሠራው ባሕረ ጥምቀት፣ በሸዋ የዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ፍርድ መስጫ አደባባይን፣ አርባ አራት ታቦታት የሚያድሩበትን የሸንኮራ ሜዳን “ራቡቴ ወንዝ” በአዲስ አበባ ደግሞ ጃንሆይ ሜዳን /ጃንሜዳን/ ወዘተ ለአብሕርተ ምጥማቃት እንደ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል፡፡ እነዚህ ቦታዎች ዛሬም ድረስ ተከብረው ይገኛሉ፡፡ እኛ በዚህ ወቅት ታቦት ይዘን፣ከወንዝ ወርደን፣ ድንኳን ተክለን በማክበራችን ይፈጸማል፡፡

#ማሕበረ_ቅዱሳን

#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ!

አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube

Sador Sisay on Youtube

Sador Sisay on Instagram

Sador Sisay on Facebook

Sador Sisay on Tiktok

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏




Forward from: አምኀ ተዋኅዶ ዘክርስቶስ
#የቃል_ኪዳኑ_ታቦት

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የቃል ኪዳኑን ታቦት ክብር የሚገልጡ ብዙ ገጸ ንባቦች ያሉ ሲሆን በተለየ መልኩ ግን የማይዘነጉ ታሪኮች እና የእግዚአብሔር መገለጫ የሆነውን ታቦት ተአምር የሚያሳዩ ሦስት ክስተቶች አሉ

#በታቦት_አክባሪዎች_እግር_የቆመ_ውኃ

"እንዲህም ኾነ ሕዝቡ ዮርዳኖስን ሊሻገሩ ከየድንኳናቸው በወጡ ጊዜ የቃል ኪዳኑን #ታቦት የተሸከሙ ካህናት በሕዝቡ ፊት ይኼዱ ነበር እንደ መከር ወራት ዅሉ ዮርዳኖስ እጅግ ሞልቶ ነበርና ታቦት ተሸካሚዎቹ ወደ ዮርዳኖስ ሲደርሱ ታቦቱንም የተሸከሙት የካህናቱ እግሮች በውኀው ዳር ሲጠልቁ ከላይ የሚወርደው ውሃ ቆመ። ....... ወደ ዐረባ ባሕር ወደጨው ባሕር የሚወርደው ውኀ ፈጽሞ ተቋረጠ ሕዝቡም በኢያሪኮ ፊት ለፊት ተሻገሩ።" ኢያ፡ 3፥13

#ለታቦት_የሰገደው_ዳጎን(ጣዖት)

"ፍልስጥኤማውያንም የእግዚአብሔርን ታቦት ወስደው ወደ ዳጎን ቤት አገቡት በዳጎንም አጠገብ አኖሩት በነጋውም የአዛጦን ሰዎች ማልደው ሔዱ እንሆም ዳጎን በእግዚአብሔር ታቦት ፊት በምድር ላይ በግንባሩ ወድቆ ነበር ዳጎንንም አንሥተው ወደ ቀድሞ ስፍራው መለሱት በነጋታውም ማልደው መጡ እንሆ አሁንም ዳጎን በእግዚአብሔር ታቦት ፊት በምድር ላይ በግንባሩ ወድቆ ነበር የዳጎንም ራስ እጆቹም ተቈርጠው በመድረኩ ላይ ወድቀው ነበር የዳጎንም ደረት ብቻውን ቀርቶ ነበር የአዛጦንም ሰዎች እንዲህ እንደ ኾነ ባዩ ጊዜ እጁ በእኛና በአምላካችን በዳጎን ላይ ጠንክራለችና የእስራኤል አምላክ ታቦት ከእኛ ዘንድ አይቀመጥ አሉ።"1ሳሙ፡ 5፥1

#ታቦተ_በመንካቱ_የተቀሰፈዎ_ሰው(ዖዛ)

