Abuki Tech በነፃ‼️


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Religion


ስለ ቴክኖሎጂ እና እስልምና በቻልኩት አቅም በነፃ አሳዉቃለሁ። https://t.me/abukiweb/88
አላማዬ: በቴክኖሎጂና እስልምና ላይ አንድነትን ማበረታታት፣ እና ማገልገል ነዉ።
"I’m a Full Stack Developer eager to grow"
የቻናሉ ስህተት እኔን ብቻ ይመለከታል፤ እስልምና ከጉድለቶች የራቀ ነው።
ለአስተያየትና ለማንኛዉም ትብብር:  @abuki211

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Religion
Statistics
Posts filter


ግን ወንድሜ ይህ ነገር ማንበቡ እንኩዋን ከከበደህና ከደበረህ 😊😊አንድ ነገር ልንገርህ
~
በየቦታዉ የምታያቸዉ በሀሳብ ሀብታም የሚያደርጉ ወሬዎችና በአቋራጭ ባለፀጋ የምትሆን የሚመስልህ ስሜትህ አዉልቀህ ጣለዉ።ሌላዉ ዉሸት እና ማጭበርበር ብቻ ነዉ።
ሌላዉ ብሩን ብቻ አይተህ ከተማርክ ግማሽ ላይ ታቆማለህና አስብበት‼️

ወንድምህ👇
@abukiweb


Full-stack development ለመማር ላሰባችሁ ብቻ‼️

1. Full-stack development ምንድን ነው?
  •  Full-stack development ማለት የድር (web) አፕሊኬሽንን ሁለቱንም ጎኖች ማለትም የደንበኛውን (front-end) እና የአገልጋዩን (back-end) በአንድ ላይ ማልማት መቻል ነው። በአጭሩ የፊት ለፊቱን የሚታየውን ገጽታ እና ከጀርባ የሚሰራውን ፕሮግራም በአንድ ላይ መስራት ማለት ነው።

2. Full-stack developer የሚያደርገው ምንድን ነው?
  •  Full-stack developer የሚከተሉትን ጨምሮ የተለያዩ ስራዎችን ይሰራል፡
    *  የድር አፕሊኬሽን የፊት ገጽታን (user interface) መፍጠር (HTML, CSS, JavaScript በመጠቀም)
    *  ከአገልጋዩ ጋር መገናኘት (API መፍጠር እና መጠቀም)
    *  መረጃዎችን ማስተዳደር (database design እና management)
    *  አፕሊኬሽኑን በአገልጋዩ ላይ ማስኬድ (server deployment and configuration)
    *  ችግሮችን መፍታት (debugging and troubleshooting)
    *  አፕሊኬሽኑን ማዘመን እና ማሻሻል

3. ምን አይነት ቴክኖሎጂዎች በ Full-stack development ውስጥ ጥቅም ላይ ይውላሉ?
  •  የሚከተሉት በብዛት ጥቅም ላይ የሚውሉ ቴክኖሎጂዎች ናቸው፡
    *  የፊት ገጽታ (Front-end):
      *  HTML, CSS, JavaScript (የግድ አስፈላጊ)
      *  JavaScript Frameworks (React, Angular, Vue.js)
      *  CSS Preprocessors (Sass, Less)
    *  የኋላ ክፍል (Back-end):
      *  Node.js (ከ JavaScript ጋር)
      *  Python (Django, Flask)
      *  Java (Spring Boot)
      *  PHP (Laravel, Symfony)
      *  Ruby on Rails
    *  መረጃ ቋቶች (Databases):
      *  Relational Databases (PostgreSQL, MySQL, SQL Server)
      *  NoSQL Databases (MongoDB, Cassandra)
    *  ሌሎች:
      *  Git (version control)
      *  Docker (containerization)
      *  AWS, Azure, Google Cloud (cloud platforms)

4. Full-stack developer ለመሆን ምን መማር አለብኝ?
  •  የሚከተሉትን መማር ያስፈልጋል፡
    *  HTML, CSS, JavaScript (በደንብ)
    *  ቢያንስ አንድ የ JavaScript framework (React, Angular, Vue.js)
    *  ቢያንስ አንድ የ back-end ቋንቋ (Node.js, Python, Java, PHP, Ruby)
    *  Database design እና management
    *  API design እና development
    *  Server deployment እና configuration
    *  Git እና Version Control
    *  ችግር ፈቺነት (problem-solving skills)

