ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Religion


የኢትዮጵያዊው ቄርሎስ የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ሕይወትና ትምህርት ይቀርብበታል።
https://t.me/abagiyorgismnale
ለሌሎች በማጋራት መንፈሳዊ ግዴታችንን እንወጣ
ለጥያቄዎችና ለአስተያየት
@Dnmikii @feke17

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Religion
Statistics
Posts filter


ጌታ ሆይ ለሳምራዊቷ ሴት እሰጥሻለሁ ያልካትን ውሃ ለኔም ስጠኝ።








አርምሞ ጽርአት በሌለበት

አርምሞ ጽርአት በሌለበት
በልሳነ መላእክት
የምትኖር በምስጋና በክብር
አንተ ነህ እግዚአብሔር

አዝ........

የሆንከን አንባ መጠጊያችን
መለስከን ወደ ርስታችን
ውዳሴ ቅኔ አለን ለስምህ
በዝቶልን ቸርነት ሰላምህ
ቅዱስ እግዚአብሔር

አዝ.........

በርአድ በፍርሀት ልቡና
ፍጥረቱ የሚሰጥህ ምስጋና
ሆነሀል የህይወታችን ወደብ
ስጦታህ በቃል የማይገደብ
ቅዱስ እግዚአብሔር

አዝ..............

ገናና ስምህም የተፈራ
በመአልት በሌሊት የሚጠራ
ከኛ ላይ አርቀህ ጨለማን
ሰጠኸን የሚያስደንቅ ብርሀን
ቅዱስ እግዚአብሔር

አዝ........

የፈጠርክ ሰውና መላእክትን
ሊያከብሩ ሊያወድሱ ስምህን
በሰማይ በምድርም ውስጥ ያሉ
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ይላሉ
ቅዱስ እግዚአብሔር

አዝ......


#ነቢዩ_ዮናስ

ይህ ነቢይ ከደቂቅ ነቢያት መካከል ይመደባል እኒህም ፦

ሆሴዕ
አሞጽ
ሚክያስ
ኢዮኤል
አብድዩ
ዮናስ
ናሆም
ዕንባቆም
ሶፎንያስ
ሐጌ
ዘካርያስ
ሚልክያስ

ከነዚህም መካከል #ነቢዩ_ዮናስ ከራሱ መጽሐፍ ውጭ የተጠቀሰ ነቢይ ነው /2ነገ 14:5/ የእስራኤል ነቢይ ነው የነበረትም ዘመን በዳግማዊ ኢዮርብዓም ዘመነ መንግሥት 825-784 ቅ.ል.ክ ነው።

በትዉፊት እንደሚነገረው ዮናስ ነቢዩ ኤልያስ ከሞት ያስነሣው የሠራፕታ መበለት ልጅ ነው። /1ነገ 18:10-24/

ዮናስ ሦስት ሌሊት ሦስት መዓልት በከርሠ አንበሪ በመቆየቱ ጌታችን በመቃብር ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት አድሮ መነሳቱን ያጠይቃል #ክብር ይግባውና ጌታችንም በመዋዕለ ሥጋዌ ሲያስተምር ይህንን ታሪክ ጠቅሶ አስተምሯናል /ማቴ 12:39፤ሉቃ 11:29/

ነቢዩ ዮናስ ከምድረ እስራኤል ውጭ/በነነዌ/ በማስተማሩ ነቢየ አሕዛብ ይባላል።








አምላክ ወደ ታች ፍጥረት ወደ ላይ ሲመለከት የሚገናኙባት ይህች "የዐይናችን ማረፊያ" ናት።


#ኦርቶዶክስተዋሕዶ #ጾመነነዌ

አባታዊ መልዕክት !

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የ2017 ዓ.ም የጾመ ነነዌ የሰላምና የጸሎት አዋጅ መግለጫ ሰጥተዋል።

ከመግለጫቸው የተወሰደ ፦

" ለችግሮች ሁሉ መፍትሔ አላቸው፤ መፍትሔውም የሚገኘው ከእግዚአብሔርና ከእኛ ነው፤ ከእኛ በንስሓ ተመልሰን ከልብ እግዚአብሔርን ይቅርታ መጠየቅና ከክፉ ተግባራችን በእውነት መጸጸት ይጠበቃል፤ እግዚአብሔር ደግሞ ይህንን ዓይነቱ ንስሓ ከኛ መኖሩ ሲመለከት ምሕረትና ይቅርታን ይለግሰናል፤በዚህም መፍትሔና ፈውስ ይገኛል።

