የጤና ተመራቂዎች የሙያ ብቃት ምዘና (COC) መቼ ይሰጣል?
የሙያ ብቃት ምዘና ለመውሰድ እየጠበቁ የሚገኙ የጤና ተመራቂዎች ምዘናው መቼ ይሰጣል የሚሉ በርካታ ጥያቄዎች ለቲክቫህ አድርሰዋል።
በጉዳዩ ዙሪያ ጤና ሚኒስቴርን የጠየቅን ሲሆን፤ ምዘናውን ለመስጠት ዝግጅት ማጠናቀቁን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።
በትምህርት ሚኒስቴር ባለፈው ሳምንት የተሰጠውን የመውጫ ፈተና ወስደው ያለፉ ተማሪዎችን ዝርዝር እየጠበቀ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር ለቲክቫህ ገልጿል።
የመውጫ ፈተና ውጤት መገለፅን ተከትሎ፥ COC የሚወስዱ አመልካቾች (በድጋሜ ተፈታኞችን ጨምሮ) ምዝገባ እንደሚደረግ ሚኒስቴሩ አረጋግጧል።
የCOC ምዘና አመልካቾች ምዝገባ በጊዚያዊነት ከየካቲት 10/2017 ዓ.ም በኋላ ለመጀመር መታቀዱን ሚኒስቴሩ ጠቁሟል።
በዚህም ምዘናውን በየካቲት ወር መጨረሻ ወይም በመጋቢት ወር የመጀመሪያ ሳምንት ለመስጠት በጊዚያዊነት መታቀዱን ከሚኒስቴሩ ሰምተናል።
✨ Share with your Friends
🎖📖🎖