5. Full-stack developer የሥራ ገበያ ሁኔታ እንዴት ነው?
  •  የ Full-stack developer የሥራ ገበያ በጣም ጥሩ ነው። ምክንያቱም ሁለቱንም ጎኖች መስራት የሚችሉ ባለሙያዎች ተፈላጊ ናቸው። ብዙ ኩባንያዎች የ Full-stack developersን ይፈልጋሉ። በተለይ ልምድ ያላቸው ባለሙያዎች በጣም ተፈላጊ ናቸው።

6. የ Full-stack developer ደመወዝ ምን ያህል ነው?
  •  የ Full-stack developer ደመወዝ እንደ ልምድ፣ ቦታ እና ኩባንያ ይለያያል። በአማካይ ግን ጥሩ ደመወዝ ያገኛሉ።
    *  በኢትዮጵያ ከ 15000 ሺ-150000 ሺ ወይም ከዛም በላይ፣ በአለም አቀፍ ደረጃ (በተለይ በአሜሪካ) አማካይ ዓመታዊ ደመወዝ ከ $50,000 እስከ $150,000 ዶላር ወይም ከዚያ በላይ ሊሆን ይችላል። እንደ ልምድ እና ክህሎት ይወሰናል።


ለመማር ከስድስት እስከ ዘጠኝ ወር ሊፈጅ ይችላል።

Share ✅
ቻናሉ ለመቀላቀል👇
https://t.me/abukiweb
https://t.me/abukiweb


ጊዜያችሁ በአግባቡ እና በእቅድ ተጠቀሙ ካለፈ ቦኃላ በጣም ይቆጫል።

Time management is another essential skill‼️

@abukiweb


Developer Roadmaps
👇👇👇
https://roadmap.sh/frontend


roadmap.sh  ለFull Stack Web Development ግልጽና የተደራጁ መመሪያዎችን የያዘ ድህረ ገጽ ነው። ምን መማር እንዳለብህ፣ እንዴት እንደ ምትማር እና ምን ግብዓቶች እንደሚያስፈልጉህ ያሳያል። ነጻ፣ ክፍት ምንጭ ነዉ ለ Web Developmnet  ጉዞህ በጣም ጠቃሚ ነው።

ሼር ✅

ቻናሉ ለመቀላቀል👇
https://t.me/abukiweb


"ለፍቶ አዳሪ የአላህ ወዳጅ ነው"

የሚለው አባባል በእስልምና እምነት ውስጥ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ጽንሰ-ሐሳብ ነው። ይህ የሚያመለክተው አንድ ሰው በሐቀኝነትና በትጋት በመሥራት የራሱንና የቤተሰቡን ኑሮ ለማሟላት ሲጥር አላህ ዘንድ ተወዳጅነትን እንደሚያገኝ ነው።

በእስልምና ውስጥ ለፍቶ አዳሪነት እንደ ትልቅ በጎ ተግባር ይቆጠራል፤ ነቢዩ  (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፡- "እጅግ በጣም ጥሩው ገቢ የአንድ ሰው በእጁ የሚሠራው ሥራ ነው።" (ቡኻሪ እና ሙስሊም )

ይህም አንድ ሰው በራሱ ጥረትና ድካም የሚሠራው ሥራ በአላህ ዘንድ እጅግ የተወደደና የተከበረ እንደሆነ ያሳያል።

ለፍቶ አዳሪነት አንድ ሰው ከሌሎች ሰዎች ላይ ጥገኛ እንዳይሆንና የራሱን ኑሮ በራሱ እንዲያሟላ ይረዳል። ይህ ደግሞ የእስልምና እምነት ለራስ ክብርና ለራስ መቻል ትልቅ ቦታ እንደሚሰጥ ያሳያል።