ከዚህ አንጻር በአሁኑ ጊዜ ለሀገራችንና ለዓለማችን ስጋት የሆኑ የጦርነት ክሥተቶች፣ የመሬት መንቀጥቀጥ፣ የአየር መዛባት፣ የድርቅ መከሠት፣ የጎርፍ መጥለቅለቅ የሰላም መደፍረስ፣ የሰላማውያን ወገኖች መጎዳት፣ የፍቅርና የአንድነት መላላት ወዘተ. . . . ከምድራችን ተወግደው ፍጹም ምሕረትና ሰላም እናገኝ ዘንድ በኃጢኣታችን ተጸጽተን በምህላ ንስሓ መግባት አለብን።

ከዚህ አኳያ ከጥንት ጀምሮ በቤተክርስቲያናችን ቀኖናዊ ሥርዓት መሠረት በየዓመቱ የሚጾመው ጾመ ነነዌ ለዚህ አመቺ ጊዜ ስለሆነ ከየካቲት 3 ቀን 2017 ዓመተ ምሕረት ጀምሮ ለሦስት ቀናት ከልኂቅ እስከ ደቂቅ ሁላችንም ጠዋትና ማታ በየቤተክርስቲያኑ ዐውደ ምሕረት እየተገኘን በንስሓ በዕንባ በጸሎት በምህላ የእግዚአብሔርን ምሕረትና ይቅርታ እንድንጠይቅ፤ እንደዚሁም በሀገራችንና በውጭ ያላችሁ ሊቃውንተ ሕዝብ ቀኖናውን ጠብቃችሁ ይህንን በማስፈጸም ምህላውን በቀኖናው መሠረት እንድታከናውኑ በእግዚአብሔር ስም አባታዊ መልእክታችንን እናስተላልፋለን። "

(የቅዱስነታቸው ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)


ኢየሱስ ክርስቶስ:-

ለሁሉ ያስባል ሁሉንም ያጠግባል

ለዕውራን ያዩ ዘንድ ብርሃንን ይሰጣቸዋል፡፡

የተዘጉ መስኮቶችን ይከፍታል ህሙማንን ይሰማቸዋል፡፡

የተደፈነችውን ጆሮ እንድትሰማ ያደርጋል፡፡

ከሰውነት የለምፅን ልብሶች ገፍፎ የስጋን መጎናፀፊያ ያለብሳል፡፡

የደረቀውን የእጅ ክንድ ያቀናል፣

የአንካሳውን እግር እንዲሄድ ያደርጋል

ነፍስን ወደ ሕዋስዋ ይመልሳታል

መንፈስንም በማደሪያዋ ያኖራታል፡፡

አለቆች ባሏቸው አጋንንት የእርያን መንጋ ያሰጥማል ከደከመችውም ሰውነት ደዌን ያርቃል፡፡

ቅዳሴ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ




ኢየሱስ ክርስቶስ፡-

ጨለማን ያሳደደው ብርሃን

ዓለምን ሁሉ ያበራው ፋና

የማይነዋወጥ መሰረትና

የማይፈርስ ግንብ

የማይሰበር መርከብና

የማይሰረቅ ማህደር

የለዘበ ቀንበርና

የቀለለ ሽክም

እርሱ ለአባቱ ሃይል ጥበቡም የሚሆን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡




ቅዳሴ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ




በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

ጥር ፳፰ ጌታችን 5 እንጀራ 2 ዓሣ አበርክቶ 5 የገበያ ሕዝብ እንደመገበ

ጥር ሃያ ስምንት በዚህች ቀን ጌታችን ተአምራትን በማድረግ ሰባት እንጀራና ጥቂት ዓሣ ቆራርሶ አበርክቶ ብዙ ሰዎችን ያጠገበበት መታሰቢያ ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመዘገበው ይህ የጌታችን ተአምር በውስጡ ብዙ ምሥጢራትን የያዘ ነው እንጂ ስለ ሥጋዊ ምግብ ብቻ የተነገረ አይደለም፡፡ ማቴ 14፡13-23፡፡ የተመገቡትና የተቆጠሩት አምስት ሺህ ወንዶች ብቻ ናቸው እንጂ ሴቶችና ሕጻናት አልተቆጠሩም፡፡ ይህስ ለምን ነው ቢሉ ሴቶች በአደባባይ ሲበሉ በሃፍረት ዳር ዳር ስለሚሉ ነው፡፡ ሕጻናት ደግሞ ከሚበሉት የሚፈረፍሩት ይበዛልና ነው፡፡

