ጃሂሊያ (መሃይምነት) የሚለው መጠሪያ በቁርዓን ውስጥ ከአራት ቃሎች ጋር ተጣምሯል፦
1- የመሃይምነትን መጠራጠር
ظن الجاهِليّة
2- የመሃይምነት ፍርድ
أفحُكمَ الجاهلِيّة
3- የመሃይምነት መገላለጥ
تبَرُّجَ الجاهلِيّةِ
4- የመሃይምነት ደራ
حَمِيّة الجاهلِيّة
የመጀመሪያው፦ ይህ ኡመት በልብ መበላሸት እንዲሚበላሽ ጠቋሚ ነው።
ሁለተኛው፦ ይህ ኡመት በፍርድ መበላሸት እንደሚበላሽ ጠቋሚ ነው።
ሶስተኛው፦ ይህ ኡመት በሴቶች መበላሸት እንደሚበላሽ ጠቋሚ ነው።
አራተኛው፦
ይህ ኡመት ለጎሣ እና ለዘር በሚደረግ ጭፍን ተከታይነት እና ዘረኝነት እንደሚበላሽ ጠቋሚ ነው። እኚህ አራቱ የመሃይማን ድርጊቶች በዚህች ኡመት ላይ ከተገኙ ይህን ኡመት ያዋረዱት እና ያጠፉት ከመሆን ቅሮት የላቸውም!
🌿🪴🪴🌿🪴🌿🪴
╭┅━━•🍃⚘🍃•━━━┅╮
⚘ ⚘
https://t.me/mesjidalteqwawenabo╰┅━━•🍃⚘🍃•━━━┅╯