ከዚህም በተጨማሪ፣ ለፍቶ አዳሪነት የሰውን ችሎታና እውቀት ለማዳበርና ለማሳደግ እድል ይሰጣል። አንድ ሰው በሥራው ውስጥ ሲሳተፍ አዳዲስ ነገሮችን ይማራል፣ ልምድ ያገኛል፣ ችሎታውም ይጨምራል። ይህ ደግሞ ለግል እድገትና ለኅብረተሰቡ እድገት አስተዋጽኦ ያደርጋል።

ስለዚህ፣ "ለፍቶ አዳሪ የአላህ ወዳጅ ነው" የሚለው አባባል በእስልምና እምነት ውስጥ ለሥራ፣ ለራስ መቻልና ለልማት ያለውን ትልቅ ቦታ ያሳያል። ይህንን መገንዘብና በተግባር ማዋል ለእያንዳንዱ ሙስሊም አስፈላጊ ነው።

በተለይም የነብዩ  (ﷺ) የኡመር ኢብኑ አል-ኸጣብ እና የአቡበክር አስ-ሲዲቅን ሕይወት እንደ ምሳሌ መውሰድ እንችላለን።

እነዚህ ታላላቅ ሰዎች ለፍቶ አዳሪነት ምን ያህል ትልቅ ቦታ እንደሰጡት እና ለህብረተሰባቸው ምን ያህል እንደተጉ አሳይተዋል።

በርቱ ለማለት ነዉ😊

https://t.me/abukiweb
https://t.me/abukiweb


ለመጀመሪያ ጊዜ ቱርክ እንደሄድኩ እንግዳ ከሆኑብኝ ነገሮች አንዱ እጅግ ንጹህና ውብ ሱፍ የለበሱና ፍጹም ፕሮቶኮላቸውን የጠበቁ ሰዎች መንገድ ላይ የተለያዩ ጥቃቅን እቃዎችን ሲሽጡ መመልከቴ ነበር። በቆይታ የተረዳሁት በርካታ የባንክ ሰራተኞች፥ ሲቪል ሰርቫንቶች፥ መምህራን እንዲሁም በተለያዩ ተቋማት ቋሚ ሰራ ያላቸው ሰዎች ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት በትርፍ ሰዐታቸው የመንገድ ላይ ሸያጭ ላይ መሰማራት የተለመደ መሆኑን ነበር።እንቅስቃሴ የሚበዛባቸው ጎዳናዎች ላይ በመቆም የባንክ ሰራተኛው ካልሲ፥ መምህሩ ጌጣ ጌጥ፥ የመንግስት ሰራተኛው ውሃ ሊሸጡ ይችላሉ። የዚህ አይነት ትርፍ ሰራ ሀገራችን እምብዛም ስላልተለመደ ለረጅም ጊዜ እንግዳ ይሆንብኝ ነበር።

በሀገራችን ዛሬም ድረስ የተለመደው ማህበራዊ አመለካከት አንድን ሰው ከአንድ ሙያ ጋር ማሰተሳሰር ነው። መምህሩ ከማሰተማር፥ አሊሙ ከማቅራት፥ ዳዒው ከመሰበክ፥ ማህበረሰብ አንቂው ከአክቲቪዝም፥ ምሁሩ እውቀት ከማሰፋፋት ጋር ብቻ ይያያዛሉ። ከዚህ ማዕቀፍ የወጣ ሰራ ሲሰሩ ለብዙዎች እንግዳ ይሆናል፥ አንዳንዱም ተቃውሞውን ያሰማል። ይህ እሳቤ ብዙዎች ከሙያቸው ያለፈ ሌላ ሰራ ላይ በንቃትና በነጻነት እንዳይሳተፉ ማነቆ ሆኗል። ጊዜው፥ እውቀቱ፥ ፍላጎቱና እድሉ እያላቸው የማህበረሰቡን እሳቤ ላለመቃረን ሲሉ ብዙ የሚለወጡበትን እድል ያመክናሉ።

አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ አይደለም የገንዘብ ነጻነት የሚሻ መደበኛ የሚባል ኑሮ ለመኖርም ሁለት፥ ሶሰትና አራት ገቢ የሚያሰገኙ ዘርፎች ላይ መሳተፍ ግድ ይላል።
ለራሰ የሰጠነው ወይም ማህበረሰብ ያሸከመን ደረጃም ሆነ ማዕረግ ከመልፋትና ከመጣርና ከምንታወቅበት ሙያ ውጪ ከመስራት ሊያግደን አይገባም። እንዴት መምህር ሁኜ፥ ባንክ እየሰራሁ፥ ዶክትሬት ጭኜ፥ ዑስታዝና ሽኽ ተብዬ፥ ሲቪል ሰርቫንት ተደርጌ ይሄን እሰራለሁ እያልክ "ብራንድህን" የምትጠብቅበት ዘመን አልፏል። በሀላል መንገድ ለፍቶ አዳሪ ሁን፥ ሌላ ባታተርፍ የአላህን ውዴታ ማግኛ ሰበብ ይሆንሃል።

ኢሰታንቡል የሚገኘው እድሜ ጠገቡና ትልቁ ገበያ Grand Bazaar መግቢያ ላይ እንዲህ የሚል ጹሁፍ ተሰቅሏል:

" ለፍቶ አዳሪ የአላህ ወዳጅ ነው"

[ኢብራሂም አብዱ]


ውድ ቤተሰቦች እንደምን ናችሁ?
እንደምታውቁት ብዙ ወጣቶች፣ በተለይም ሴቶችና ኒቃቢስት እህቶቻችን፣ በክረምቱ ወቅት ወይም በዓመቱ ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት የ internship/ተለማማጅነት እድል ለማግኘት ይቸገራሉ። ይህንን ችግር ተረድቻለሁ። ለዚህም ነው ለወንድሞቻችንም ሆነ ለሴት ተማሪዎች፣ በተለይም ለኒቃቢስት እህቶቻችን፣ የ internship እድል መስጠት የምትችሉ ሰዎች ካላችሁ ብታሳውቁኝ በደስታ በቻናሌ መልዕክታቹ ይተላለፋል።
ማንኛውም አይነት ድርጅት፣ ንግድ ወይም ግለሰብ internship ለመቀበል ፍቃደኛ ከሆኑ እባካችሁ በግሩፕ ላይ ወይም በግል አድራሻዬ ያሳውቁኝ። ይህ ለወጣቶች፣ በተለይም ለሴቶችና ለኒቃቢስት እህቶቻችን ትልቅ የሥራ ልምድ እድል ይፈጥራል።
ለምታደርጉት ትብብርና ድጋፍ ጀዛኩሙላህ ኸይረን።

ሼር በማድረግ ያግዙኝ✅
ቻናሉን ለመቀላቀል
https://t.me/abukiweb


ቆይ ተማሪዎች ለግሬዳችሁ ትጨነቃላችሁ ከዛስ⁉️
ከዛም ትመረቃላችሁ‼️አልሀምዱሊላህ።
~
ግን ስራ የሚባል ነገር ዉጭ ስትወጡ  የለም ወይም እስከሚገኝ አስቸጋሪ ነዉ ።
ግሬድ አንዳንዴ ከግቢ ማያልፍበት አጋጣሚ አለ። ስለዚህ ከትምህርታችሁ ጎን ለጎን የኦንላይ ትምህርቶች  ተማሩ። ተዉ  ተማሪዎች  አደራ  እንዳትሸዉዱ።ከታላቆቻችሁ ልምድ ውሱዱ።


share
ቻናሉ ለመቀላቀል👇
https://t.me/abukiweb


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
አላህ ለረመዳን ያድርሰን🤲🤲
በጣት የሚቆጠሩ ቀናት ብቻ ቀሩት✅


ቻናሉ ለመቀላቀል👇
https://t.me/abukiweb


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
📌 pin
የምንፈልገዉ ቻናል ወይም የግል አካዉንት pin ለማድረግ ቀላስ Step