"ወደ ናኮንም ዐውድማ በደረሱ ጊዜ በሬዎቹ ይፋንኑ ነበርና ዖዛ እጁን ዘርግቶ የእግዚአብሔርን ታቦት ያዘ የእግዚአብሔርም ቍጣ በዖዛ ላይ ነደደ እግዚአብሔርም ስለ ድፍረቱ በዚያው ቀሠፈው በእግዚአብሔርም ታቦት አጠገብ በዚያው ሞተ እግዚአብሔርም ዖዛን ስለ ሰበረው ዳዊት ዐዘነ እስከ ዛሬም ድረስ የዚያ ስፍራ ስም የዖዛ ስብራት ተብሎ ተጠራ።" 2ሳሙ 6:6

እነዚህን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍላተ ንባባት በመረዳት በማመን በመጠንቀቅ በመፍራት በመንቀጥቀጥ በዓላችንን እናክብር አንዳፈር ታቦታትን ለመቅረብ አይደለም በሙሉ ዐይኖቻችን ለማየት አንድፈር በእምነት እንጂ በልማድ የምናከብር አንሁን!

#መልካም_በዓለ_ከተራ

#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ!

አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube

Sador Sisay on Youtube

Sador Sisay on Instagram

Sador Sisay on Facebook

Sador Sisay on Tiktok

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏




Forward from: አምኀ ተዋኅዶ ዘክርስቶስ
#ጾመ_ገሃድ(#ጋድ)

ጥር አስር በዚች ዕለት ምንም ምን መብልን ሳይቀመሱ ምዕመናን ሁሉ እስከ ምሽት ይጾሙ ዘንድ ከእኛ አስቀድመው የነበሩ ታላላቅ ሊቃውንት የቤተ ክርስቲያን መምህራን ሥርዓትን ሠሩ በምሽትም ቢሆን በታላቁ ጾም ከሚበላው በቀር ጥሉላትን እንዳይቀምሱ።

በዚች ዕለት ምዕመናን እስከ ምሽት እንዲጾሙት ያዘዙበት ምክንያቱ ይህ ነው የልደትና የጥምቀት በዓል በረቡዕ ወይም በዐርብ ቀን ቢብት በበዓለ ሃምሳ የሚበላውን የጥሉላት መብል በጠዋት በመብላት ምዕመናን ሁሉ በዓሉን እንዲያከብሩ የከበሩ አባቶቻችን ሐዋርያት አዝዘዋል እሊህ ሁለቱ የእግዚአብሔር ታላላቅ በዓሎቹ ናቸውና።

እኛ በዚህ በኃላፊው ዓለም ተድላ ደስታ ደስ የሚለን ለሌሎች እንዳይመስላቸው እንደ አይሁድና እንደ አረማውያን በዓል በመብልና በመጠጥ ብቻ እንዳናደርግ ስለዚህ ከልደትና ከጥምቀት በዓል ዋዜማ ያሉትን ሁለቱን ዕለታት እንድንጾም አዘዙን

የልደትና የጥምቀት በዓል በረቡዕና በዐርብ በሚብትበት ጊዜ በሁለቱ ዕለታት ፈንታ ሌሎች ተለዋጭ ዕለታትን እንድንጾማቸው ይገባል በዚህም ሁለት ሥራ ይፈጸምልናል የጾም ሥራና የበዓል ማክበር ሥራ ነው እንዲሁም በግብጻውያን አብያተ ክርስቲያን የተሠራ ነው።

በይረሙን( በዓለ አስተርዕዮ ወይም ከተራ) በእሑድ ወይም በአይሁድ ሰንበት ቀን(ቅዳሜ) ቢብት ይህም ጌታ የተገለጸበት ጥር ዐሥር ቀን ነው በዋዜማው ዐርብ እስከ ምሽቱ ይጹሙ አስቀድመን እንደተናገርን ጥሉላት አይብሉ የልደትና የጥምቀት በዓልም ሰኞ ቀን ቢሆን በሰንበት ቀን ይጾሙ ዘንድ አይቻልም ነገር ግን ጥሉላትን ከመብላት ይጠበቁ።

በጥምቀትም ዕለት ከእኩለ ሌሊት በፊት ተነስተው በውኃው ላይ ይጸልዩና ይጠመቁ ሕፃናትም በሚጠመቁ ጊዜ በውኃ እንዳይገድፉ ካህናቱም ከመንጋቱ በፊት ቀድሰው ቁርባኑን ያሳርጉ እጅግም ማልደው በጥዋት ከቤተ ክርስቲያን ይውጡ በከበረ ሥርዓታቸው ጌቶቻችን ሐዋርያት እንዳዘዙ።

