Forward from: Bahiru Teka
👉 ረመዳን ሁለተኛው አስር
የተከበራችሁ ምእመናን የአላህ ባሮች እንሆ ረመዳን የመጀመሪያው 10 አልቆ ሁለተኛው ሊገባ ነው ። እስኪ ሁላችንም ራሳችንን እንጠይቅ ።
ከቁርኣን ጋር ምን ያክል ጊዜ አሳለፍን ?
ከዚክር ጋር
ከዱዓእ ጋር
ከሶላት ጋር
ከሶደቃ ጋር
ሁኔታችን ምን ያክል ተቀይሯል
ንግግራችን
ቀልዳችን
ትረባችን
ማሽማጠጣችን
መሳደባችን
ባጠቃላይ ከረመዳን በፊት ከነበረን ባህሪ ምን ያክል ተቀይረናል ? በጊዜያችን ምን ያክል ተጠቅመናል ? በምን እያጠፋነው ነው ?
ጊዚ ከሰከንድ አመልካች ወደ ደቂቃ አመልካች በተሸጋገረ ቁጥር እኛ ደግሞ ከተወሰነልን ጊዜ እየተሸረፈ ወደ ቀብር አየተጠጋን ነው ።
ይህ አላህ ለድክመታችን ማካካሻ የሰጠን ገፀ በረከት ( የረመዳን ወር ) ካልተጠቀምንበት ምንም ሳይዛነፍ ጉዞዉን መጨረሱ አይቀርም ። ቀኑ ለለሊት ለሊቱ ለቀን እየተቀባበሉ ሳምንት እያለ ወር ያልቃል ። የተወሰነው የገፀ በረከት ጊዜ ከዚያም የእድሜ መንገድ ጉዞዉን ይቀጥላል በዱንያ ላይ የተወሰነለት ገደብ እስኪያበቃ
የሚጠብቀን ከሁለት አንድ ነው ። ዘላለማዊ ፀፀት ወይም ዘላለማዊ የተድላ ህይወት
የፈለግነውን መምረጥ እንችላለን ። ግን እጅ በማውጣት ሳይሆን በስራ ነው ።
አላህ ካገራላቸው ባሮቹ ያድርገን ።
http://t.me/bahruteka