ሁሌም መርሳት የማንፈልገዉ ሰዉ😊
ወይም ቴሌግራም ስንገባ  ግዴታ ማየት ያሉብን  ቻናሎች ወደ ታች እንዳይወርዱብን በጣም ጠቃሚ ነዉ መቶም ይሁን ሁለት መቶ ቻናል ቢኖር  በየግዜዉ አዲስ ነገር ሲለቁ የምንፈለገዉ ግን ሁሌም እላይ pin ሆኖ ይቀመጣል‼️


step 1 የምንፈልገዉ ቻናል ላይ አንዴ ጠበቅ አድርገን መያዝ

step 2  ከላይ 3 ነጠብብጣቡ በመንካት Pin (📌) የሚለዉ መምረጥ።
ከዛም Pin (📌) ሆኖ እናገኘዋለን።
ከዚህ ቦኃላ የምንፈልገዉ ቻናል ወይም ግለሰብ   አካዉንት pin ማድረግ ይልድብን።

ከጠቀማችሁ ሼር🤝
ቻናሉ ለመቀላቀል👇
https://t.me/abukiweb


መሰረት ግዜ ይወስዳል። መሰረት ከሌላችሁ ወዲያው ለማደግ አትሯሯጡ። መጀመሪያ ወደ ታች፣ ከዛ ወደ ላይ። ስር ወደ ውስጥ ከሌለክ፣ ማንም መቶ ይነቅልሃል፤ ጀምረህ ታቆማለህ። መነሳትና መጀመር ሁሌም ቢሆን ጊዜ ይወስዳል። እስክትነሱ ከታች ያለው ጊዜ በጣም አድካሚ አሰልቺ ነው ነገር ግን ቡሃላ ለፍጥነት እና ለጥንካሬ ስለሚጠቅማችሁ እንደምንም ታግሶ ማለፍ የተሻለ ነው ።
ሁሌም አስተውሉ ምትሰሩት ስራ ላይ ድክመት እና መንገጫገጭ ካለ ገና መሰረት ላይ እንደሆናችሁ አስታውሱ ።

