Ministry Of Education


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Education


📚ይህ ትክክለኛው የትምህርት ሚኒስትር የተማሪዎች መረጃ ማቀበያ ገፅ ነው
🔵ከ1-12 መፅሃፍት ለማግኘት: @STBookbot
🔴ለFreshman : @Freshman_Robot
«Buy Ads» @MoeAds_bot or https://telega.io/c/Tmhrt_minister

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Education
Statistics
Posts filter


የጤና ተመራቂዎች የሙያ ብቃት ምዘና (COC) መቼ ይሰጣል?

ከትናንት ጥር 26/2017 ዓ.ም ጀምሮ የጤና ተማሪዎችን ጨምሮ የቅድመ-ምረቃ ዕጩ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና እየተሰጠ ይገኛል።

የሙያ ብቃት ምዘና (COC) ለመውሰድ እየጠበቁ የሚገኙ የጤና ተመራቂዎች (ምዘናውን በድጋሜ የሚወስዱትን ጨምሮ) ምዘናው መቼ እንደሚሰጥ ቲክቫህን ጠይቀዋል።

በጉዳዩ ዙሪያ ጤና ሚኒስቴርን የጠየቅን ሲሆን፤ በትምህርት ሚኒስቴር እየተሰጠ የሚገኘው የመውጫ ፈተና መጠናቀቅና ውጤት መገለፅን ተከትሎ COC የሚወስዱ አመልካቾች (ድጋሜ ተፈታኞችን ጨምሮ) ምዝገባ እንደሚደረግ ከሚኒስቴሩ አረጋግጠናል።

የCOC ምዘናውን በየካቲት ወር መጨረሻ ወይም በመጋቢት ወር የመጀመሪያ ሳምንት ለመስጠት በጊዚያዊነት መታቀዱን ከሚኒስቴሩ ሰምተናል።

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister

5k 0 13 11 30

@Tmhrt_Minister History grade 12 unit 4.pdf
1.1Mb
📚History grade 12 unit 4

🔘Short Note

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister


Forward from: ቀለሜ
🤖 Qeleme Exams Mobile Application

📱ለ መጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች የ ስኬታቸው አጋር ሁኗል።🎉

በተደጋጋሚ ቅርጻቸውን እየቀየሩ የሚመጡ ጥያቄዎችን ከ ሙሉ ማብራሪያቸው 'ና አጫጭር ትምህርቶች ጋር አንድ ጊዜ በማውረድ ያለምን Internet ግንኙነት በ Qeleme Exams ቀላል እና ሳቢ በሆነ መልኩ ይለማመዱ።

🔍 መተግበሪያውን ያውርዱ!👇🏾
V1.2.0: https://t.me/keleme_2013/15165

👨🏾‍💻 Need help? Contact the admin:
https://t.me/QelemeExamsAdmin


@Tmhrt_Minister 500 English questions for grade 11.pdf
585.8Kb
📚500 English questions for grade 11

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister

8.7k 0 62 25 18

የ2017 ዓ.ም የመጀመሪያ ሴሜስተር ሞዴል ፈተናዎች

📚የ6ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና

📚የ12ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና 👇

የኦሮሚያ ክልል

የአዲስ አበባ አቃቂ ክ/ከተማ

እነዚህንና ሌሎች ፈተናዎችን ኖቶችን ለማዉረድ ቻናላችንን ይቀላቀሉ! 👇
🔘 Join : https://t.me/Moe_Library


የ2017 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራም ዕጩ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና መሠጠት ጀምሯል።

ፈተናው ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጥር 30/2017 ዓ.ም ድረስ ለአምስት ተከታታይ ቀናት ይሰጣል።

ተፈታኞች በዛሬው መርሐግብር የአካውንቲንግ እና የአካውንቲንግና ፋይናንስ ትምህርት ፈተና በመውሰድ ላይ ይገኛሉ።

ፈተናውን በድጋሚ የሚወስዱትን ጨምሮ በጠቅላላው 176 ሺህ ተማሪዎች የመውጫ ፈተናውን እንደሚወስዱ ይጠበቃል ሲል ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወቃል።

ምስል፦ ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister


#EXITEXAM #Note

ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ተግባራዊ ማድረግ ከጀመራቸው ስራዎች አንዱ የሆነ የተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ከጥር 26 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ ይሰጣል።

⚡️በፈተና ወቅት ከተፈታኝ ተማሪዎች ምን ይጠበቃል ?