የመለካውያን ወገኖች ግን የልደትና የጥምቀት ዋዜማ በቅዳሜ ቀን ወይም በእሑድ ቀን ቢሆን በሦስት ሰዓት ይቀድሳሉ ከወደዱም የተባረከ ኅብስት ተመግበው ውኃ ይጠጣሉ ከዚህም በኋላ ካህናቱ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሆነው በየሰዓቱ በመጸለይ ለበዓሉ የሚገባውን የነቢያትን ትንቢቶች ያነባሉ በዚያም ቀን በምሽት ይኸውም ጥር ዓሥር ነው በውኃው ላይ ይጸልያሉ ይህም አባቶቻችን ሐዋርያት እንዳዘዙት አልሆነም።

እርሳቸው የኤጲፋንያን በዓል እንዲያከብሩ አዘዋል ይኸውም መድኀኃኒታችን የተገለጠበት ካኑን በሚባል በሮም ሁለተኛ ወር በሰባት ይህም ጥር ዐሥራ አንድ ቀን ነው።

መለካውያን ግን የከበሩ አባቶች የቤተ ክርስቲያን መምህራን ያዘዙትን ይተላለፋሉ በልደትና በጥምቀት በዓል ዐርብም ረቡዕም ቢሆን አስቀድመው በርሱ ፈንታ ሳይጾሙ በጥዋት ተነሥተው ይበላሉና።

እኛንም ከበደላችን ያነጻን ዘንድ በዮረዳኖስም ወንዝ እንደ ተገለጸ የጌትነቱን ክብር በልቡናችን ይገልጥልን ዘንድ የክብር ባለቤት የሆነ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንለምነው ጌትነት ክብር ስግደት ለእርሱ ይገባልና ከቸር አባቱ ጋር ይቅር ባይ ከሆነ መንፈስ ቅዱስም ጋር ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን።

መጽሐፈ ስንክሳር

#ማስታወሻ


#አልሰማንም_አላየንም_እንዳትሉ_ነገ_እስከ_ምሽቱ_12_ሰዓት_ነው_የሚጾመዉ።

#ቅዳሜ_ከጥሉላት_ምግብ_ብቻ_ነው_የምንቆጠበዉ_እንጂ_ከመብል_አንከለከልም

#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ!

አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube

Sador Sisay on Youtube

Sador Sisay on Instagram

Sador Sisay on Facebook

Sador Sisay on Tiktok

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏




Forward from: አምኀ ተዋኅዶ ዘክርስቶስ
#በእንተ_ጾመ_ገሃድ/ጋድ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ  አሐዱ አምላክ አመ አሡሩ ለጥር በዛቲ ዕለት ሠርዑ አበዊነ መምህራነ ቤተ ክርስቲያን እለ ቀደሙነ ሊቃውንት ዐበይት ከመ ይጹሙ ኵሎሙ መሃይምናን እስከ ምሴት እንዘ ኢይጥዕሙ ምንተኒ መባልዕተ ወበጊዜ ሠርክኒ ኢይጥዐሙ ጥሉላተ ዘእንበለ ዘይትበላዕ በጾም ዐቢይ

ወለእመ ኮነ ዕለተ በይረሙን ዘውእቱ አስተርእዮ በዕለተ እሑድ አው በዕለተ ሰንበተ አይሁድ ይጹሙ በዕለተ ዓርብ እምቅድሜሁ እስከ ምሴት

ወለእመ ኮነ በዓለ ልደት ወበዓለ ጥምቀት በዕለተ ሰኑይ ኢይትከሃል ከመ ይጹሙ በዕለተ ሰንበት ዳዕሙ ይትዐቀቡ እምነ በሊዕ ጥሉላተ (ስንክሳር ጥር 10)

#ትርጉሙንና_ማብራሪያውን_እመለስበታለሁ


Forward from: አምኀ ተዋኅዶ ዘክርስቶስ
የቀደሙት ሰዎች በሰናዖር ከምድር እስከ ሰማይ፣ እስከ አምላክ ማደሪያ የሚደርስ ግንብ ሊሠሩና ስማቸውን ሊያስጠሩ ተነሡ። ነገር ግን በትዕቢታቸው ጠፉ። እነዚህ የባቢሎን ሰዎች ምንኛ ችኩሎች ሆኑ?! ጥቂት ዘመን ቢታገሱ ኖሮ ራሱ አምላክ ከእነርሱ እንደ አንዱ ሰው ሆኖ በግርግም ተኝቶ ያገኙት አልነበር?!