በተለይ Developer የሆናችሁ።
©
@abukiweb


ፁሁፉ ቢበዛም

ምርጥ መልዕክት አለዉ👌

እሁድም ስለ ሆነ አንብቡ……


« አንዳንዴ ልጅነት ንፅህናው ደስ ይላል። ቤት ውስጥ ታናሾቼን አወራቸዋለሁ። አንዳንዴ የማደረገውን ነገር ምክንያቱን እነግራቸዋለሁ፣ አንዳንዴ ደግሞ እራሳቸው እንዲደርሱበት እጠቁማቸዋለሁ። ባለፈው ስለ ገንዘብ ያላቸውን አረዳድ እንዲያስተካክሉና በትክክለኛው መንገድ ከቢዝነስ አንግል እንዴት ማየት እንዳለባቸው እያወራን ነበር(እኔ በጣም የምቸገርበት ስለሆነ ያን እንዲደግሙት ስለማልፈልግ ነው።) ጊዜው ወደ ቴክኖሎጂው በጣም እያደላ ስለሆነ ወደዛ እንዲያስቡ እኔም ያንን ለማድረግ እየሞከርኩ እንደሆነ አወራን። ታድያ ጋሽ ኡስማን ምን አለ
‹ ባቢ አሁን ምንም ገንዘብ እያገኘሁ ስላልሆነ ትምህርቱን አቁሜ ለምን ስራ አልጀምርም አለ! › አይ እውቀት ሲኖርህ መልካም ነው የምታገኘውንም በደንብ ለመጠቀም እንዲሁም እውቀት በደንብ ገንዘብ ለማግኘት ጥሩ መንገድ ስለሆነ ትምህርት አስፈላጊ ነው ተባባልን። ተስማማ። ቀጥተኛ አረዳዱን አንዳንዴ እወድለታለሁ።
የሆነ ሳምንት ያሀል ነገር አለፈ። ከዚያም ‹ ባቢ ቲክቶክ አሰራኝ። ታዋቂ እሆንና ብዙ ገንዘብ አገኛለሁ፣ ለእማ እና አባ የሚፈልጉትን አደርግላቸዋለሁ! › አለ።
ታዋቂ ስለሆንክ ብቻ ገንዘብ ታገኛለህ ማለት አይደለም። ደግሞ ታዋቂ መሆን በራሱ የራሱ የሆነ ችግር አለው። ላንተ አሁን ላይ የሚጠቅምህ ቢሆን ኖሮ ሳትጠይቀኝ እራሱ አሰራህ ነበር። በደንብ በእውቀትህ ከጎበዝክ የምትፈልገውን ታደርግላቸዋለህ አልኩት። ተስማማን። ያን ሰሞን ነገሮችን ው ቢዝነስ ስለመቀየር በማሰብ ተጠምዶ ነበር።
ብቻ የሆኑ ጊዜያት አለፉ። በቃ ሁሉንም እርግፍ አድርጎ ረሳው። እንደአጋጣሚ ሰሞኑን ፌስቡክ ልክ ልከፍት ስል አየና ‹ባቢ ይሄ ነገር አታብዛ ጥሩ አይደለም ይቅርብህ አለኝ! › እሺ ብዬ አይኑ እያየ ዘጋሁትና ተቀመጥኩ። የሆነ ደስ አለው።
ምን ለማለት መሰላችሁ ታናናሽ እህት ወንድሞቻችሁን አውሯቸው፣ በተለያየ መንገድ እንደ እድሜያቸው እይታዎችን አመላክቷቸው። ከምንም በላይ ከራሳቸው ጋር እንጂ ከሌሎች ሰዎች ጋር ንፅፅር ውስጥ እንዳይገቡ ንገሯቸው። የሌሎች ሰዎች ስኬት እና ውጤት እንዲያስደስታቸው አድርጋችሁ ምከሯቸው። እያንዳንዱ በልጅነታቸው የምትነግሯቸው ነገር አዕምሯቸው ላይ ይመዘገባል። ዛሬ በሀላል መንገድ ገንዘብ ስለማግኘት ስታወሯቸው ወድያው ይተገብሩታል ማለት አይደለም፣ ጭራሽም ትዝ ላይላቸው ይችላል። ነገር ግን የሆነ ሰዓት ላይ እያደጉ ሲመጡ የሆነ አይነት እይታን ያዳብራሉ።
ከምንም በላይ በፍፁም ፈፅሞ ሊያልፉት የማይገባውን አንድ ቀይ መስመር አብጁላቸው። ይህም ነገሮችን ሲሰሩ ለሰው ብለው ሳይሆን ለአላህ ብለው እንዲያደርጉ አስታውሷቸው። ሁሌም ላያደርጉት ይችላሉ ግን ስሜቱን እንዲያዳብሩ ገፋፏቸው። ሌላው የወላጆቻቸውን ክብር እንዲጠብቁ አድርጓቸው። ታላላቆቻቸው ወደ ቤት ሲመጡ በአክብሮት መቀበልን አሳዯቸው።
ዋጋ እንዳላቸው፣ የሚወደዱ እንደሆኑ፣ ጎበዝ እንደሆኑ፣ ቆንጆ እንደሆኑ እናንተ ቀድማችሁ ንገሯቸው። እህትና ወንድሞቻችሁ ጠላቶቻችሁ አይደሉም፣ አውሩ ተጨዋወቱ፣ ተመካከሩ፣ ተከባበሩ። ከምንም በላይ ውሸታም አትሁኑባቸው። የውሸት ቃል እና ተስፋ አትስጧቸው። ከሌላችሁ አሁን የለኝም በሏቸው፣ ኖሯችሁ ለሌላ ጉዳይ የምትፈልጉት ከሆነና ካልበቃችሁ በግልፅ ንገሯቸው። ያንን ታማኝነት እንዲያዳብሩ አድርጉ።
እናንተ ተቸግራችሁ እያለፋችሁበት ያለውን ወይም ያለፋችሁትን እንዲደግሙት አትለጎሙባቸው። ውድድ ስታደርጓቸው እስከ ጥግ፣ ቅብጥ ሲሉም እስከ ጥግ አደብ ማስያዝ ግዴታችን ነው። ታላላቆቻችን ከሆኑ ክብራቸውን ጠብቀን ማስታወስም የግድ ይላል። »
[ አብዱልሀኪም ሰፋ ]


የብዙዎቻችን ስህተት‼️

ኮርስ ጨረስን ማለት ስራ እናገኛለን ማለት አይደለም!