👉🏾 ተፈታኞች ወደ መፈተኛ ክፍል ሲመጡ ማንኛውም አይነት ስልክ፣ ስማርት ሰዓት ፣ ታብሌት ፣ ላፕቶፕና ... ወዘተ ተመሳሳይ ኤክትሮኒክ ቁሳቁስ መያዝ በፍፁም የተከለከለ ነው።  (ይዞ የተገኘ ፈተናው /ውጤቱ ተሰርዞበት በቀጣይ ጊዜ እንዲቀመጥ ይደርጋል)

👉🏾 ፈተና ከመጀመሩ ከ30 ደቂቃ በፊት መፈተኛ ክፍል መገኘት አለባቸው ይህም ማለት ከጥዋቱ 2፡00 በፊት ፤ ከሰዓት ደግሞ ከ8፡00 በፊት ተፈታኞች መገኘት አለባቸው።

👉🏾 ተፈታኞች ለፈተና ሲመጡ ID መያዝ ያለባቸው ሲሆን User Name እና Password lower-case and upper-case ፊደላትን ለይተው በጥንቃቄ መያዝ አለባቸው።

👉🏾 ተፈታኞች ፈተና ከተጀመረ በኃላ ከ30 ደቂቃ በፊት ከፈተናው ክፍል መውጣት የለባቸውም።

👉🏾 ተፈታኞች ፤ ፈተናውን የሚያስፈትኑ መምህራን በሚያሳዩት ቦታ ብቻ መቀመጥ አለባቸው።

👉🏾 ሁሉም ተፈታኝ እንዲቀመጥ የተመደበበት የራሱ ኮምፒውተር ላይ ብቻ ተቀምጦ መክፈትና መጠቀም አለበት።

👉🏾 በፈተና ክፍል ውስጥ መነጋገር እና ከቦታ ቦታ መዘዋወር በፍፁም የተከለከለ ነው። እንዲሁም ማንኛውም ተፈታኝ ከጎኑ ያለውን ተማሪ ኮምፒውተር በፍፁም ማየት የለበትም።

👉🏾 ምንም ዓይነት ወረቀት ወደ መፈተኛ ክፍል ይዞ መምጣት አይቻልም።

👉🏾 ተፈታኞች በምንም ሁኔታ መኮርጅም ሆነ ማስኮርጅ ተግባር ላይ ቢሳተፉ እርምጃ ይወሰድባቸዋል።

👉🏾 ሁሉም ተፈታኞሽ ለፈታኝ መምህራንና ለአስተባባሪዎች  መታዘዝ ያለባቸው ሲሆን የፈተናው ደንብ እና ስርዓት ተገዢ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

👉🏾 በድጋሚ ተፈታኞች የፈተና መግቢያ ትኬት (Exit Exam Entry Ticket) መያዝ ይጠበቅባቸዋል።

NB.  ሁሉም ተፈታኞች ወደ መፈኛ ክፍል ተፈትሸው እንዲገቡ የሚደረግ ሲሆን ማንኛውም ተፈታኝ ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በፍተሻ ወቅት ይሁን ሥርዓት ለማስያዝ በሚደረግ እንቅስቃሴ እንቅፋት ሆኖ ከተገኘ ከመፈተኛ አከባቢ እንዲገለል ተደርጎ በቀጣዩ የመውጫ ፈተና መስጫ ወቅት እንዲቀመጥ ይፈቀድለታል።

⚡️ከፈታኝ መምህራን የሚጠበቅ

👉🏾 የተፈታኝ ተማሪዎችን ID በአግባቡ በማረጋገጥ ወደ ክፍል እንዲገቡ ማደረግ ይጠበቅባቸዋል።

👉🏾 ተፈታኝ ተማሪዎችን በሥም ዝርዝራቸው መሠረት ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።

👉🏾 ፈታኝ መምራህን የተማሪዎችን አቴንዳንሰ ይወስዳሉ ፤ ተማሪዎችን ፊርማ ያስፈርማሉ።

👉🏾 በፈተና ክፍል ውስጥ ደምጽ እንዳይሰማ፣ ተማሪዎች ከቦታ ቦታ እንዳይዘዋወሩ ተገቢውን ቁጥጥር ማድረግ አለባቸው።

👉🏾 የፈተናው አጠቃለይ ሂደት በትኩረት መከታተል አለባቸው።

👉🏾 በህመም ምክንያት ተማሪዎች ከክፍል መውጣት ቢፈልጉ ከሱፐርቨዘር ጋር በመነጋገር አስፈላጊውን እርዳታ ያደርጋሉ።

👉🏾 ተማሪዎች በጎናቸው ያለውን ሌላ ኮምፒውተር እንዳይመለከቱ መቆጣጠር አለባቸው።

👉🏾 ተማሪዎች ፈተናው ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በፊት እንዳይወጡ መቆጣጠር ይጠበቅባቸዋል።

👉🏾 ሲኮርጂ ወይንም ሲያስኮርጅ የተገኘ ተማሪ ከመፈተኛ ክፍል እንዲወጣ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

