በዚኽች ዕለት የካቲት 29 ቀን በዓመታዊ የዕረፍት በዓሏ ታስባ የምትውለው እናታችን ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ማኅበርተኞቿ የሆኑ ደናግል መነኮሳት ልጆቿ በእባብ መርዝ ምክንያት ሞቱ፡፡ እናታችን ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስም የልጆቿን መሞት ባየች ጊዜ ወደ ልዑል እግዚአብሔር በዕንባ ጸለየች፡፡ ከዚህም በኃላ እነዚያ በእባብ መርዝ የሞቱ ልጆቿ በጸሎቷ ከሞቱ ተነሡ፡፡ እነርሱም በሰማይ ያዩትን የእናታቸውን የቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስን ክብርና የተዘጋጀላትን ርስት አይተው እንዳደነቁ ነገሯት፡፡ ሁላቸውም እራት አብረው ተመገቡ፡፡ በዚህም ጊዜ እናታችን ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ እነዚያን በጸሎቷ ከሞት ያስነሣቻቸውን ልጆቿን "....ውዳሴ ከንቱ እንዳይሆንብኝ ይህንን ለሰው አትንገሩ" አለቻቸው፡፡ "ነገር ግን ከዕረፍቴ በኃላ ተናገሩ" አለቻቸው።"
+ + +
ዳግመኛም ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ይኽን ተአምር አደረገች፡- ኃጢአቷ የበዛ አንዲት ሴት ነበረች፤ ለበደሏም ወሰን የለውም፡፡ እርሷም ወደ እናታችን ወደ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ሔዳ በጸሎቷና በልመናዋ ተማጸነች፡፡ የሠራችው ኃጢአት ሕፃናትን በስራይ እንዳስወረደች 10 ጊዜም የተለያዩ ባሎቿን እንደገደለች ነገረቻት፡፡
በዚኽም ጊዜ እናታችን ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ "... ኃጢአትሽን ለቀሲስ እከሌ ተናዘዥ" አለቻትና ስለ እርሷ ጸለየችላት፡፡ ኃጥእዋ ሴትም እናታችን እንዳዘዘቻት ሄዳ ኃጢአቷን ለካህን ተናዘዘች፡፡ በፍጹም ልቧም ንስሓ ገብታ በጾሞ በጸሎት ጸናች፡፡ እግዚአብሔርም ንስሓዋን ተቀብሎ ጸሎቷን ሰምቶ አንቺ ሴት ከዚህ በኃላ ኃጢአት አትስሪ ብሎ ተናገራት፡፡ ያቺም ሴት እግዚአብሔር ኃጢአቷን ይቅር እንዳላት ባየች ጊዜ ዕድሜ ዘመኗን በቀኖና አሳልፋ በሰላም ዐረፈች፡፡ አስማንድዮስ የተባለ ጋኔን በወለተ ራጉኤል ጭን ላይ አድሮ ባሎቿን እየገደለ ሲያሠቃያት ቅዱስ ሩፋኤል ጋኔኑን አስጨንቆ እንዳስወጣላት ሁሉ (ጦቢት 3፡8-17) ልዑል እግዚአብሔርም በቸርነቱና በምሕረቱ በቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስም ምልጃና ጸሎት ይቅር ብሏታልና መንግሥተ ሰማያትን አወረሳት፡፡
+ + +
ከዕለታት በአንደኛው ቀን ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ በገዳማትና በተራራዎች መካከል ስትሄድ ከአንድ ሰው ቤት አደሩ፡፡ የዚያም ሰው አንዲት ሴት ልጅ ነበረችው፡፡ እርሷም በጠና ደዌ የታመመች ነበረች፡፡ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስም በልጅቷ ላይ በጸለየችላት ጊዜ ወዲያው ከደዌዋ ዳነች፡፡ የሀገሩ ሰዎችም ይህንን ተአምር ሲሰሙ ተሰበሰቡ፡፡ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ወንድ መስላቸው ነበርና ሰው ሁሉ ሥራዋን እንዳያውቁ ጃንደረባ መስላ ትኖር ዘንድ ወደ እግዚአብሔር እንደለመነች አላወቁምና፡፡
ከዚኽም በኋላ የሀገሩ ሰዎች ‹‹አባታችን እባክህ ከዚህ ተቀመጥ፣ ከዚህ ቦታ ተቀምጠህ ትጸልይልን ዘንድ ሕመምተኞችን ትፈውስልን ዘንድ…›› ብለው ተማጸኑ፡፡ በቤተ ክርስቲያንም አጠገብ ማረፊያ ሠሩ፡፡ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስም በዚያ ሆና ስትጸልይ ስፍር ቁጥር የሌላቸው የሌላቸው ብዙ ሕሙማንን በተአምራት በጸሎቷ ፈወሰች፡፡ ከሰው ብዛትና መጨናነቅ የተነሣ ቦታዋ በሰው ተሞልታ ነበር፡፡ የአገረ ገዥውም ሚስት መጥታ ‹‹አባቴ በጸሎትዎ አስቡኝ፣ አይርሱኝ…›› ብላ ብዙ ምሥጢር ነገረቻት፡፡ ከዚህም በኋላ አንዲትን