ብዙዎች web developmnet  ወይም አንድ online ኮርስ ጨርሰው ወዲያውኑ ስራ አገኛለሁ ብለው ያስባሉ። ይህ ግን እውነታው አይደለም።

ለምን? ኮርስ መጨረስ መጀመሪያው እርምጃ ብቻ ነው። እውነተኛው ስኬት የሚመጣው በየቀኑ በመለማመድ፣ ፕሮጀክቶች ላይ በመስራት እና ስኪልህን በማሳደግ ነው።


ምሳሌ 1: እንደ አንድ አትሌት አድርገህ አስብ። ጂም ሄደህ ጥቂት ክብደት ስታነሳ ወዲያውኑ ኦሎምፒክ ላይ ትወዳደራለህ ብለህ ታስባለህ? አይደል? ስኬታማ አትሌት መሆን የሚጠይቀው በየቀኑ በመለማመድ፣ ጡንቻህን በማጠናከር እና አቅምህን በማሳደግ ነው። በተለይም ጠዋት ወይም ሌሊት ተነስቶ ልምምድ በማድረግ ይህንን ግብ ለማሳካት የሚጥር ነው።


ምሳሌ 2: ቁርአንን በቃል መያዝ የሚፈልግ ሰውን አስብ። አንድ ጊዜ ቁርአንን አንብቦ ወዲያውኑ ሀፊዝ ይሆናል ብሎ ያስባል? አይደል? ሀፊዝ መሆን የሚጠይቀው በየቀኑ በመድገም፣ በመተንተን እና በመረዳት ላይ ያለ ረጅምና ከባድ ትግል ነው። በተለይም ሌሊት ተነስቶ ቁርአንን በመደጋገም ይህንን ግብ ለማሳካት የሚጥር ነው።

እንደዚሁም፣ አንድ ፕሮግራመር መሆን የሚፈልግ ሰው አንድ ኮርስ ጨርሶ ብቻ ስራ ያገኛል ብሎ ማሰብ ትክክል አይደለም። ስኬታማ ፕሮግራመር ለመሆን በየቀኑ ኮድ መጻፍ፣ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን መማር እና ፕሮጀክቶች ላይ መስራት ያስፈልጋል።

ስለዚህ ምን ታደርጋለህ?
ተለማመድ፡ የተማርከውን ነገር በየቀኑ ተለማመድ።
ፕሮጀክቶች ስራ: ትንንሽም ይሁኑ ትላልቅ፣ ፕሮጀክቶች ላይ ስራ።
አዳዲስ ነገሮችን ተማር: ቴክኖሎጂ በፍጥነት እየተለወጠ ነው። ስለዚህ ሁልጊዜ አዳዲስ ነገሮችን ለመማር ተዘጋጅ።

#repost
ቻናሉ ለመቀላቀል👇
Abuki Tech
HTML Full Course✅


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
ወንድማችን መካ ጀማል(Ibnu Jemal)ሰሞኑ በ innovation and technology minister ተጋብዘዉ ስለ 5millions coders አጠር ያለች ግንዛቤ ለመፍጠር ሞክረዋል:: ከ EBS በነበራቸዉ ቆይታ ትምህርቱ እንዴት ነው? በምን መልኩ መማር አለብን? እንዲሁም የሚሰጠው እንዴት ነው? ምን ያስፈልገናል? እና የመሳሰሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክረዋል።

ይህ ወንድማችን Ibnu Jemal የ Abuki Coders  የወንዶች ግሩፕ ዋና አስተማሪና ተቆጣጣሪ  ነዉ እሱ ስላገኘን አልሀምዱሊላህ  ደስ ብሎናል አላህ እዉቀቱ ይጨምርለት አላህ ሀሳቡ
እንዲያሳካለት ምኞቴ ነዉ።


አሁንም ቢሆን ገና 32% ብቻ ነዉ ትምህርት የጨረሱት ገብታችሁ ነፃ ነዉ ተማሩ ተማሩ ተማሩ።

ያልገባችሁ ጠይቁን።

ለመመዝገብ ይህን ሊንክ ይጠቀሙ።
👇👇👇👇
https://t.me/abukiweb/221


አንድ የአላህ ባሪያ ላይ
የዱንያም
የአኼራም እዉቀት ኖሮት በዛም እዉቀቱ ጠቃሚ ነገር ሲሰራበት እንዴት ነዉ የሚያምረዉ🥰አላህ ሁለቱም ይወፍቀን ከኢህላስ ጋር🤲።