ጌታችን ያንን ሁሉ ሕዝብ በመንደር አጠገብ ሊመግባቸው ሲችል ለምን አርቆ ወደ ምድረ በዳ ወሰዳቸው ከተባለ ስለ ሁለት ምክንያት ነው፡፡

አንድም ‹‹ጥንት አባቶቻችሁን ከመንደር (ከግብጽ) አውጥቼ አርባ ዘመን ሙሉ መና የመገብኳቸው እኔ ነኝ፤ አሁንም በሥልጣኔ በተአምራቴ መገብኳችሁ›› ሲላቸው ነው፡፡

አንድም ጌታችን ተአምራቱን ከመንደር አጠገብ አድርጎት ቢሆን ኖሮ ሁልጊዜ ክፋትንና ጠማማ ነገርን ማሰብ ለአይሁድ ልማዳቸው ነውና ‹‹ፈጣን ፈጣን ደቀ መዛሙርቱን በጎን ወደ መንደር እየላከ ያስመጣው ነው›› ይሉት ነበር፡፡ ስለሆነም ጌታችን ለጥርጥር ምክንያት እንዳይኖራቸው አድርጎ ነው ተአምራቱን የገለጠላቸው፡፡ ጊዜውም አመሻሽ ላይ ነበርና ምሽት ላይ ያደረገበትም ምክንያት ጠዋት ላይ ቢሆን ኖሮ ‹‹የበላነው ሳይጎድል ነው ያበላን›› ብለው ከማመን ይርቁ ነበር፡፡

በተጨማሪም በበረሃ ያውም በምሽት ሕዝቡን በውኃ አጠገብ በሣር ላይ አስቀምጧቸው መመገቡ ‹‹በፍጻሜው ዘመን በምቹ ስፍራ በመንግሥተ ሰማያት መንፈሳዊ ምግብ እመግባችኋለሁ፤ በውኃ (በጥምቀት) በሚገኝ ክብርም አከብራችኋለሁ›› ሲላቸው ነው፡፡ ተአምራቱን ከውኃ ዳር ማድረጉ ‹‹መታጠቢያ ብናጣ በደንብ ሳንበላ ቀረን›› እንዳይሉ ነው፡፡ ሳር የበዛበት ቦታ ላይ ማድረጉም ‹‹መቀመጫ ብናጣ በደንብ ሳንበላ ቀረን›› እንዳይሉ ነው፡፡

አምስቱ እንጀራ የአምስቱ አዕማደ ምሥጢር ማለትም የምሥጢረ ሥላሴ፣ የምሥጢረ ሥጋዌ፣ የምሥጢረ ጥምቀት፣ የምሥጢረ ቁርባንና የምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን ምሳሌዎች ናቸው፡፡ ሁለቱ ዓሣ ደግሞ የፍቅረ እግዚአብሔርና የፍቅረ ቢጽ ምሳሌዎች ናቸው፡፡ ፍቅረ እግዚአብሔር ማለት እግዚአብሔር አምላክን በፍጹም ነፍስና በፍጹም ሐሳብ መውደድ ነው፡፡ ፍቅረ ቢጽ ደግሞ ባልንጀራን እንደራስ አድርጎ መውደድ ነው፡፡ አንድም ደግሞ እንጀራውና ዓሣው የቅዱስ ሥጋውና የክቡር ደሙ ምሳሌ ነው፡፡
ከበዓሉ ረድኤት በረከት ያሳትፈን ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር




"በጥጃና በበሬ መካከል የክብደት እንጅ የዕውቀት ልዩነት የለም።"

[ መጋቤ ሐዲስ እሸቱ ዓለማየሁ ]




ቤተ ክርስቲያን ታመሰግንሻለች

"ያዘነች ስትሆን በልጅሽ በወዳጅሽ ትንሣኤ የተጽናናችው፡፡ የተዋረደች ስትሆን በድንግልናሽ ቡቃያ መውጣት ከፍ ከፍ ያለችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታመሰግንሻለች ፡፡ በዕለተ ዓርብ ከልጅሽ ቀኝ በፈሰሰው ውኃ ተጠምቃ ፣ የጎኑን ደም ተቀብታ ቅድስት ቤተክርስቲያን ታመሰግንሻለች ። የልዑል እግዚአብሔር በግ የተባለ ልጅሽ አማኑኤል የተሞሸረባት መርዓዊ ሰማያዊ የተባለባት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታመሰግንሻለች"

አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

20 last posts shown.