እነዚህ የሰናዖር ሰዎች ትንሽ ቢታገሱ ኖሮ ከምድር ወደ ሰማይ መሻገሪያ የምትሆን በእግዚአብሔር እጅ የታነጸች ታላቋን የብርሃን ድልድይ ድንግል ማርያምን ያገኙዋት ነበር። በዚህችም የብርሃን ድልድይ (መሰላል) እነርሱ ብቻ ሳይሆኑ የሰው ልጆች ሁሉ ስም እንደ ተጠራ አይተው ደስ ይሰኙ ነበር።

====

አቤቱ ጾም፣ ጸሎት፣ መንፈሳዊ ትሩፋቶቻችን የአንተ ረድኤት የሌለባቸው በትዕቢት ያቆምናቸው የሰናዖር ግንቦች አይሁኑብን። እንዲህም ከሆኑ፣ በሥራዬ እያለ ልባችን እንዳይኮራ፣ ዓይናችንም ወደታች እያየ ወዳጆቹን እንዳይንቅ ወደ አንተ የማያደርሱንን እነዚህን የሐሰት ግንቦች አፍርስልን። በእነርሱም ፈንታ በትሕትና እና በፍቅር ያጌጡ ውብ ግንቦችን እናንጽ ዘንድ ረድኤትህን ላክልን።

#ዲያቆን_አቤል_ካሳሁን


Forward from: አምኀ ተዋኅዶ ዘክርስቶስ
#በሥላሴ እናምናለን #ለሥላሴ እንገዛለን #ለሥላሴ እንሰግዳለን ፤ ከነፋስ ከእሳት ፣ ከውኃና ከመሬት ባሕርያት ፈጥረውናልና የቸርነት ባለቤት የኾነው #የቅድስት_ሥላሴ በረከት እንዲያድርብን የአብ ሰላም ፣ የወልድ ፍቅር የመንፈስ ቅዱስ ሃይማኖት በመካከላችሁ ይደር ! የሰላም አምላክ ከእኛ ጋር ይኑር ።

ቅድመ ዓለም በነበረ በአንዱ በእግዚአብሔር አብ እናምናለን እናመልካለን አብን በጌትነት በሚመስለው በሚተካከለው በእግዚአብሔር ወልድ እናምናለን እናመልካለን በዓለም ምሉዕ በሆነው በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ እናምናለን እናመልካለን #ቅድስት_ሥላሴ የአምልኮታችን ማዕከል ናቸውና የሚሠዋው መሥዋዕት የሚታጠነው ዕጣን የሚቀርበው ቁርባን ሁሉ የሚያርገው ወደ #ቅድስት_ሥላሴ_ነው ።


Forward from: አምኀ ተዋኅዶ ዘክርስቶስ
#የግዝረት_በዓል_ከጌታችን_ከዘጠኙ_ንዑሳን_በዓላት_አንዱ_ነው

#ጥር_ስድስት የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቤተ ግዝረት በመግባት የኦሪትን ሕግ የፈጸመበት ቀን ነው ቅዱስ ወንጌል « ስምንተኛው ቀን በተፈጸመ ጊዜ ሕጻኑን ሊገርዙት ወሰዱት ገና ሳትፀንሰው መልአኩ ስሙን እንዳወጣለት ኢየሱስ አሉት » ( ሉቃ 2 ፥ 22 )በማለት መዝግቦልናል

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአባቶች የተሰጠውን ቃል ኪዳን ይፈጽም ዘንድ በሥጋው ግዝረትን እንደ ተቀበለ እንዲህ ሲል ተናግሯል « በእግዚብሔር ፊት የግዝረት ምልክትን አደረገ ፤ ኢያሱም በእስራኤል ልጆች ዘንድ እንዲሁ አደረገ » ብሏል ።

