{==========================} https://t.me/joinchat/AAAAAEPpTBShn5X7GEubZg
[መ ን ታ' መ ን ገ ድ]
ህይወትን በማስመሰል ውስጥ መኖርን ካኖርናት ህይወት አልባ ህይወት መሆኗ ጥርጥር የለውም የሰው ልጅ ራሱን እያታለለ ከመኖር በላይ ትልቅ በሽታ የለውም ማንም ሰው ራሱን ቢያታልልም ውሎ አድሮ ግን እራሱን መውቀስ ይጀምራል የሚያሳዝነው ደግሞ ከዚያ ከሚኖርበት አሳዛኝ ህይወት በአሳዛኝ ሁኔታ ቢወጣም ለሁለተኛው ምዕራፍ ህይወቱ የውሳኔ ባለቤት መሆን አለመቻሉ ነው ብዙ ግዜ የብዙሃኖቻችን ህይወት በአስቸጋሪ እና በአሳዛኝ ሁኔታ የሚመራው ለሰዎች ማስመሰልን ስለምንወድ ነው…… ትዳር በአሉባልታ የማይመራ አንዱን አጣሁ ብሎ በአንዱ እኖራለሁ በሚል እንቆቅልሽ ጨዋታ የማይቀጥል ትልቅ መስዕዋት ሊከፈልለት የሚገባ ትልቁ የህይወታችን ምእራፍ ነው ድሮ ድሮ እናቶቻችን ትልቅ መስእዋት የከፈሉለት ትዳር ዛሬ ዛሬ እኛ የእንቆቅልሽ ጨዋታ ያህል እንኳ ክብር ስንሰጠው አይታይም……………"
ውድ እና የተከበራችሁ የዘዋጅ ሰኢድ የዋትሳፕ፣ እና የቴሌግራም ቻናል ቤተሰቦች አሰላሙ ዓለይኩም ወራህመቱሏህ ወበረካትሁ...
"
"
ይህ ዘወትር እሁድ በኡኽት ሙሃመድ እየተዘጋጀ የሚቀርብላችሁ የመንታ መንገድ ፕሮግራም ነው
"
"
የዛሬዋ ባለ መንታ መንገድ እህታችን እንዲህ ስትል ትጀምራለች የፍቅር ጥያቄ የቀረበልኝ ገና በለጋ እድሜየ ነበር ያኔ ለአቅመ ትምህርት እንደደረስኩ በአንድ ሰፈር ያለን ተማሪዎች ተጠራርተን ወደ ትምህርት ስናመራ የእኔው ፈላጊም ከመካከላችን ነበር በአንድ ሰፈር ተወልደን ያደግን በአንድ ትምህርት ቤት ተምረን ያደግን ነን በሰአቱ ምንም እንኳ እንደሚወደኝ ባይነግረኝም ከብዙ አመት ቡሃላ ማለትም የ6ተኛ ክፍል ተማሪ እያለሁ ቤተሰቦቼን ጠየቀ አባቴም ልጄ ገና ለትዳር አልደረሰችም በማለት መለሰው ከዚያ ቡሃላ ብዙ ወንዶች ለትዳር ቢጠይቁኝም የእሱ ሁኔታ ግን ትምህርትን እስከማቋረጥ ደረሰ እኔም በተለያዩ ወንዶች ከምቸገር በሚል 7ተኛ ክፍል እያለሁ ወደ አረብ ሀገር ተሰደድኩ ከተወሰነ የአረብ ሀገር ቆይታየ እንደተመለስኩ በቤተሰብ የመጣን ትዳር መሰረትኩ… ምንም እንኳ ውስጤ ባያምንበትም ለሰዎች እልህ በሚል ነበር ትዳር የመሰረትኩት…… ነገር ግን ትዳር ላይ ሆኘ ከባለቤቴ ጋር በቤቴ ውስጥ ሰላም ማስፈን አልቻልኩም ህይወት ለእኔ ከባድ ሆነች ትዳር በመሰረትኩ በ4 ወሬ ነበር ከትዳሬ የተፈታሁት…… ተመልሸም ወደ አረብ ሀገር ተመለስኩ አረብ ሀገር እደተመለስኩ አንድ ስልክ ተደወለ አነሳሁት ማመን አቃተኝ ገና ትምህርት ቤት እያለሁ ያኔ አብረን እየቦረቅን ያደግነው የልጅነት አፍቃሪየ ነበር ዛሬ የዩኒቨርስቲ ተማሪም እንደሆነ ነግሮኝ ዛሬም የእኔው አፍቃሪ እንደሆነ ነገረኝ… … እኔም ድሮ ቦታ ባይኖረኝም ግን ለእኔ መጥፎን አያስብም ከእሱ በላይ እኔን የሚያውቀኝ የለም በሚል እሽ አልኩት…… ነገር ግን በመካከላችን አንድ ነገር አለ እሱም ቤተሰቦቹ እኔን እንዲያገባ አይፈልጉም ምክንያቱም ከዚህ በፊት ቤተሰቦቼን ጠይቀው እቢ ስለተባሉ እና አግብቼም ስለተፈታሁ……እናም እሱ አንድ ሃሳብ አመጣልኝ እሱም ቤተሰቦቹ የሚያጩለትን አግብቶ ከዚያም እሷን ፈትቶ እኔን ማግባት
"
"
እኔን ግራ ያጋባኝ ነገር ቤተሰቦቼ የመረጧትን አልወዳትም ግን እነሱን ለማስደሰት ላግባ እና ልፍታት እና አግቢኝ አለኝ እሽ ብለው ቤተሰቦቹ ለእኔ ጥሩ አመለካከት ይኖራቸው ይሆን?? ምንም የማታውቀውን እህታችንንስ አግብቶ ቢፈታ ለእኔስ ታማኝ ባል ይሆን ይሆ?? ደግሞ አሁን አሁን ለእሱ ትልቅ ቦታ እያለኝ መጥቷል ደግሞ ቤተሰቦቹ እኔን እንዲያገባ አይፈልጉም ታድያ እናንተ በእኔ ቦታ ብትሆኑ ምን ታደርጋላችሁ?? እባካችሁ ውሳኔ መወሠን ተቸግሬያለሁ እና ሃሳባችሁን ስጡኝ
ውድ የዘዋጅ ሰኢድ ቤተሰቦች የእህታችን ሃሳብ ይህንን ይመስላል እደተለመደው መልካም ሃሳባችንን እናጋራት የእኛም መልዕክት ነው
አዘጋጅ "ኡኽት ሙሃመድ
From Zewaj Seid For Solution Whatsapp Group& Tele gram
ለሃሳብ& ለአስተያየት👇👇👇🕶
@Haytekulwulilah92_bot
@Haytekulwulilah92_bot
👒👒👒👒👒👒👒👒👒👒