👉🏾 ፈተናው ከጀመረ 15 ደቂቃ በኃላ የሚመጣ ተማሪ እንዲገባ ማድረግ የላባቸውም።

👉🏾 የፈተና አፈጻጸም ሪፖርት ለሱፐርቨዘር ማቅረብ

🍀 መልካም ፈተና 🍀

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister


#Notice

Wallaga_University, Mid-Year (2017 Academic Year) National Exit Exam Schedule

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister


Exit Exam Schedule - Full ጥር 2017 ዓ.ም.xls
201.0Kb
#ExitExamSchedule

ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ከጥር 26-30/2017 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ ይታወቃል፡፡

የፈተናው ሙሉ መርሐግብር (የሚሰጡ ፈተናዎች ዝርዝር፣ የፈተና ቀንና ሰዓት፣ የመፈተኛ ማዕከላት እንዲሁም የተፈታኞች ዝርዝር) ከላይ ተያይዟል፡፡

እሑድ የካቲት 2/2017 ዓ.ም ጠዋት የኢኮኖሚክስ ትምህርት የመውጫ ፈተና በአምቦ እና በወለጋ ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚሰጥም መርሐግብሩ ያሳያል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister




#ExitExam

176 ሺሕ ተማሪዎች የመውጫ ፈተናን ለመውሰድ መመዝገባቸው ተገለጸ

👉ፈተናው ከጥር 26 እስከ 30 ድረስ ይሰጣል

ጥር 23/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በ2017 ዓ.ም አጋማሽ ላይ የሚሰጠውን የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና ለመውሰድ 176 ሺሕ ተማሪዎች መመዝገባቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

ፈተናውን በድጋሚ የሚወስዱትን ጨምሮ በጠቅላላው 176 ሺሕ ተማሪዎች የመውጫ ፈተናውን ይወስዳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ በትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዬች መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ኤባ ሚጀና #ለአሐዱ ገልጸዋል።

በዚህም መሰረት በኢትዮጵያ የሚገኙ በሁሉም የኒቨርሲቲዎች ፈተናው የሚሰጥ ሲሆን፤ ተጠሪነቱ ለትምህርት ሚኒስቴር ያልሆነው የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ጭምር በዚህ ፕሮግራም ተካታች መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የግል ኮሌጆችን በሚመለከት አሐዱ ላቀረበላቸው ጥያቄ ትምህርት ሚኒስቴር የግል ኮሌጆች ላይ ገብቶ ለመፈተን የሚያስችል መዋቅር እንደሌለው በማንሳት፤ ነገር ግን ተማሪዎች በአቅራቢያቸው በሚገኝ የመንግስት ተቋም በኩል መፈተን እንደሚችሉ ገልፀዋል።

የፈተና ቀኑ በተለያዩ ምክንያቶች ዘግይተው ትምህርት የጀመሩትን ዩኒቨርሲቲዎች ታሳቢ ያደረገና በቂ ዝግጅት ማድረጋቸው ከተረጋገጠ በኋላ መወሰኑን ተናግረዋል።

ፈተናውን ለመስጠት ታቅዶ የነበረው ጥር 14 እና 15 የነበረ ቢሆንም፤ ሁሉም ዩኒቨርስቲዎች እኩል ትምህርት ባለመጀመራቸው ወደ ጥር 26 ቀን 2017 ዓ.ም. እንዲሸጋገር መደረጉን ገልጸዋል፡፡

በዚህ የፈተና ፕሮግራም ተንቀሻቃሽ ስልክና የወረቀት ፅሁፍ ይዞ መገኘት ፈፅሞ #የተከለከለ መሆኑን የገለጹት የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈፃሚው፤ "ተፈታኞች መታወቂያ መያዝና ከፈተና ፕሮግራሙ 30 ደቂቃ ቀድሞ ቦታው ላይ መድረስ ይጠበቅባቸዋል" ብለዋል፡፡ የወጣው ፈተናም ከተማሩት በመሆኑ ሳይጨነቁ በተረጋጋ መንፈስ መስራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

የዘንድሮው የዩኒቨርስቲዎች የመውጫ ፈተና ከዚህ በፊት ይሰጥ እንደነበረው ሙሉ ለሙሉ በኦንላይን የሚካሄድ ሲሆን፤ ከጥር 26 እስከ 30 ከሰኞ እስከ አርብ ባሉት አምስት ተከታታይ ቀናት እንደሚሰጥ አስታውቀዋል።

የተማሪዎች ፈተና እንደተጠናቀቀ ቅዳሜ ማለትም የካቲት 1 ቀን የመምህራንን ስልጠና ሲወስዱ የነበሩ መምህራን ፈተና ይወስዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

[ዘገባው የአሃዱ ሬድዮ ጣቢያ ነው]

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister


@Tmhrt_Minister_Biology_Review_question_Unit_3_Energy_transformation.pdf
889.4Kb
📚Biology Review question

📁Unit 3 Energy transformation for practice

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister

15k 0 52 4 14
12 last posts shown.