ግዝረት ማለት የወንድ ልጅ የሥጋን ሸለፈት መግረዝ ማለት ሲሆን ሥርዐተ ግዝረት ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰጠው ለአባታችን ለአብርሃም ነው ይኸውም የእግዚአብሔር ድርሻ የመሆን ምልክት ፣ የእምነትና የቃል ኪዳን ማረጋገጫ ማኅተም ነበር ።

በብሉይ ኪዳን ያልተገረዘ ወደ ተቀደሰው ቦታ አይገባም ፤ የተቀደሰውን መሥዋዕትም አይሳተፍም ከተገረዘው ማኅበረሰብ (ቤተ አብርሃም) ጋር ምንም ዐይነት ዝምድና መፍጠርም ሆነ ጋብቻ መመሥረት አይችልም ከዚህ ወገን መለየት ይኖርበታል ፤ በገንዘብ የተገዛ አገልጋይ ቢሆንም መገረዝ አለበት ።

ለብዙዎችም ጌታችን ወደ ቤተ ግዝረት እንዳልገባና እንዳልተገረዘ ይመስላቸው ነበር ።

እነርሱ እንዳሰቡት ሆኖ ቢሆን ኖሮ አይሁድ ታላቅ ምክንያትን ባገኙ ነበር ፤ ጌታችን ግን የግዝረትን ሕግ ፈጽሟል ለእኛም በግዝረት ፈንታ ጥምቀትን ሰጠን የፋሲካውንም ቂጣ እንደበላ በእርሱ ፈንታ ሥጋውንና ደሙን እንደሰጠን ። ( ዘፍጥ 17 ፥ 9 ) ይገልጻል ።

ለአብርሃም በተሰጠው የግዝረት ቃል ኪዳን መሠረት ከአብርሃም የተወለደ ሁሉ ይገረዝ ዘንድ በሙሴ ሕግ ስለተጻፈ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም የአብርሃም ዘር በመሆኗ ጻድቅ አረጋዊ ዮሴፍን « እንደ ሕጉ ልጄን እንዲገርዘውና ስሙንም እንዲሠይመው ብልህ ገራዥ ሰው አምጣልኝ አለችው ።

ዮሴፍም ሄዶ የሚገርዝ ብልህና በሀገሩ የታወቀ ባለሞያ አመጣላት ያ ባለሙያም ሕፃኑን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በእናቱ በቅድስት ድንግል ማርያም ክንድ ላይ አየው እንድገርዘው ሕፃኑን በጥንቃቄ ያዙት አላቸው
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም መልሶ ባለሙያውን እንዲህ አለው ፦

« ባለሙያ ገራዥ ሆይ ደሜ ሳይፈስ ትገርዘኝ ዘንድ ትችላለህን ? በዕለተ ዐርብ ካልሆነ በቀር ደሜ አይፈስምና » አለው « ያን ጊዜ ጎኔን በጦር ሲወጉኝ ውኃና ደሜ ይፈሳል ለአዳምና ለሚያምኑ ልጆች ሁሉ መድኃኒት ይሆናል » አለው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረውን ቃል ያ ባለሞያ በሰማ ጊዜ ደነገጠ አደነቀም ዕቃውንም ሰብስቦ ተነሥቶ ከሕፃኑ ጌታ እግር ስር ሰገደ ።

ያን ጊዜም ምላጩ በእጁ ላይ እንደ ሰም ቀልጦ እንደ ውኃ ሆኖ ፈሰሰ የከበረች ድንግል እመቤታችንንም « አንቺ ከሴቶች ተለይተሸ የተባረክሽ ነሽ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው ይህ ልጅሽ ስለ እርሱ ነቢያት ትንቢት የተናገሩለት የሕያው አምላክ ልጅ ነው » ብሎ እሷን ወላዲተ አምላክ መሆኗን እሱን አምላክ መሆኑን መስክሯል ።

