ኧረ በቃኝ ይሄስ ዓለም
ቀኔ ጎድሏል ሙሉ አይደለም።
ልሂድ ልግዛ ፣ አንዲት ገመድ
ልጓዝ ልብረር ፣ በሙት መንገድ።
ያስከፋኛል አገዛዙ ፣
ዙሪያው ገባው አያያዙ
የሰው ክፋት ጉድ ፣ መዘዙ
አላፈራም … ከምዘራው
እንባዬን ነው የማዘራው።
:
ልሂድ በቃ ልሰናበት…
ዘመኔ ላይ ልፍረድበት …
አንዲት ገመድ ላንዲት አንገት
በሽንቁሯ ልለፍበት ፤
ብዬ ጀመርኩ የሙት ጉዞ
ልቤ ቀልቤ ተመርዞ … ።
:
ግና ከንቱ…
ምን ዋጋ አለው?
:
አገኘኋት ስረማመድ
ያቺን ሸጋ ልጃገረድ
ገለጠችው ያንን ከንፈር
ይኸው ሳቀች ለክፋቱ
ልኑር በቃ ምናባቱ!
@Yoppoem
ቀኔ ጎድሏል ሙሉ አይደለም።
ልሂድ ልግዛ ፣ አንዲት ገመድ
ልጓዝ ልብረር ፣ በሙት መንገድ።
ያስከፋኛል አገዛዙ ፣
ዙሪያው ገባው አያያዙ
የሰው ክፋት ጉድ ፣ መዘዙ
አላፈራም … ከምዘራው
እንባዬን ነው የማዘራው።
:
ልሂድ በቃ ልሰናበት…
ዘመኔ ላይ ልፍረድበት …
አንዲት ገመድ ላንዲት አንገት
በሽንቁሯ ልለፍበት ፤
ብዬ ጀመርኩ የሙት ጉዞ
ልቤ ቀልቤ ተመርዞ … ።
:
ግና ከንቱ…
ምን ዋጋ አለው?
:
አገኘኋት ስረማመድ
ያቺን ሸጋ ልጃገረድ
ገለጠችው ያንን ከንፈር
ይኸው ሳቀች ለክፋቱ
ልኑር በቃ ምናባቱ!
@Yoppoem