Posts filter






🔴 ከክልሉ መዲና ይልቅ ዱባይ ይቀርባቸዋል በሚል የተገመገሙት ሁለት የክልሉ ባለስልጣናት ስማቸው ከብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ምርጫ ተቀነሰ::
ዝርዝሩን በዕለቱ ዜና ተመልከቱ




በቦሌ ቡልቡላ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 በተለምዶ 93 ማዞሪያ አካባቢ የእሳት አደጋ መነሳቱ ተሰማ::


በ10 ደቂቃ ውስጥ በ3 መረጃዎች ዝግጅታችን ይዘን የምንቀርበው ዜና እንዳያመልጣችሁ። ልዩ መረጃ ነው።


የንብረት ማስመለስ አዋጅን በተመለከተ የአዋጁን ዓላማ፣ መሠረታዊ ይዘቶች፣ እንዲሁም ቀጣይ አተገባበር በተመለከተ የተፈጠሩ ብዥታዎችን ለማስተከከል በሚል ፍትህ ሚኒስትር መግለጫ ሰጥቷል።
በመግለጫውም፤ በኢትዮጵያ ይህ ህግ ከመውጣቱ በፊት በወንጀል የተገኘ ሃብት ማስመለስን በተመለከተ ራሱን የቻለና ወጥ የሆነ የሕግ ማዕቀፍ ያልነበረ በመሆኑ በሕግ ማስከበር ሂደት ክፍተት ፈጥሮ ቆይቷል ብሏል።
የፍትህ ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሀና አርአያስላሴ ቀደም ሲል የንብረት ማስመለስ አዋጁን በተመለከተ ያለ ህግ ቢኖርም ብዙ ህጎችን ያካተተ እንዳልነበር ገልፀዋል።
ምንጩ ያልታወቀ ንብረትን በተመለከተ በቅድመ ክስ ሂደት ማንኛውም ሰው ጉዳዩን እንዲያስረዳ የሚቀርቡ ጥያቄዎች እና አቤቱታዎች የፍርድ ቤቶች የሥነ ሥርዓት ሕጎችንና መርሆዎችን ተከትለው ማጣራት እንደሚደረግባቸው አንስተዋል።
አቤቱታ የሚቀርብባቸውም ሰዎች በሕጉ መሰረት ያላቸውን ማስረጃዎች የማቅረብ በፍርድ ቤት ዘንድ ቀርበው የመደመጥ መብታቸው እንዲከበርላቸው ይደረጋል ብለዋል።


@ለአለም አሰፋ

ሸገር ኤፍኤም


የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራር የነበሩት አቶ ብርሃኑ አዴሎ፤ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንን እንዲመሩ ተሾሙ

በቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የስልጣን ዘመን ለስድስት ዓመታት ገደማ የካቤኔ ጉዳዮች ኃላፊ ሆነው የሰሩት አቶ ብርሃኑ አዴሎ፤ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንን (ኢሰመኮ) እንዲመሩ በፓርላማ ተሾሙ።

አቶ ብርሃኑ የብሔራዊው የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት፤ ተቋሙን ለአምስት ዓመታት የመሩትን ዶ/ር ዳንኤል በቀለን በመተካት ነው። ዶ/ር ዳንኤል ከኃላፊነታቸው የተሰናበቱት፤ የስራ ዘመናቸው ባበቃበት ባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር ነበር።

ላለፉት አምስት ወራት ኢሰመኮን የመምራት ኃላፊነት በተጠባባቂነት ተረክበው የቆዩት የእርሳቸው ምክትል የነበሩት ራኬብ መሰለ ናቸው።

ተጠሪነቱ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሆነው ኢሰመኮ፤ ለሰብዓዊ መብቶች መስፋፋት፣ መከበር እና ጥበቃ የመስራት ስልጣን በአዋጅ የተሰጠው ነው።

በ2012 ዓ.ም. የተሻሻለው የኢሰመኮ ማቋቋሚያ አዋጅ፤ ተቋሙን በዋና ኮሚሽነርነት፣ በምክትል ዋና ኮሚሽነርነት እና በዘርፍ ኮሚሽነርነት የሚያገለግሉ ኃላፊዎች በተወካዮች ምክር ቤት እንደሚሾሙ ይደነግጋል።