ሕፃኑም ለዚያ ባለሞያ ዳግመኛ መልሶ እንዲህ አለው « እኔ ነኝ ትገዝረኛለህን ወይስ ተውክ ? ወይም የአባቶቼ አባቶች እንዳደረጉ እኔ ላድርግ ? » አለው ያም ባለሞያ « የአባቶችህ አባቶች እነማን ናቸው » አለው ሕፃኑ ጌታችንም
« የሕዝብ ሁሉ አባቶች የሆኑ አብርሃም ፣ ይስሐቅና ያዕቆብ ናቸው ለእነርሱም ይህ ግዝረት አስቀድሞ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቷቸዋልና » አለው

ባለሞያውም እኔ ካንተ ጋር እናገር ዘንድ አልችልም በአንተ ህልውና መንፈስ ቅዱስ አለና አለው በዚያን ጊዜ ሕፃኑ ዐይኖቹን ወደ ስማይ አቅንቶ « አባት ሆይ ለአብርሃም ለይስሐቅ ያዕቆብ አስቀድሞ ግዝረትን የሰጠሀቸው ያቺን ግዝረት ዛሬ ለእኔ ስጠኝ » አለ ይህ ብሎ ሲጨርስ ያለ ሰው እጅ በሕፃኑ ሥጋ ላይ ግዝረት ተገለጠች ።

ይኸውም ድንግልናዋ ሳይለወጥ ከድንግል ማኅፀን እንደ መውጣቱ ፤ የጌታችን ግዝረቱም የማይመረመር ሆነ ወደ ሐዋርያት በተዘጋ አዳራሽ መግባቱና መውጣቱ እንደማይመረመር ሁሉ እንዲሁ በረቀቀ ጥበቡ ከሥጋው ምንም ምን ሳይቆረጥ በመገረዙ ጌትነቱና ከሃሊነቱ ተገለጠ ።

ያም ገዛሪ ይህን ተአምር አይቶ የሕፃኑንም አነጋገር ሰምቶ እጅግ አደነቀ ፤ የክብር ባለቤት ከሆነ ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እግር በታች ሦስት ጊዜ ሰገደና « በእውነት አንተ የእግዚአብሔር ልጅ የእስራኤልም ንጉሥ ነህ » አለው ከዚህ በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያደረገውን ተአምራት እየተናገረ ወደ ቦታው ሔደ።

#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ!

አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube

Sador Sisay on Youtube

Sador Sisay on Instagram

Sador Sisay on Facebook

Sador Sisay on Tiktok

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏




Forward from: አምኀ ተዋኅዶ ዘክርስቶስ
ኖኅ ማለት ዕረፍት ደስታ ማለት ነው የአዳም 10ኛ ትውልድ በ950 ዓመቱ #ጥር_6 ቀን ዕረፍቱ ነው ብላ ቅድስት ቤተ ክርስቲያ በዓልን ሰርታ ታከብራለች። ዘፍ፡ 9 ፥ 29

አባታችን ኖኅ ከጥፋት ውኃ በኋላ ከመርከብ ወጥቶ መስዋዕት ሠዋ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም « ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሏት » አለው « ጌታዬ የኔ ልጆች ኃጢአት መሥራት አይተውምና ፈርደህ ልታጠፋቸው መብዛቴ ለምኔ ነው ? » አለ፡፡

ጌታም « ምድርን በንፍር ውኃ እንዳላጠፋት ዳመና በዞረ ጊዜ አራት ኅብር አድርጌ ዳግመኛ ቀርጬ አሳይሀለሁ » ብሉ ቃልኪዳን ገባለት፡፡

ቸሩ ጌታችን ሆይ « በእኔና በእናንተ መካከል፥ ሕያው ነፍስ ባለውም ሥጋ ሁሉ መካከል ያለውን ቃል ኪዳኔን አስባለሁ፤ ሥጋ ያለውንም ሁሉ ያጠፋ ዘንድ ዳግመኛ የጥፋት ውኃ አይሆንም። » ብለህ የገባህውን ቃል ኪዳን ዛሬ ለኛ ለልጆችህ ያስፈልገናልና በብዙ የጥፋት ውኃ ውስጥ ነንና አስበን አትርሳን!

20 last posts shown.