እባካችሁ ዘካ የምትሰጡ ወገኖች!
~~~
ህዝብን በተለያዩ መንገዶች ዲን እያስተማሩ ያሉ (በደዕዋ፣ በቁርኣን፣ በተድሪስ፣ ወዘተ ላይ የተሰማሩ) አቅመ ደካማ መሻይኾችን፣ ዱዓቶችን በዘካችሁ አትርሷቸው። ወላሂ አፍ አውጥተው ችግራቸውን የማይናገሩ ነገር ግን ዲን ለማስተማር ጊዜያቸውን በመስጠታቸው የተነሳ የሰቀቀን ህይወት የሚገፉ ብዙ ናቸው። በተለይ በዚህ ዘመን ደግሞ የኑሮ ጫና በየጊዜው ይበልጥ እየከበደ ነው። እነሱ የህዝባቸው ኣኺራ አሳስቧቸው እንደሌሎች መስራት፣ መነገድ፣ መለወጥ ሲችሉ ዱንያቸውን መስዋእት አድርገው የችግር ህይወት ሲገፉ እንዴት ውለታቸው ይዘነጋል? እንዴትስ ዋጋቸው ይቃለላል? ለነሱ ውለታ መዋል ለዲን ውለታ መዋል ነው። እንዲያውም ለማህበረሰባችንም ውለታ መዋል ነው። ከጎናቸው የሚቆም አጋር ሲያገኙ ይበልጥ የመስራት ሞራል ያገኛሉ። እናም ዘካ የሚመለከታችሁ ወገኖች ሆይ! እባካችሁ እባካችሁ በየአካባቢያችሁ ተመልካች ያጡ መሻይኾችን፣ ኡስታዞችን፣ የቁርኣን አስተማሪዎችን፣ የመስጂድ ኢማሞችን፣ ሙአዚኖችን የአቅማችሁን ያክል አትርሷቸው።