ዛሬ ሐሙስ ጥር 22፤ 2017 በተካሄደው የተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ፤ ኮሚቴው የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር እንዲሆኑ አቶ ብርሃኑ አዴሎን በዕጩነት አቅርቧል። ላለፉት አስር አመታት በግል አማካሪነት እና ጠበቃነት እየሰሩ የቆዩት አቶ ብርሃኑ፤ በኢህአዴግ የስልጣን ዘመን በከፍተኛ የኃላፊነት ቦታ የሰሩ ናቸው።

@ኢትዮጵያ ኢንሳይደር


ቀሲስ በላይ መኮንን በአምስት ዓመት ጽኑ እስራት እና በ10 ሺህ ብር ተቀጡ

በሐሰተኛ ሰነድ ከአፍሪካ ኅብረት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ገንዘብ ለማውጣት በመሞከር የሙስና ወንጀል ክስ የተመሠረተባቸው ቀሲስ በላይ መኮንን በአምስት ዓመት እስራት እና በ10 ሺህ ብር ተቀጡ።

ከቀሲስ በላይ ጋር አንድ ላይ ክስ ቀርቦባቸው የነበሩት ሌሎች ሁለት ተከሳሾች ደግሞ እያንዳንዳቸው የአራት ዓመት እስራት እና የ3 ሺህ ብር ቅጣት እንደተፈረደባቸው ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዘግቧል።

የቅጣት ውሳኔውን ያስተላለፈው ሐሙስ ጥር 22/2017 ዓ.ም. የዋለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ መድብ ሦስተኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።

ጥፋተኛ የተባሉት ግለሰቦች ዐቃቤ ሕግ ክስ የቀረበባቸው የወንጀል ሕጉን እና የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ተላልፈዋል በሚል ነበር።

ግለሰቦቹ ላይ የተመሠረተው ክስ በአፍሪካ ኅብረት ስም የተዘጋጀ ሐሰተኛ ሰነድ በመጠቀም በኅብረቱ ዋና መሥሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ስድስት ሚሊዮን 50 ሺህ ዶላር ለማውጣት ሞክረዋል በሚል ነው።

ተከሳሾቹ በዐቃቤ ሕግ የቀረበባቸው ክስ እንዲሻሻል መቃወሚያ አቅርበው የነበረ ቢሆንም፤ ፍርድ ቤቱ ግን ሳይቀበለው መቅረቱ ይታወሳል። ይህን ተከትሎ ግለሰቦቹ የእምነት ክህደት ቃላቸውን የሰጡ ሲሆን ዐቃቤ ሕግ በበኩሉ ሦስት ምስክሮችን በችሎት አሰምቷል።

የዐቃቤ ሕግን ማስረጃ የመረመረው ፍርድ ቤቱ የተጠቀሰው የወንጀል ድርጊት መፈጸሙን ዐቃቤ ሕግ በማስረጃ ማረጋገጡን ጠቅሶ ተከሳሾቹ እንዲከላከሉ ብይን መስጠቱ ይታወሳል።

ተከሳሾቹ በዐቃቤ ሕግ የቀረበባቸውን ክስ በሚገባ መከላከል ባለማቻላቸው ፍርድ ቤት ጥፋተኛ ናቸው ሲል ከሁለት ሳምንት በፊት ወስኗል።

ይህን ውሳኔ ተከትሎ በተላለፈው የቅጣት ውሳኔ መሠረት 1ኛ ተከሳሽ ቀሲስ በላይ መኮንን በአምስት ዓመት ጽኑ እስራት እና በ10 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ ቀሪዎቹ ሁለት ተከሳሾች ደግሞ እያንዳንዳቸው በአራት ዓመት እስራት እና የ3 ሺህ ብር ቅጣት ተወስኖባቸዋል።

በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የኦሮሚያ ቤተ ክህነትን ለመመሥረት በነበራቸው እንቅስቃሴ የሚታወቁት ቀሲስ በላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የጠቅላይ ቤተ ክህነት ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ነበሩ።




