የምንወደውና የምናከብረው ወንድማችን ኡስታዝ Ibnu Munewor ሴቶችን መበደል በሚል ርዕስ ይህን ብሎ ነበር
=========
"ሚስቱን ለመፍታት 200ሺ የሚጠይቅ አለ እኮ"🤔
ሙሉውን የ7 ደቂቃ ተግሳፁን በቴሌግራም ቻናሌ አድምጡት።
(https://t.me/EzedinSultan14)
"በሀገር አቀፍ ደረጃ ያለ ችግር ነው። ለሱና የቀረቡ በርካታ ወንድሞች ሴቶችን እየበደሉ ነው። የሱና ሸዓኢር (መገለጫ) የሚታይባቸው፣ አለባበሳቸው ያማረ፣ ፂማቸው ያደገ፣ ነገር ግን ሴቶችን የሚይዙበት ከሌሎች (ለሱና) ምንም ቅርበት ከሌላቸው የከፋ ጭካኔ የተሞላበት ነው።
በመጀመርያ ሱና ማለት ሙዐመላታችንንም(አኗኗራችንንም) ያካትታል። ከሰዎች ጋር ያለንን መስተጋብር ያካትታል። ነብዩ صل الله عليه وسلم "ከናንተ በላጭ ማለት ለቤተሰቡ(ለሚስቱ) በላጭ የሆነው ነው። እኔ ለቤተሰቤ ከናንተ በላጭ ነኝ" አሉ። ይሄ ሱና ለምንድነው የሚዘነጋው?
ውጫዊ ነፀብራቆች ላይ ማተኮር ዋጋ አለው አይካድም። ሰዎች ላይ በደል መፈፀም ግን ይሄንን ከመተው የከፋ ነው። ፂም ከመላጨት፣ ልብስ ከማስረዘም የከፋ ነው። ይሄ (ወንጀልነቱ)ራስህ ጋር የሚቆም ነው። ተሻጋሪ በደል ግን ከባድ ነው። ይቅርታውን ካላገኘህ የማትላቀቀው ነገር ነው። ይህን አላህ ይቅር ሊልህ ይችላል። (ሰው መበደል ግን ሰውየው ይቅር ካላለህ አላህ ይቅር አይልህም)
ደግሞ ሚስቱ ላይ በደል የሚፈፅም ሰው በምን መልኩ ነው ልጁን ተርቢያ(በጎ አስተዳደግ) እያደረገ ያለው . . . . "
ከድምፅ ቅጂው የተቀነጨበ። ብዙ ጉድ ዘርዝሯል። አድምጡ፣ ተገሰፁ፣ አሰራጩ!