ሴት ከእናታችን ወጥታ ስትሄድ አንድ ሰው በመንገድ አገኛትና በኃጢአት እንቅፋት ወደቁ፡፡ በዚህም ጊዜ ፀነሰች፤ ባሏም ፅንሷን አወቀና ከማን እንደፀነሰች አስጨንቆ ጠየቃት፡፡ ሴቲቱም ‹‹ይህ መነኩሴ ወደ እርሱ ዘንድ ኔድኩ ጊዜ አስገድዶ ደፈረኝና ፀነስኩ›› ብላ በእናታችን ላይ በሐሰት መሰከረች፡፡ በዚህም ጊዜ ባሏ በጣም ተናዶ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስን አሠራት፡፡ በግርፋትም ያሰቃያት ነበር፡፡ የሀገሩ ሰዎች ግን ይፈታት ዘንድ ይጠይቁት ነበር፡፡ በመጨረሻም ‹‹በቃ ልጁን ይዞ ይሂድ…›› ብለው ስለመከሩት ሰውየው ለቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ሕፃኗን ሰጥቶ አሰናበታት፡፡
እናታችንም ሕፃኗን በጥበብ ወተት አሳደገቻት፡፡ መዝሙረ ዳዊትንም እያስተማረቻት በጸሎት በጾም አሳገቻት፡፡ ልጅቱም ስታድግ መነኮሰች፡፡ ከዚህም በኋላ ያች ክፉ ሴት ማለት እናቷ በጸና ታመመች፡፡ እርሷም በታመመች ጊዜ እናታችንን ወንድ መስላት ስለነበር ‹‹..እርሱ ንጹሕ ነው ከእርሱ አይደለም ያረገዝኩት›› ብላ ተናገረች፡፡ ያ የደፈራት ሰው ግን በመብረቅ ሞተ፡፡ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስም ያሰሯትና የገረፏት ሰዎች በኋላ ላይ ሴት እንደሆነች ባወቁ ጊዜ እጅግ ተጸጽተው አለቀሱ፡፡ ከእግሯም ሥር ወድቀው ‹‹..ሳናውቅ አስቀይመንሻል ይቅር በይን›› ብለው ለመኗት፡፡ እናታችንም ይቅር አለቻቸው፡፡
በእናታችን ፍቅርተ ክርስቶስ ገዳም ውስጥ ዱባ በብዛት ይበቅል ነበር፡፡ ከፍሬውም ብዛት የተነሣ እርሷንና ሌሎቹንም ቅዱሳን ሁሉ ሌሊት ወደ ጸሎት ሲሄዱ የበሰበሰው ዱባ እንደ ጭቃ እያዳለጠ ይጥላቸው ነበር፡፡ እግራቸውንም ይውጣቸው ነበር፡፡ ያልበሰለውም ዱባ እንቅፋት እየሆነ ያሰነካክላቸው ነበር፡፡ ከዚህም በኋላ እናታችን ፍቅርተ ክርስቶስ ያን ዱባ ‹በዚህ ገዳም ውስጥ ብትበቅል እንጂ ፍሬ አትስጥ› ብላ አዘዘችው፡፡ ዱባውም ቃሏን አክብሮ እስካሁን ድረስ ቅጠሉ ቢዘረፈፍም፣ አበባው ቢያሳሳም፣ ሐረጉ ቢጎተትም፣ ዱባው ግን በገዳሙ ውስጥ ፈጽሞ ፍሬን አያፈራም፡፡ ከገዳሙ ውጭ ያሉ ሰዎች ግን ዱባውን እየተከሉ ፍሬም እያፈራላቸው ይጠቀሙበታል፡፡ በገዳሙ ክልል ውስጥ ፈጽሞ ፍሬን አያፈራም፡፡ ይኽም አባታችን አዳም እናታችን ሔዋን በንጽሕናና በቅድስና ሳሉ እንስሳትና ዕፅዋት ይታዘዙላቸው እንደነበር ሁሉ መድኀኔዓለም ክርስቶስ በሞቱ የአዳምንና የሔዋንን የቀድሞ ጸጋቸውን እንደመላቸው ያሳያል፡፡ የክብር ባለቤት ጌታችን ዓለምን በደሙ ካዳነ በኃላ ለቅዱሳኑ ዕፅዋትና እንስሳት መታዘዛቸው ለዚህ ነው፡፡
የእመ ምኡዟ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ባሕርን በአጽፏ ተሻግራ ወደ ሀገረ ናግራን አገር ሄዳ ወንጌልን የሰበከች ታላቅ ሐዋርያዊት እናታችን ናት፡፡ ለእርሷም እመቤታችን ተገልጣላት በጌታችን መከራ ሞት ምክንያት ስለደረሱባት ሀዘናት የነገረቻት፣ የፈለገችውንም ታደርግበት ዘንድ የእጇን መስቀል የሰጠቻት ሰሆን ሰውን ወደሚበሉ ሰዎች አገር ሄዳ ስንዴን በአንድ ቀን ብቻ ዘርታ፣ አብቅላ፣ አጭዳ፣ ፈጭታ ለምግብነት አብቅታ ከመገበቻቸው በኋላ እንደዚህ እያደረጉ እየሠሩ እንዲበሉ አስተምራ አስጠምቃቸው ስድስት አብያተ ክርስቲያናትን የሠራችላቸውና ቅዱስ ወንጌልን፣ ስንክሳርን፣ ሃይማኖተ አበውን፣ ግንዘትን፣ መዝሙረ ዳዊትን፣ አርጋኖንን ሁሉ በእጇ ጽፋ ያስቀመጠችላቸው ሐዋርያዊት እናታችን ስትሆን በሌላም በኩል ሙታንን እያስነሣች ለዐፄ ሱስንዮስ ስለእውነት እንዲመሰክሩለት ታደርግ የነበረችና እርሷም ራሷ አንገቷን ተሰይፋ ሰማዕትነትን የተቀበለችና ጌታችን ከሞት ያስነሣት ቅድስት ናት፡፡
ረድኤት በረከቷ ይደርብን በጸሎቷ ይማረን!
(ገድለ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ)
(ለ3ኛ ጊዜ በተከፈተው አዲስ ቻናል በኩልም በጽሑፍና በድምፅ ይከታተሉ።)
https://t.me/kegedilatandebet27217