አሜሪካ በኮሮና ቫይረስ 85 ሺህ 498 ተጠቂዎችን በማስመዝገብ ከአለም ቀዳሚ ሀገር ሆናለች።
አሜሪካ አሁን በኮሮና ቫይረስ የተጠቂዎች ቁጥር ከቻይናና ከጣልያን በመብለጥ ከየትኛውም የአለማችን ሀገር ቀዳሚ ሆናለች፡፡
እንደ ጆንስ ሆፕኪንስ መረጃ ከሆነ ቻይና 81 ሺህ 340 ተጠቂ ሲኖራት ጣልያን ደግሞ 80 ሺህ 589 ተጠቂ አላት፡፡
በአሜሪካ በኮሮና ህይወታቸው ያለፈው1 ሺህ 307 ሲሆኑ ከጣልያን 8 ሺህ 215 እና ከቻይና 3 ሺህ 292 ያንሳል፡፡
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሀገራቸው በፍጥነት ወረርሽኙን አሸንፋ ወደ ወትሮው እንቅስቃሴ ትመለሳለች ብለው የነበረ ቢሆንም ሁኔታዎች እየከፉ እንጂ እየተሸሻሉ አልሄዱም፡፡
ትናንት ከሰአት ትራምፕ የምንመረምራቸው ሰዎች ቁጥር ከሌላ ሀገራት አንፃር በመብዛቱ ነው የተጠቂዎች ቁጥር ሊበዛ የቻለው ብለው ነበር፡፡
ሌሎች ሀገራት እንደኛ ቢመረምሩ ኖሮ ከኛ የበለጠ ተጠቂዎች ይኖራቸው ነበር ብለዋል፡፡
በተለይ በቻይና ምን ያህል የኮሮና ተጠቂ እንዳለ ምንም ማወቅ አንችልም ሲሉ መናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
እንደ ምክትል ማይክ ፔንስ ከሆነ በ 50ውም የአሜሪካ ግዛት ኮሮና ምርመራ እየተካሄደ ሲሆን ከ552 ሺህ በላይ ምርመራዎች ተካሂደዋል፡፡
ትራምፕ የቻይናውን ዢ ቺን ፒንግን በስልክ አውርተዋቸው እንደነበር የገለፁ ሲሆን ወረርሽኙን የቻይና ቫይረስ ብለው በመጥራትዎት ዢ ቺን ፒንግ ቋንቋዎትን ያርሙ ሲሉ አልገሰፅዎትም ወይ ሲሉ ጋዜጠኞች ለጠየቋቸው ጥያቄ ይሔን መሳይ ንግግር በመሀላችን እንደነበረ ተደርጎ የሚወራው ሀሰት ነው ብለዋል፡፡
(ኢትዮ ኤፍ ኤም)
መጋቢት 18ቀን 2012 ዓ.ም
---------------------------------------------------
ክቡራን ቤተሰቦች ሀሳብ አስተያየታችሁን የዜና የመረጃ ጥቆማችሁን ከሰር ባለው ሊንክ አድርሱኝ:: አመሰግናለሁ
አቤል ብርሀኑ (የወይኗ ልጅ)
👉@abel21bot