(ዘ-ሐበሻ ዜና) ከዚህ ቀደም በሕዝብ ቅሬታ ምክንያት ከኃላፊነታቸው የተነሱት አቶ ብርሃኑ አዴሎን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽንን እንዲመሩ ዕጩ ሆነው ቀረቡ።
በሕዝብ ቅሬታ ምክንያት በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ተደርገው የነበሩትን አቶ ብርሃኑ አዴሎን፣ አሁን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንን በኮሚሽነርነት እንዲመሩ እጩ ሆነው መቅረባቸው ተገልጿል።
በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ዘመን፣ አቶ ብርሃኑ እስከ 1998 ዓ.ም. ድረስ የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ ሚኒስትርና የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ነበሩ፡፡ በወቅቱ ከተወለዱበት የደቡብ ክልል ካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ ነዋሪዎች አዲስ አበባ ድረስ በመምጣት በአቶ ብርሃኑ ላይ የተፈራረሙትን የቅሬታ አቤቱታ (ፔቲሽን) ለቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ማስገባታቸውን በወቅቱ ተዘግቦ ነበር፡፡ በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር የተቋቋመ አጣሪ ኮሚቴ ባቀረበባቸው ሪፖርት ከካቢኔ ጉዳይ ሚኒስትርነታቸውና ከኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነታቸው እንዲነሱ መደረጉም አይዘነጋም፡፡
ከዚያም በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተርነት ከ10 ዓመት በፊት ሲመሩ የነበር ሲሆን ከዚያም ስልጣናቸው "በቀረበባቸው ቅሬታ" ተነስተው ነበር፡
አሁን አቶ ብርሃኑ አዴሉ፣ ስልጣናቸውን የለቀቁትን የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነርን ተክተው እንዲመሩ እጩ ሆነው መቅረባቸው ታውቋል።
ከሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ያገኙት አቶ ብርሃኑ በዓለም አቀፍ ሰብዓዊ መብቶች ከሕንድ አገር የማስተርስ ዲግሪያቸውን ተቀብለዋል።




𝐎𝐅𝐅𝐈𝐂𝐈𝐀𝐋: (ዘ-ሐበሻ ዜና) በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ በሚገኘው ፖቶማክ ወንዝ 64 ሰዎችን የጫነ ንብረትነቱ የአሜሪካ አየር መንገድ የሆነ አውሮፕላን እና 3 ወታደሮችን የጫነ የጦር ሂሊኮፕተር መጋጨታቸውን ተከትሎ በተፈጠረው አደጋ ዙሪያ፣ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ስለአደጋው ሙሉ በሙሉ ገለጻ እንደተደረገላቸው ምሽቱን በሰጡት መግለጫ ገለጹ። "እግዚአብሔር ነፍሳቸውን ይማር" ሲሉ የጀመሩት ትራምፕ "በመጀመሪያ ምላሽ ሰጪዎቻችን እየሰሩት ላለው አስደናቂ ስራ እናመሰግናለን፣ ሁኔታውን እየተከታተልኩ ሲሆን ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎችን እሰጣለሁ" ብለዋል።
ትራምፕ የአደጋው መንስኤ ምን እንደሆነም ጥያቄ አንስተው "ይህ መፈጠር ያልነበረበት መጥፎ ሁኔታ ነው... ጥሩ አይደለም!!!" ብለዋል።
የአደጋው መንስኤ በትክክል ምን እንደሆነ ተጣርቶ በሚመለከታቸው ባለስልጣናት ይነገራል። እስካሁን ነፍስ ለማዳን እየተደረገ ባለው ጥረትም የ18 ሰዎች አስከሬን እንደተገኘ ከዚህ ቀደም ባቀረብነው መረጃ ላይ መግለጻችን ይታወሳል።






አማዞን ዛሬ ከፍተኛ ቅናሽ የተደረገባቸውን ምርቶች ይዟል። ምናልባት የሚፈልጉትን ሊያገኙ ስለሚችሉ ይመልከቱ።
https://amzn.to/4aFjEu5




በደቡብ ሱዳን ዩኒቲ ግዛት አነስተኛ አውሮፕላን ተከስክሶ የ20 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ።




እንደምን አደርሽ እማማ ኢትዮጵያ?!
💚💛❤
በሐራሬ በሰርግ የሚለበስ አልባሳት

20 last posts shown.