ቻናሉ ለመቀላቀል👇
https://t.me/abukiweb


በነገራችን ላይ ይህ ለኒቃብ ያለቸዉ ጭፍን ጥላቻ እንጂ እንዲዉ በር ላይ አንድ ፈታሽ ማስቀመጥ ቀላል መፍትሄ ነበር ።
👇
https://t.me/abukiweb/309

ግን የኛ አላማ እነሱ ለሚያነሱት ማማኸኛ መፍትሄ እንዳለዉ ለማሳየት ያክል ነዉ።

አሁንም ቢሆን ኒቃብ ሆነ ኢስላምን በጭፍን ከመጥላት ወጥተዉ ለሀገርም ለወገንም የሚበጀዉን መፍትሔ ብያፀድቁ ይሻላል።

ቻናሉ ለመቀላቀል👇
https://t.me/abukiweb


እኛ ሙስሊሞች ቫላንታይን ዴይ የሚባል ነገር አናዉቅም።

ተማሪዎች በተለይ ዋ ተጠንቀቁ🛑

https://t.me/abukiweb


🛑ለኒቃቢስት ተማሪዎች🛑 መፍትሔ የሚሆን ድንቅ የቴክኖሎጂ ፈጠራ‼️☘🍀☘🍀☘🍀
👇👇

https://youtu.be/wDekeH_UE38?si=lmvdAD0BZU7eiQoK


እስካሁን ያላያቹት ትኖራላቹ
ይህንን ድንቅ ስራ የሰራው ወንድማችን ነስሩ ይባላል። አላህ እውቀቱን ይጨምርለትና!
የሱ መነሻ ሀሳብ ለሚቃርቡት የደህንነት ችግር አንጻር ኒቃብ ለመከልከል ለሚያስቡ ሰዎች አፍ የሚያዘጋ መፍትሔ ነው። ይህንን የፈጠራ ስራ የሰራው ራሱ ወንድማችን ነስሩ ሲሆን፣ ለዚህም Specific Arduino እና C#  ሌሎችምን ቋንቋዎች ተጠቅሟል።
እንዴት እንደሚሰራ እና ለተጨማሪ ማብራሪያ 👉
ቪድዮውን ይመልከቱ።
ለበለጠ መረጃ ወንድማችንን ለማግኘት እና ፕሮጀክቱን ለማስቀጠል ያነጋግሩት።
ይህ ነው ተምረህ በምትችለው ለዲንህ መብቃት እና ማሰብ ማለት!
ነስሩ ለማግኘት
👉
https://me.kertech.co/nes

Share Share

ቻናሉ ለመቀላቀል👇
https://t.me/abukiweb
https://t.me/abukiweb


ሙስሊሙ ማህበረሰብ ልጆቹን፣ እህቶቹን፣ ወንድሞቹን፣ ጎረቤቶቹን... በሁሉም መስክ ማለትም በዲኒ፣ በቴክኖሎጂ፣ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ ሳይንስ፣ በጤና እና በአጠቃላይ በሁሉም የሕይወት ዘርፎች መማርና ማብቃት ይኖርበታል። ይህ ማለት የእውቀት እድገትና የህብረተሰብ መሻሻል ለማምጣት ወሳኝ ነው።
እስልምና በእውቀት ላይ ትልቅ ቦታ ይሰጣል፣ ቁርአንም ሆነ ሐዲሶች የእውቀትን አስፈላጊነት በተደጋጋሚ ያሳስባሉ። ስለዚህም ሙስሊሞች የእውቀት ፍላጎታቸውን ማሟላትና ለሌሎችም ማካፈል ይገባቸዋል


ፁሁፍ ፡  @abukiweb
ድምፅ፡ Ustaz IbnuMunewor ደርስ የተወሰደ

ሼር🤝
ቻናል👇
https://t.me/abukiweb

20 last posts shown.