መረጃ፣ መረጃ፣ መረጃ!
የኒውዮርክ አስተዳዳሪው አንድሪው ኩኦሞ በቫይረሱ ዙርያ ጋዜጣዊ መግለጫ በየቀኑ ይሰጣሉ። ኧረ እዛ ሳንሄድ በአህጉራችን ውስጥ የኬንያ፣ የደቡብ አፍሪካ እና የግብፅ የጤና ሀላፊዎች እንዲሁ በተደጋጋሚ መረጃዎችን በድረ-ገፆቻቸው፣ የሶሻል ሚድያዎች እንዲሁም በቲቪ እና ሬድዮ እየቀረቡ ይሰጣሉ።
እኛ ሀገር እየታየ ያለው አሰራር ይህ አይደለም። እውነተኛውም፣ ሀሰተኛውም መረጃ ውስጥ ውስጡን ሶሻል ሚድያ ላይ ከተራገበ እና ህዝብን ካወዛገበ በሁዋላ የሆነ ነገሩ ይፋ ይደረጋል።
ያለንበት ለየት ያለ ግዜ ነው። በበሽታው ከሚጠቃው ቀጥሎ በሳይኮሎጂም፣ በመረጃ መዛባትም መደናገጥ ውስጥ እየገባ ያለው የህዝብ ቁጥር ቀላል አይደለም። ስለዚህ ትክክለኛ መረጃ በወቅቱ ይሰጥ።
ይህ ከታች የምታዩት "ኢትዮጵያ ውስጥ በኮሮና ቫይረስ የመጀመርያው ሞት ተከሰተ" የሚል ዜና ህዝቡን ሲያስጨንቅ ያደረ እና ሁዋላ ላይ ከቴሌግራም ቻናሉ ላይ የጠፋ መረጃ ነው።
በቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታልም አዲስ ታማሚ ተገኘ ተብሎ በብዙ ሰዎች ሲሰራጭ የነበረው መረጃ እስካሁን በጤና ሚኒስትርም፣ በህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትም አልተረጋገጠም፣ ህዝቡን ግን ከማስጨነቅ ወደሗላ አላለም።
እንዲህ አይነት በብዛት የሚሰራጩ መረጃዎች ተገቢውን ማረጋገጫም ሆነ ማስተባበያ በፍጥነት ይፈልጋሉ።
መልካም ቀን!
via eliasmeseret