Forward from: Getasew Adane
6000 ገደማ ሴቶች ጋር ምክክር ተደርጓል-ጥምረት
ጥምረት ለሴቶች ድምፅ በሀገራዊ ምክክር መድረክ ጠቅላላ ጉባኤውን ጥር 22 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሲያካሂድ ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ 6000 ገደማ ሴቶች ጋር ምክክር ማድረጉን ገለጸ።
ጥምረቱ በሀገራዊ ምክክር ሂደት ውስጥ ሴቶች ትርጉም ያለው ተሳትፎ እንዲኖራቸው ለማስቻል ከሁለት ዓመታት በፊት በ22 ድርጅቶች ተመሥርቶ በአኹኑ ወቅት ከ60 በላይ አባል ድርጅቶችን ይዞ የሚንቀሳቀስ ጥምረት ነው።
ለተሳታፊዎች የእንኳን ደኅና መጣችኹ መልእክት ያስተላለፉት የጥምረቱ ጽ/ቤት በመኾን የምታገለግለው ትምራን ሥራ አስኪያጅ ኢየሩሳሌም ሶሎሞን፣ የጥምረቱ ምሥረታን ተከትሎ የአቋም መግለጫ የማውጣት፣ በቀጣይ ሊሠራቸው ያቀዳቸውን ተግባራት በማስቀመጥ እና በየክልሉ በመዘዋወር የሴቶችን አጀንዳዎች የመሰብሰብ፣ በሌሎች ሀገራዊ ፖለቲካዊ ጉዳዮች እንደሚታየው በሀገራዊ ምክክር ሂደት ውስጥ የሴቷ አጀንዳ ተረስቶ ሳይካተት እንዳይቀር ብሎም የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሚያከናውናቸው ተግባራት ውስጥ የሴቶች ተሳትፎ እንዲኖር ክትትል የማድረግ ሥራዎች ማከናወኑን ጠቅሰዋል።
በዚህም መሠረት ሐምሌ 2016 ዓ.ም ውስጥ ከስምንት ክልሎች እና ሁለት ከተማ አስተዳደሮች ያሰባሰባቸውን አጀንዳዎች ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማስረከቡን፣ ቀጥሎም በማእከላዊ ኢትዮጵያ እና ጋምቤላ ክልሎች እንዲሁም በአዲስ አበባ፣ ሲዳማ፣ ደቡብ ኢትዮጵያ እና ኦሮሚያ ተጨማሪ ማኅበረሰብ ተኮር ውይይት በማካሄድ የሴቶችን አጀንዳዎች መሰብሰብ መቻሉን ተናግረዋል።
በቀጣይ በኮሚሽኑ በየክልሉ ባደረጋቸው ሕዝባዊ ውይይቶች ላይ ለሀገራዊ ምክክር የተመረጡ ሴቶች በብሔራዊ ደረጃ ምክክር በሚደረግበት ወቅት ሐሳባቸውን አቀናጅተው ለማቅረብ የሚያስችላቸው ሥልጠና ለመስጠት እቅድ መያዙን ጠቁመው፣ የጥምረቱ አባል ድርጅቶች የሴቶች አጀንዳዎች ትኩረት ተሰጥቷቸው ለውጤት እንዲበቁ የውትወታ ሥራዎችን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።
የጥምረቱ ሥራ አስፈጻሚ አባል እና ተርካንፊ ለዘላቂ ልማት የተሰኘ ድርጅት የሚመሩት ወርቅነሽ ቤጊ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር፣ ጥምረት ለሴቶች ድምፅ ሀገራዊ የምክክር ሂደቱ በትክክል ከተተገበረ ለችግሮቻችን መፍትሔ ይሆናል በሚል እምነት ሴቶችን በማሳተፍ ሂደቱን ለማገዝ መቋቋሙን አስታውሰው፣ የጥምረቱ አባል ድርጅቶች የሴቶች ድምፅ እንዲሰማ በሚደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ የሚያደርጉትን አስተዋጽኦ አጠናክረው እንዲቀጥሉ አደራ ብለዋል።
በመርሐ ግብሩ ላይ የጥምረቱ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እና የኢትዮጵያ ሴቶች መብቶች ተሟጋች የተሰኘ ድርጅት የሚመሩት ፌቨን አርአያ፣ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ያከናወናቸውን ተግባራት ሪፖርት አቅርበዋል።
ባለፉት ጊዜያት ጥምረቱ ያከናወናቸውን አንኳር ጉዳዮች ያቀረቡት የፕሮግራም አስተባባሪው አቶ አስቻለው ማቴዎስ፣ በ10 ክልሎች እና ሁለት ከተማ አስተዳደሮች ውስጥ በተካሄዱ የምክክር መድረኮች እና ማኅበረሰብ ተኮር ውይይቶች ከአካል ጉዳት ጋር የሚኖሩ 483 ሴቶችን ጨምሮ በጠቅላላው 5631 ተሳታፊዎች ከተገኙባቸው ውይይቶች የሴቶች አጀንዳዎች መሰብሰቡን አስረድተዋል።
ያለፈው ዓመት የጥምረቱ የኦዲት ሪፖርት በተመሰከረለት የሒሳብ አያያዝ አዋቂ ድርጅት የቀረበ ሲሆን፣ የጥምረቱ ቀጣይ እቅድ በጥምረቱ የክትትል እና ግምገማ ከፍተኛ ባለሞያ አቶ አስማማው መኮንን ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። በዚሁ ወቅት ጠቅላላ ጉባኤው ከጥምረቱ ጋር በአጋርነት ሲሠሩ የቆዩ ሦስት ድርጅቶችን በአባልነት ተቀብሎ አጽድቋል።
የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት የጥምረቱ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሴቶች ማኅበር ሊቀመንበርት ሃይማኖት ታደሰ፣ ጥምረቱ ሀገራዊ ምክክሩ በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ ሴቶች ትርጉም ባለው መልኩ እንዲሳተፉ፣ የሴቶች አጀንዳ ተሰብስቦ በአግባቡ እንዲሰነድ፣ ለሀገራችን ቀጣይ የተሳካ ጉዞ የሴቶች ድምፅ ጎልቶ እንዲደመጥ እና በሀገር ደረጃ ያሉ ችግሮች እንዲፈቱ ለማድረግ በአስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ሴቶችን ጭምር በማካተት አጀንዳዎችን በመሰብሰብ ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማስረከቡን ጠቁመዋል።
በቀጣይ ምክክር ባልተካሄደባቸው አማራ እና ትግራይ ክልል የሚኖሩ ሴቶች አጀንዳቸው ተካትቶ ዘላቂ የሆኑ የመፍትሔ ሐሳቦች እና አተገባበር ይኖራል የሚል እምነት እንዳላቸውም ገልጸዋል።